መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #138
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 138

Psalm 138

1 አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሰምተኸኛልና በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።

1 I will praise thee with my whole heart: before the gods will I sing praise unto thee.

2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

2 I will worship toward thy holy temple, and praise thy name for thy lovingkindness and for thy truth: for thou hast magnified thy word above all thy name.

3 በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት።

3 In the day when I cried thou answeredst me, and strengthenedst me with strength in my soul.

4 አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።

4 All the kings of the earth shall praise thee, O Lord, when they hear the words of thy mouth.

5 በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና።

5 Yea, they shall sing in the ways of the Lord: for great is the glory of the Lord.

6 እግዚአብሔር ከፍ ያለ ነውና፥ ወደ ችግረኞችም ይመለከታልና ትዕቢተኞችንም ከሩቅ ያውቃል።

6 Though the Lord be high, yet hath he respect unto the lowly: but the proud he knoweth afar off.

7 በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።

7 Though I walk in the midst of trouble, thou wilt revive me: thou shalt stretch forth thine hand against the wrath of mine enemies, and thy right hand shall save me.

8 እግዚአብሔር ብድራትን ይመልስልኛል አቤቱ፥ ምሕረትህ ለዘላለም ነው አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።

8 The Lord will perfect that which concerneth me: thy mercy, O Lord, endureth for ever: forsake not the works of thine own hands.