መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #39
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 39 |
Ps 39 |
1 በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ። |
1 I said, I will take heed to my ways, that I sin not with my tongue: I will keep my mouth with a bridle, while the wicked is before me. |
2 ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፥ ቍስሌም ታደሰብኝ። |
2 I was dumb with silence, I held my peace, even from good; and my sorrow was stirred. |
3 ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ፥ በአንደበቴም ተናገርሁ። |
3 My heart was hot within me, while I was musing the fire burned: then spake I with my tongue, |
4 አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ። |
4 Lord, make me to know mine end, and the measure of my days, what it is; that I may know how frail I am. |
5 እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሕያው የሆነ ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ብቻ ነው። |
5 Behold, thou hast made my days as an handbreadth; and mine age is as nothing before thee: verily every man at his best state is altogether vanity. Selah. |
6 በከንቱ ይታወካል እንጂ በእውነት ሰው እንደ ጣላ ይመላለሳል ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም። |
6 Surely every man walketh in a vain shew: surely they are disquieted in vain: he heapeth up riches, and knoweth not who shall gather them. |
7 አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው። |
7 And now, Lord, what wait I for? my hope is in thee. |
8 ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፥ ለሰነፎችም ስድብ አታድርገኝ። |
8 Deliver me from all my transgressions: make me not the reproach of the foolish. |
9 አንተ ሠርተኸኛልና ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም። |
9 I was dumb, I opened not my mouth; because thou didst it. |
10 መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና። |
10 Remove thy stroke away from me: I am consumed by the blow of thine hand. |
11 በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ ነፍሱም እንደ ሸረሪት ድር ታልቃለች በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው። |
11 When thou with rebukes dost correct man for iniquity, thou makest his beauty to consume away like a moth: surely every man is vanity. Selah. |
12 አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም እንግዳ ነኝና። |
12 Hear my prayer, O Lord, and give ear unto my cry; hold not thy peace at my tears: for I am a stranger with thee, and a sojourner, as all my fathers were. |
13 ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ። |
13 O spare me, that I may recover strength, before I go hence, and be no more. |