መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #74
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 74 |
Psalm 74 |
1 አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ? |
1 O God, why hast thou cast us off for ever? why doth thine anger smoke against the sheep of thy pasture? |
2 አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ። |
2 Remember thy congregation, which thou hast purchased of old; the rod of thine inheritance, which thou hast redeemed; this mount Zion, wherein thou hast dwelt. |
3 ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ። |
3 Lift up thy feet unto the perpetual desolations; even all that the enemy hath done wickedly in the sanctuary. |
4 ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ። |
4 Thine enemies roar in the midst of thy congregations; they set up their ensigns for signs. |
5 እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ። |
5 A man was famous according as he had lifted up axes upon the thick trees. |
6 እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት። |
6 But now they break down the carved work thereof at once with axes and hammers. |
7 መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ። |
7 They have cast fire into thy sanctuary, they have defiled by casting down the dwelling place of thy name to the ground. |
8 አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ። |
8 They said in their hearts, Let us destroy them together: they have burned up all the synagogues of God in the land. |
9 ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም። |
9 We see not our signs: there is no more any prophet: neither is there among us any that knoweth how long. |
10 አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን? |
10 O God, how long shall the adversary reproach? shall the enemy blaspheme thy name for ever? |
11 ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ? |
11 Why withdrawest thou thy hand, even thy right hand? pluck it out of thy bosom. |
12 እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ። |
12 For God is my King of old, working salvation in the midst of the earth. |
13 አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ። |
13 Thou didst divide the sea by thy strength: thou brakest the heads of the dragons in the waters. |
14 አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው። |
14 Thou brakest the heads of leviathan in pieces, and gavest him to be meat to the people inhabiting the wilderness. |
15 አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ። |
15 Thou didst cleave the fountain and the flood: thou driedst up mighty rivers. |
16 ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ። |
16 The day is thine, the night also is thine: thou hast prepared the light and the sun. |
17 አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ። |
17 Thou hast set all the borders of the earth: thou hast made summer and winter. |
18 ይህን ፍጥረትህን አስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ፥ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ። |
18 Remember this, that the enemy hath reproached, O Lord, and that the foolish people have blasphemed thy name. |
19 የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ። |
19 O deliver not the soul of thy turtledove unto the multitude of the wicked: forget not the congregation of thy poor for ever. |
20 ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና። |
20 Have respect unto the covenant: for the dark places of the earth are full of the habitations of cruelty. |
21 ችግረኛ አፍሮ አይመለስ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ። |
21 O let not the oppressed return ashamed: let the poor and needy praise thy name. |
22 አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ። |
22 Arise, O God, plead thine own cause: remember how the foolish man reproacheth thee daily. |
23 የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይወጣል። |
23 Forget not the voice of thine enemies: the tumult of those that rise up against thee increaseth continually. |