መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #11
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 11

Ps 11

1 በእግዚአብሔር ታመንሁ ነፍሴን። እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሉአታላችሁ?

1 In the Lord put I my trust: how say ye to my soul, Flee as a bird to your mountain?

2 ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።

2 For, lo, the wicked bend their bow, they make ready their arrow upon the string, that they may privily shoot at the upright in heart.

3 አንተ የሠራኸውን እነሆ እነርሱ አፍርሰዋልና ጻድቅ ግን ምን አደረገ?

3 If the foundations be destroyed, what can the righteous do?

4 እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው ዓይኖቹ ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

4 The Lord is in his holy temple, the Lord’s throne is in heaven: his eyes behold, his eyelids try, the children of men.

5 እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።

5 The Lord trieth the righteous: but the wicked and him that loveth violence his soul hateth.

6 ወጥመድ በኅጥኣን ላይ ያዘንባል እሳትና ዲን ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።

6 Upon the wicked he shall rain snares, fire and brimstone, and an horrible tempest: this shall be the portion of their cup.

7 እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።

7 For the righteous Lord loveth righteousness; his countenance doth behold the upright.