መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #73
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 73 |
Psalm 73 |
1 ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው። |
1 Truly God is good to Israel, even to such as are of a clean heart. |
2 እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ። |
2 But as for me, my feet were almost gone; my steps had well nigh slipped. |
3 የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና። |
3 For I was envious at the foolish, when I saw the prosperity of the wicked. |
4 ለሞታቸው መጣጣር የለውምና ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና። |
4 For there are no bands in their death: but their strength is firm. |
5 እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም። |
5 They are not in trouble as other men; neither are they plagued like other men. |
6 ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት። |
6 Therefore pride compasseth them about as a chain; violence covereth them as a garment. |
7 ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ። |
7 Their eyes stand out with fatness: they have more than heart could wish. |
8 አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ። |
8 They are corrupt, and speak wickedly concerning oppression: they speak loftily. |
9 አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ። |
9 They set their mouth against the heavens, and their tongue walketh through the earth. |
10 ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል |
10 Therefore his people return hither: and waters of a full cup are wrung out to them. |
11 እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ። |
11 And they say, How doth God know? and is there knowledge in the most High? |
12 እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ። |
12 Behold, these are the ungodly, who prosper in the world; they increase in riches. |
13 እንዲህም አልሁ። በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ። |
13 Verily I have cleansed my heart in vain, and washed my hands in innocency. |
14 ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው። |
14 For all the day long have I been plagued, and chastened every morning. |
15 እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር። |
15 If I say, I will speak thus; behold, I should offend against the generation of thy children. |
16 አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ። |
16 When I thought to know this, it was too painful for me; |
17 ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ። |
17 Until I went into the sanctuary of God; then understood I their end. |
18 በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው። |
18 Surely thou didst set them in slippery places: thou castedst them down into destruction. |
19 እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኃጢአታቸውም ጠፉ። |
19 How are they brought into desolation, as in a moment! they are utterly consumed with terrors. |
20 ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ። |
20 As a dream when one awaketh; so, O Lord, when thou awakest, thou shalt despise their image. |
21 ልቤ ነድዶአልና፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና |
21 Thus my heart was grieved, and I was pricked in my reins. |
22 እኔ የተናቅሁ ነኝ አላውቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ። |
22 So foolish was I, and ignorant: I was as a beast before thee. |
23 እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ። |
23 Nevertheless I am continually with thee: thou hast holden me by my right hand. |
24 በአንተ ምክር መራኸኝ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ። |
24 Thou shalt guide me with thy counsel, and afterward receive me to glory. |
25 በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? |
25 Whom have I in heaven but thee? and there is none upon earth that I desire beside thee. |
26 የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው። |
26 My flesh and my heart faileth: but God is the strength of my heart, and my portion for ever. |
27 እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው። |
27 For, lo, they that are far from thee shall perish: thou hast destroyed all them that go a whoring from thee. |
28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ። |
28 But it is good for me to draw near to God: I have put my trust in the Lord God, that I may declare all thy works. |