መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #12
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 12

Ps 12

1 አቤቱ፥ አድነኝ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።

1 Help, Lord; for the godly man ceaseth; for the faithful fail from among the children of men.

2 እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።

2 They speak vanity every one with his neighbour: with flattering lips and with a double heart do they speak.

3 የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ

3 The Lord shall cut off all flattering lips, and the tongue that speaketh proud things:

4 ምላሳችንን እናበረታለን ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።

4 Who have said, With our tongue will we prevail; our lips are our own: who is lord over us?

5 ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር፦ አሁን እነሣለሁ ይላል መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።

5 For the oppression of the poor, for the sighing of the needy, now will I arise, saith the Lord; I will set him in safety from him that puffeth at him.

6 በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።

6 The words of the Lord are pure words: as silver tried in a furnace of earth, purified seven times.

7 አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

7 Thou shalt keep them, O Lord, thou shalt preserve them from this generation for ever.

8 በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።

8 The wicked walk on every side, when the vilest men are exalted.