ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #21
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 21 |
Genesis 21 |
1 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሣራን አሰበ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ለሣራ አደረገላት። |
1 And the Lord visited Sarah as he had said, and the Lord did unto Sarah as he had spoken. |
2 ሣራም ፀነሰች፥ እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን ወለደችለት። |
2 For Sarah conceived, and bare Abraham a son in his old age, at the set time of which God had spoken to him. |
3 አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው። |
3 And Abraham called the name of his son that was born unto him, whom Sarah bare to him, Isaac. |
4 አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛ ቀን ገረዘው። |
4 And Abraham circumcised his son Isaac being eight days old, as God had commanded him. |
5 አብርሃምም ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ የመቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። |
5 And Abraham was an hundred years old, when his son Isaac was born unto him. |
6 ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች። |
6 And Sarah said, God hath made me to laugh, so that all that hear will laugh with me. |
7 ደግሞም፦ ሣራ ልጆችን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው? በእርጅናው ልጅን ወልጄለታለሁና አለች። |
7 And she said, Who would have said unto Abraham, that Sarah should have given children suck? for I have born him a son in his old age. |
8 ሕፃኑም አደገ፥ ጡትንም ከመጥባት ተቋረጠ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ። |
8 And the child grew, and was weaned: and Abraham made a great feast the same day that Isaac was weaned. |
9 ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ሲስቅ አየችው። |
9 And Sarah saw the son of Hagar the Egyptian, which she had born unto Abraham, mocking. |
10 አብርሃምንም፦ ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና አለችው። |
10 Wherefore she said unto Abraham, Cast out this bondwoman and her son: for the son of this bondwoman shall not be heir with my son, even with Isaac. |
11 ይህም ነገር በአብርሃም ዘንድ ስለ ልጁ እጅግ ችግር ሆነበት። |
11 And the thing was very grievous in Abraham’s sight because of his son. |
12 እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። |
12 And God said unto Abraham, Let it not be grievous in thy sight because of the lad, and because of thy bondwoman; in all that Sarah hath said unto thee, hearken unto her voice; for in Isaac shall thy seed be called. |
13 የባሪያይቱን ልጅ ደግሞ ሕዝብ አደርገዋለሁ፥ ዘርህ ነውና። |
13 And also of the son of the bondwoman will I make a nation, because he is thy seed. |
14 አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት እርስዋም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች። |
14 And Abraham rose up early in the morning, and took bread, and a bottle of water, and gave it unto Hagar, putting it on her shoulder, and the child, and sent her away: and she departed, and wandered in the wilderness of Beer–sheba. |
15 ውኃውም ከአቁማዳው አለቀ ብላቴናውንም ከአንድ ቍጥቋጦ በታች ጣለችው |
15 And the water was spent in the bottle, and she cast the child under one of the shrubs. |
16 እርስዋም ሄደች፦ ብላቴናው ሲሞት አልየው ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ ተቀመጠች። ፊት ለፊትም ተቀመጠች፥ ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች። |
16 And she went, and sat her down over against him a good way off, as it were a bowshot: for she said, Let me not see the death of the child. And she sat over against him, and lift up her voice, and wept. |
17 እግዚአብሔርም የብላቴናውን ድምፅ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፦ አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የብላቴናውን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ። |
17 And God heard the voice of the lad; and the angel of God called to Hagar out of heaven, and said unto her, What aileth thee, Hagar? fear not; for God hath heard the voice of the lad where he is. |
18 ተነሺ፥ ብላቴናውንም አንሺ፥ እጅሽንም በእርሱ አጽኚው ትልቅ ሕዝብ አደርገዋለሁና። |
18 Arise, lift up the lad, and hold him in thine hand; for I will make him a great nation. |
19 እግዚአብሔርም ዓይንዋን ከፈተላት፥ የውኃ ጕድጓድንም አየች ሄዳም አቁማዳውን በውኃ ሞላች፥ ብላቴናውንም አጠጣች። |
19 And God opened her eyes, and she saw a well of water; and she went, and filled the bottle with water, and gave the lad drink. |
20 እግዚአብሔርም ከብላቴናው ጋር ነበረ አደገም፥ በምድረ በዳም ተቀመጠ፥ ቀስተኛም ሆነ። |
20 And God was with the lad; and he grew, and dwelt in the wilderness, and became an archer. |
21 በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ እናቱም ከምድረ ግብፅ ሚስት ወሰደችለት። |
21 And he dwelt in the wilderness of Paran: and his mother took him a wife out of the land of Egypt. |
22 በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው። በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው |
22 And it came to pass at that time, that Abimelech and Phichol the chief captain of his host spake unto Abraham, saying, God is with thee in all that thou doest: |
23 አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ። |
23 Now therefore swear unto me here by God that thou wilt not deal falsely with me, nor with my son, nor with my son’s son: but according to the kindness that I have done unto thee, thou shalt do unto me, and to the land wherein thou hast sojourned. |
24 አብርሃምም፦ እኔ እምላለሁ አለ። |
24 And Abraham said, I will swear. |
25 አቢሜሌክንም ባሪያዎቹ በነጠቁት በውኃ ጕድጓድ ምክንያት አብርሃም ወቀሰው። |
25 And Abraham reproved Abimelech because of a well of water, which Abimelech’s servants had violently taken away. |
26 አቢሜሌክም አለ፦ ይህን ነገር ያደረገውን አላወቅሁም አንተም ደግሞ ምንም አልነገርኸኝም፥ እኔም ከዛሬ በቀር አልሰማሁም። |
26 And Abimelech said, I wot not who hath done this thing: neither didst thou tell me, neither yet heard I of it, but to day. |
27 አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ። |
27 And Abraham took sheep and oxen, and gave them unto Abimelech; and both of them made a covenant. |
28 አብርሃምም ሰባት ቄቦች በጎችን ለብቻቸው አቆመ። |
28 And Abraham set seven ewe lambs of the flock by themselves. |
29 አቢሜሌክም አብርሃምን፦ ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚህ ሰባት ቄቦች በጎች ምንድር ናቸው? አለው። |
29 And Abimelech said unto Abraham, What mean these seven ewe lambs which thou hast set by themselves? |
30 እርሱም፦ እኔ ይህችን የውኃ ጕድጓድ እንደቆፈርሁ ምስክር ይሆንልኝ ዘንድ እነዚህን ሰባት ቄቦች በጎች ከእጄ ትወስዳለህ አለው። |
30 And he said, For these seven ewe lambs shalt thou take of my hand, that they may be a witness unto me, that I have digged this well. |
31 ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው ከዚያ ሁለቱ ተማምለዋልና። |
31 Wherefore he called that place Beer–sheba; because there they sware both of them. |
32 በቤርሳቤህም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ። |
32 Thus they made a covenant at Beer–sheba: then Abimelech rose up, and Phichol the chief captain of his host, and they returned into the land of the Philistines. |
33 አብርሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍን ተከለ በዚያም የዘላለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። |
33 And Abraham planted a grove in Beer–sheba, and called there on the name of the Lord, the everlasting God. |
34 አብርሃምም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀመጠ። |
34 And Abraham sojourned in the Philistines’ land many days. |