መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #27
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 27 |
Proverbs 27 |
1 ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ። |
1 Boast not thyself of to morrow; for thou knowest not what a day may bring forth. |
2 ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም። |
2 Let another man praise thee, and not thine own mouth; a stranger, and not thine own lips. |
3 ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም ሸክሙ ጽኑ ነው ከሁለቱ ግን የሰነፍ ቍጣ ይከብዳል። |
3 A stone is heavy, and the sand weighty; but a fool’s wrath is heavier than them both. |
4 ቍጣ ምሕረት የሌለው ነው፥ መዓትም እንደ ጎርፍ ነው በቅንዓት ፊት ግን ማን ይቆማል? |
4 Wrath is cruel, and anger is outrageous; but who is able to stand before envy? |
5 የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል። |
5 Open rebuke is better than secret love. |
6 የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው። |
6 Faithful are the wounds of a friend; but the kisses of an enemy are deceitful. |
7 የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል። |
7 The full soul loatheth an honeycomb; but to the hungry soul every bitter thing is sweet. |
8 ስፍራውን የሚተው ሰው ቤቱን ትቶ እንደሚበርር ወፍ ነው። |
8 As a bird that wandereth from her nest, so is a man that wandereth from his place. |
9 ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ እንዲሁ ነፍስ በወዳጁ ምክር ደስ ይላታል። |
9 Ointment and perfume rejoice the heart: so doth the sweetness of a man’s friend by hearty counsel. |
10 ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል። |
10 Thine own friend, and thy father’s friend, forsake not; neither go into thy brother’s house in the day of thy calamity: for better is a neighbour that is near than a brother far off. |
11 ልጄ ሆይ፥ ጠቢብ ሁን፥ ልቤንም ደስ አሰኘው፥ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ። |
11 My son, be wise, and make my heart glad, that I may answer him that reproacheth me. |
12 ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ። |
12 A prudent man foreseeth the evil, and hideth himself; but the simple pass on, and are punished. |
13 ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው። |
13 Take his garment that is surety for a stranger, and take a pledge of him for a strange woman. |
14 ባልንጀራውን በታላቅ ቃል ማለዳ የሚባርክ ሰው እንደሚራገም ያህል ነው። |
14 He that blesseth his friend with a loud voice, rising early in the morning, it shall be counted a curse to him. |
15 በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው |
15 A continual dropping in a very rainy day and a contentious woman are alike. |
16 እርስዋንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው። |
16 Whosoever hideth her hideth the wind, and the ointment of his right hand, which bewrayeth itself. |
17 ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል። |
17 Iron sharpeneth iron; so a man sharpeneth the countenance of his friend. |
18 በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል። |
18 Whoso keepeth the fig tree shall eat the fruit thereof: so he that waiteth on his master shall be honoured. |
19 ፊት በውኃ ላይ ለፊት እንደሚታይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል። |
19 As in water face answereth to face, so the heart of man to man. |
20 ሲኦልና ጥፋት እንዳይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዓይን አይጠግብም። |
20 Hell and destruction are never full; so the eyes of man are never satisfied. |
21 ብር በከውር ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል ሰውም በሚያመሰገኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል። |
21 As the fining pot for silver, and the furnace for gold; so is a man to his praise. |
22 ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም። |
22 Though thou shouldest bray a fool in a mortar among wheat with a pestle, yet will not his foolishness depart from him. |
23 የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር |
23 Be thou diligent to know the state of thy flocks, and look well to thy herds. |
24 ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። |
24 For riches are not for ever: and doth the crown endure to every generation? |
25 ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥ |
25 The hay appeareth, and the tender grass sheweth itself, and herbs of the mountains are gathered. |
26 በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ። |
26 The lambs are for thy clothing, and the goats are the price of the field. |
27 ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል። |
27 And thou shalt have goats’ milk enough for thy food, for the food of thy household, and for the maintenance for thy maidens. |