መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #72
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 72

Psalm 72

1 አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥

1 Give the king thy judgments, O God, and thy righteousness unto the king’s son.

2 ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።

2 He shall judge thy people with righteousness, and thy poor with judgment.

3 ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።

3 The mountains shall bring peace to the people, and the little hills, by righteousness.

4 ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ትፈርዳለህ የድሆችንም ልጆች ታድናለህ ክፉውንም ታዋርደዋለህ።

4 He shall judge the poor of the people, he shall save the children of the needy, and shall break in pieces the oppressor.

5 ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኖራል።

5 They shall fear thee as long as the sun and moon endure, throughout all generations.

6 እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል።

6 He shall come down like rain upon the mown grass: as showers that water the earth.

7 በዘመኑም ጽድቅ ያብባል፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።

7 In his days shall the righteous flourish; and abundance of peace so long as the moon endureth.

8 ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል።

8 He shall have dominion also from sea to sea, and from the river unto the ends of the earth.

9 በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።

9 They that dwell in the wilderness shall bow before him; and his enemies shall lick the dust.

10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።

10 The kings of Tarshish and of the isles shall bring presents: the kings of Sheba and Seba shall offer gifts.

11 ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።

11 Yea, all kings shall fall down before him: all nations shall serve him.

12 ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።

12 For he shall deliver the needy when he crieth; the poor also, and him that hath no helper.

13 ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።

13 He shall spare the poor and needy, and shall save the souls of the needy.

14 ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል ስማቸው በፊቱ ክቡር ነው።

14 He shall redeem their soul from deceit and violence: and precious shall their blood be in his sight.

15 እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።

15 And he shall live, and to him shall be given of the gold of Sheba: prayer also shall be made for him continually; and daily shall he be praised.

16 በምድር ውስጥ በተራሮች ላይ መጠጊያ ይሆናል ፍሬውም ከሊባኖስ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል እንደ ምድር ሣር በከተማ ይበቅላል።

16 There shall be an handful of corn in the earth upon the top of the mountains; the fruit thereof shall shake like Lebanon: and they of the city shall flourish like grass of the earth.

17 ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉም አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል።

17 His name shall endure for ever: his name shall be continued as long as the sun: and men shall be blessed in him: all nations shall call him blessed.

18 ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።

18 Blessed be the Lord God, the God of Israel, who only doeth wondrous things.

19 የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘላለም ይባረክ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን ይሁን።

19 And blessed be his glorious name for ever: and let the whole earth be filled with his glory; Amen, and Amen.

20 የእሴይ ልጅ የዳዊት መዝሙር ተፈጸመ።

20 The prayers of David the son of Jesse are ended.