ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #35
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 35

Exodus 35

1 ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ቃል ይህ ነው

1 And Moses gathered all the congregation of the children of Israel together, and said unto them, These are the words which the Lord hath commanded, that ye should do them.

2 ስድስት ቀን ሥራ ይደረጋል፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የዕረፍት ሰንበት የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል የሚሠራበትም ሁሉ ይገደል።

2 Six days shall work be done, but on the seventh day there shall be to you an holy day, a sabbath of rest to the Lord: whosoever doeth work therein shall be put to death.

3 በማደሪያዎቻችሁ ውስጥ በሰንበት ቀን እሳትን አታንድዱ።

3 Ye shall kindle no fire throughout your habitations upon the sabbath day.

4 ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ አላቸው። እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘው ነገር ይህ ነው

4 And Moses spake unto all the congregation of the children of Israel, saying, This is the thing which the Lord commanded, saying,

5 ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቍርባንን አቅርቡ የልብ ፈቃድ ያለው የእግዚአብሔርን ቍርባን ያምጣ ወርቅና ብርም ናስም

5 Take ye from among you an offering unto the Lord: whosoever is of a willing heart, let him bring it, an offering of the Lord; gold, and silver, and brass,

6 ሰማያዊም ሐምራዊም ቀይ ግምጃም፥ ጥሩ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም

6 And blue, and purple, and scarlet, and fine linen, and goats’ hair,

7 ቀይም የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣም ቁርበት፥ የግራርም እንጨት

7 And rams’ skins dyed red, and badgers’ skins, and shittim wood,

8 ለመብራትም ዘይት፥ ለቅብዓት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም

8 And oil for the light, and spices for anointing oil, and for the sweet incense,

9 መረግድ ለኤፉዱና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ ያምጣ።

9 And onyx stones, and stones to be set for the ephod, and for the breastplate.

10 በእናንተም ዘንድ ያሉ በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ።

10 And every wise hearted among you shall come, and make all that the Lord hath commanded;

11 ማደሪያውን፥ ድንኳኑንም መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም

11 The tabernacle, his tent, and his covering, his taches, and his boards, his bars, his pillars, and his sockets,

12 ታቦቱን መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም በእርሱም ፊት የሚሸፍነውን መጋረጃ

12 The ark, and the staves thereof, with the mercy seat, and the vail of the covering,

13 ገበታውን መሎጊያዎቹንም ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ኅብስት

13 The table, and his staves, and all his vessels, and the shewbread,

14 መብራት የሚያበሩበትን መቅረዙን ዕቃውንም፥ ቀንዲሉንም፥ የመብራቱንም ዘይት

14 The candlestick also for the light, and his furniture, and his lamps, with the oil for the light,

15 የዕጣኑን መሠዊያም መሎጊያዎቹንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ ለማደሪያውም ደጃፍ የሚሆን የደጃፉን መጋረጃ

15 And the incense altar, and his staves, and the anointing oil, and the sweet incense, and the hanging for the door at the entering in of the tabernacle,

16 ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም

16 The altar of burnt offering, with his brasen grate, his staves, and all his vessels, the laver and his foot,

17 የአደባባዩን መጋረጆች ምሰሶቹንም እግሮቻቸውንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ

17 The hangings of the court, his pillars, and their sockets, and the hanging for the door of the court,

18 የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች አውታሮቻቸውንም

18 The pins of the tabernacle, and the pins of the court, and their cords,

19 በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች።

19 The cloths of service, to do service in the holy place, the holy garments for Aaron the priest, and the garments of his sons, to minister in the priest’s office.

20 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ።

20 And all the congregation of the children of Israel departed from the presence of Moses.

21 ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሣሣው መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለመገናኛው ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ።

21 And they came, every one whose heart stirred him up, and every one whom his spirit made willing, and they brought the Lord’s offering to the work of the tabernacle of the congregation, and for all his service, and for the holy garments.

22 ወንዶችና ሴቶችም ልባቸው እንደ ፈቀደ ማርዳዎችን፥ ሎቲዎችንም፥ ቀለበቶችንም፥ ድሪዎችንም፥ የወርቅ ጌጦችንም ሁሉ አመጡ ሰዎችም ሁሉ የወርቅ ስጦታ ወደ እግዚአብሔር አቀረቡ።

22 And they came, both men and women, as many as were willing hearted, and brought bracelets, and earrings, and rings, and tablets, all jewels of gold: and every man that offered offered an offering of gold unto the Lord.

23 ሰማያዊም ሐምራዊም ቀይ ግምጃም፥ ጥሩ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበትም፥ የአቆስጣ ቁርበትም ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።

23 And every man, with whom was found blue, and purple, and scarlet, and fine linen, and goats’ hair, and red skins of rams, and badgers’ skins, brought them.

24 ስእለት የተሳለ ሁሉ የብርንም የናስንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ቍርባን አቀረበ የግራርም እንጨት ያለው ሁሉ ለማገልገያ ሥራ አመጣ።

24 Every one that did offer an offering of silver and brass brought the Lord’s offering: and every man, with whom was found shittim wood for any work of the service, brought it.

25 በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶችም በእጃቸው ፈተሉ፥ የፈተሉትንም ሰማያዊውን ሐምራዊውንም ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ አመጡ።

25 And all the women that were wise hearted did spin with their hands, and brought that which they had spun, both of blue, and of purple, and of scarlet, and of fine linen.

26 ልባቸውም በጥበብ ያስነሣቸው ሴቶች ሁሉ የፍየልን ጠጕር ፈተሉ።

26 And all the women whose heart stirred them up in wisdom spun goats’ hair.

27 አለቆችም መረግድን፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚገቡትንም ፈርጦችን፥

27 And the rulers brought onyx stones, and stones to be set, for the ephod, and for the breastplate;

28 ለመብራትም ለቅብዓት ዘይትም ለጣፋጭ ዕጣንም ሽቱንና ዘይትን አመጡ።

28 And spice, and oil for the light, and for the anointing oil, and for the sweet incense.

29 ከእስራኤል ልጆችም ያመጡ ዘንድ ልባቸው ያስነሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግዚአብሔር ላዘዘው ሥራ ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጦታ በፈቃዳቸው አመጡ።

29 The children of Israel brought a willing offering unto the Lord, every man and woman, whose heart made them willing to bring for all manner of work, which the Lord had commanded to be made by the hand of Moses.

30 ሙሴም የእስራኤልን ልጆች አላቸው። እዩ፥ እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው።

30 And Moses said unto the children of Israel, See, the Lord hath called by name Bezaleel the son of Uri, the son of Hur, of the tribe of Judah;

31 በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞላበት

31 And he hath filled him with the spirit of God, in wisdom, in understanding, and in knowledge, and in all manner of workmanship;

32 የጥበብን ሥራ ያስተውል ዘንድ፥ በወርቅና በብር በናስም ይሠራ ዘንድ፥

32 And to devise curious works, to work in gold, and in silver, and in brass,

33 በፈርጥ የሚሆነውን የዕንቍ ድንጋይ ይቀርጽ ዘንድ፥ እንጨቱንም ይጠርብ ዘንድ፥ የብልሃት ሥራውንም ሁሉ ይሠራ ዘንድ።

33 And in the cutting of stones, to set them, and in carving of wood, to make any manner of cunning work.

34 እርሱና የዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ያስተምሩ ዘንድ በልባቸው አሳደረባቸው።

34 And he hath put in his heart that he may teach, both he, and Aholiab, the son of Ahisamach, of the tribe of Dan.

35 በአንጥረኛ፥ በብልህ ሠራተኛም፥ በሰማያዊና በሐምራዊ በቀይም ግምጃ በጥሩ በፍታም በሚሠራ ጠላፊ፥ በሸማኔም ሥራ የሚሠራውን፥ ማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ።

35 Them hath he filled with wisdom of heart, to work all manner of work, of the engraver, and of the cunning workman, and of the embroiderer, in blue, and in purple, in scarlet, and in fine linen, and of the weaver, even of them that do any work, and of those that devise cunning work.