መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #9
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 9 |
Ps 9 |
1 አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ። |
1 I will praise thee, O Lord, with my whole heart; I will shew forth all thy marvellous works. |
2 በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ። |
2 I will be glad and rejoice in thee: I will sing praise to thy name, O thou most High. |
3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፥ ይሰናከላሉ ከፊትህም ይጠፋሉ። |
3 When mine enemies are turned back, they shall fall and perish at thy presence. |
4 ፍርዴንና በቀሌን አድርገህልኛልና ጽድቅን እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ። |
4 For thou hast maintained my right and my cause; thou satest in the throne judging right. |
5 አሕዛብን ገሠጽህ፥ ዝንጉዎችንም አጠፋህ፥ ስማቸውንም ለዘላለም ደመሰስህ። |
5 Thou hast rebuked the heathen, thou hast destroyed the wicked, thou hast put out their name for ever and ever. |
6 ጠላቶች በጦር ለዘላለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውም በአንድነት ጠፋ። |
6 O thou enemy, destructions are come to a perpetual end: and thou hast destroyed cities; their memorial is perished with them. |
7 እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ |
7 But the Lord shall endure for ever: he hath prepared his throne for judgment. |
8 እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል። |
8 And he shall judge the world in righteousness, he shall minister judgment to the people in uprightness. |
9 እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው። |
9 The Lord also will be a refuge for the oppressed, a refuge in times of trouble. |
10 ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። |
10 And they that know thy name will put their trust in thee: for thou, Lord, hast not forsaken them that seek thee. |
11 በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ |
11 Sing praises to the Lord, which dwelleth in Zion: declare among the people his doings. |
12 ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና። |
12 When he maketh inquisition for blood, he remembereth them: he forgetteth not the cry of the humble. |
13 አቤቱ፥ እዘንልኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ |
13 Have mercy upon me, O Lord; consider my trouble which I suffer of them that hate me, thou that liftest me up from the gates of death: |
14 ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል። |
14 That I may shew forth all thy praise in the gates of the daughter of Zion: I will rejoice in thy salvation. |
15 አሕዛብ በሠሩት ጕድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች። |
15 The heathen are sunk down in the pit that they made: in the net which they hid is their own foot taken. |
16 እግዚአብሔር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው ኃጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ። |
16 The Lord is known by the judgment which he executeth: the wicked is snared in the work of his own hands. Higgaion. Selah. |
17 ኃጢአተኞች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ሁሉ። |
17 The wicked shall be turned into hell, and all the nations that forget God. |
18 ድሀ ለዘላለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘላለም አይጠፋም። |
18 For the needy shall not alway be forgotten: the expectation of the poor shall not perish for ever. |
19 አቤቱ፥ ተነሥ ሰውም አይበርታ፥ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው። |
19 Arise, O Lord; let not man prevail: let the heathen be judged in thy sight. |
20 አቤቱ፥ ፍርሃትን በላያቸው ጫንባቸው አሕዛብ ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ። |
20 Put them in fear, O Lord: that the nations may know themselves to be but men. Selah. |