ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #10
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 10

Exodus 10

1-2 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በግብፃውያን ያደረግሁትን ነገር ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጅህ በልጅ ልጅህም ጆሮች ትነግር ዘንድ፥ ይህችንም ተአምራቴን በመካከላቸው አደረግ ዘንድ የእርሱን የባሪያዎቹንም ልብ አደንድኜአለሁና ወደ ፈርዖን ግባ አለው።

1 And the Lord said unto Moses, Go in unto Pharaoh: for I have hardened his heart, and the heart of his servants, that I might shew these my signs before him:
2 And that thou mayest tell in the ears of thy son, and of thy son’s son, what things I have wrought in Egypt, and my signs which I have done among them; that ye may know how that I am the Lord.

3 ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ አሉትም። የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

3 And Moses and Aaron came in unto Pharaoh, and said unto him, Thus saith the Lord God of the Hebrews, How long wilt thou refuse to humble thyself before me? let my people go, that they may serve me.

4 ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ

4 Else, if thou refuse to let my people go, behold, to morrow will I bring the locusts into thy coast:

5 የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፥ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል

5 And they shall cover the face of the earth, that one cannot be able to see the earth: and they shall eat the residue of that which is escaped, which remaineth unto you from the hail, and shall eat every tree which groweth for you out of the field:

6 ቤቶችህም የባሪያዎችህም ሁሉ ቤቶች የግብፃውያንም ሁሉ ቤቶች በእነርሱ ይሞላል አባቶችህ የአባቶችህም አባቶች በምድር ላይ ከተቀመጡበት ቀን ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያላዩት ነው። ተመልሶም ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።

6 And they shall fill thy houses, and the houses of all thy servants, and the houses of all the Egyptians; which neither thy fathers, nor thy fathers’ fathers have seen, since the day that they were upon the earth unto this day. And he turned himself, and went out from Pharaoh.

7 የፈርዖንም ባሪያዎች። ይህ ሰው እስከ መቼ ዕንቅፋት ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ሰዎችን ልቀቅ ግብፅስ እንደ ጠፋች ገና አታውቅምን? አሉት።

7 And Pharaoh’s servants said unto him, How long shall this man be a snare unto us? let the men go, that they may serve the Lord their God: knowest thou not yet that Egypt is destroyed?

8 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን መልሶ አስመጣቸው። ሂዱ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው? አላቸው።

8 And Moses and Aaron were brought again unto Pharaoh: and he said unto them, Go, serve the Lord your God: but who are they that shall go?

9 ሙሴም፦ እኛ እንሄዳለን፥ የእግዚአብሔር በዓል ሆኖልናልና ታናናሾቻችንና ሽማግሌዎቻችን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም በጎቻችንና ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር ይሄዳሉ አለ።

9 And Moses said, We will go with our young and with our old, with our sons and with our daughters, with our flocks and with our herds will we go; for we must hold a feast unto the Lord.

10 ፈርዖንም። እናንተን ከልጆቻችሁ ጋር ስለቅቅ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ነገር ግን ክፉ ነገር በፊታችሁ እንደሚሆን ተመልከቱ።

10 And he said unto them, Let the Lord be so with you, as I will let you go, and your little ones: look to it; for evil is before you.

11 እንዲህም አይይደለም እናንተ ወንዶቹ ሂዱ፥ ይህን ፈልጋችኋልና እግዚአብሔርን አገልግሉ አላቸው። ከፈርዖንም ፊት አባረሩአቸው።

11 Not so: go now ye that are men, and serve the Lord; for that ye did desire. And they were driven out from Pharaoh’s presence.

12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በግብፅ አገር ላይ እንዲወጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ ስለ አንበጣዎች በግብፅ አገር ላይ እጅህን ዘርጋ አለው።

12 And the Lord said unto Moses, Stretch out thine hand over the land of Egypt for the locusts, that they may come up upon the land of Egypt, and eat every herb of the land, even all that the hail hath left.

13 ሙሴም በግብፅ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ እግዚአብሔርም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ ማለዳም በሆነ ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።

13 And Moses stretched forth his rod over the land of Egypt, and the Lord brought an east wind upon the land all that day, and all that night; and when it was morning, the east wind brought the locusts.

14 አንበጣዎችም በግብፅ አገር ሁሉ ላይ ወጡ፥ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጡ እጅግም ብዙ ነበሩ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፥ ወደ ፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም።

14 And the locusts went up over all the land of Egypt, and rested in all the coasts of Egypt: very grievous were they; before them there were no such locusts as they, neither after them shall be such.

15 የምድሩንም ፊት ፈጽመው ሸፈኑት አገሪቱም ጨለመች የአገሪቱን ቡቃያ ሁሉ በረዶውም የተወውን በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በሉ ለምለም ነገር ዛፍም የምድር ሣርም በግብፅ አገር ሁሉ አልቀረም።

15 For they covered the face of the whole earth, so that the land was darkened; and they did eat every herb of the land, and all the fruit of the trees which the hail had left: and there remained not any green thing in the trees, or in the herbs of the field, through all the land of Egypt.

16 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ

16 Then Pharaoh called for Moses and Aaron in haste; and he said, I have sinned against the Lord your God, and against you.

17 አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው።

17 Now therefore forgive, I pray thee, my sin only this once, and intreat the Lord your God, that he may take away from me this death only.

18 ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመነ።

18 And he went out from Pharaoh, and intreated the Lord.

19 እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፥ አንበጣዎችንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም።

19 And the Lord turned a mighty strong west wind, which took away the locusts, and cast them into the Red sea; there remained not one locust in all the coasts of Egypt.

20 እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም።

20 But the Lord hardened Pharaoh’s heart, so that he would not let the children of Israel go.

21 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፥ በግብፅም አገር ላይ ሰው የሚዳስሰው ፅኑ ጨለማ ይሁን አለው።

21 And the Lord said unto Moses, Stretch out thine hand toward heaven, that there may be darkness over the land of Egypt, even darkness which may be felt.

22 ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፥ በግብፅም አገር ሁሉ ላይ ፅኑ ጨለማ ሦስት ቀን ሆነ

22 And Moses stretched forth his hand toward heaven; and there was a thick darkness in all the land of Egypt three days:

23 ማንም ወንድሙን አላየም፥ ሦስት ቀንም ሙሉ ከስፍራው ማንም አልተነሣም ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።

23 They saw not one another, neither rose any from his place for three days: but all the children of Israel had light in their dwellings.

24 ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ። ሂዱ፥ እግዚአብሔርን አገልግሉ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ ልጆቻችሁ ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሂዱ አለው።

24 And Pharaoh called unto Moses, and said, Go ye, serve the Lord; only let your flocks and your herds be stayed: let your little ones also go with you.

25 ሙሴም፦ አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ።

25 And Moses said, Thou must give us also sacrifices and burnt offerings, that we may sacrifice unto the Lord our God.

26 አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፥ አንድ ሰኮናም አይቀርም አምላካችን የምናገለግለው ምን እንደሆነ ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም አለ።

26 Our cattle also shall go with us; there shall not an hoof be left behind; for thereof must we take to serve the Lord our God; and we know not with what we must serve the Lord, until we come thither.

27 እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና፥ ሊለቅቃቸውም አልወደደም።

27 But the Lord hardened Pharaoh’s heart, and he would not let them go.

28 ፈርዖንም። ከእኔ ዘንድ ሂድ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ አለው።

28 And Pharaoh said unto him, Get thee from me, take heed to thyself, see my face no more; for in that day thou seest my face thou shalt die.

29 ሙሴም፦ እንደ ተናገርህ ይሁን ፊትህን እንደ ገና አላይም አለ።

29 And Moses said, Thou hast spoken well, I will see thy face again no more.