ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #36
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 36

Exodus 36

1 ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ባስልኤልና ኤልያብ በልባቸው ጥበበኞችም ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ነገር ሁሉ አደረጉ።

1 Then wrought Bezaleel and Aholiab, and every wise hearted man, in whom the Lord put wisdom and understanding to know how to work all manner of work for the service of the sanctuary, according to all that the Lord had commanded.

2 ሙሴም ባስልኤልንና ኤልያብን፥ እግዚአብሔርም በልቡ ጥበብን ያደረገለትን በልብ ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውንም ለመሥራት ይቀርብ ዘንድ ልቡ ያስነሣውን ሁሉ ጠራቸው።

2 And Moses called Bezaleel and Aholiab, and every wise hearted man, in whose heart the Lord had put wisdom, even every one whose heart stirred him up to come unto the work to do it:

3 እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።

3 And they received of Moses all the offering, which the children of Israel had brought for the work of the service of the sanctuary, to make it withal. And they brought yet unto him free offerings every morning.

4 የመቅደሱንም ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ የሚያደርጉትን ሥራ ትተው መጡ፥

4 And all the wise men, that wrought all the work of the sanctuary, came every man from his work which they made;

5 እነርሱም ሙሴን፦ እግዚአብሔር ለማገልገያ ሥራ ይደረግ ዘንድ ላዘዘው ከሚበቃ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ሕዝቡ አመጡ ብለው ተናገሩት።

5 And they spake unto Moses, saying, The people bring much more than enough for the service of the work, which the Lord commanded to make.

6-7 ያመጡትም ነገር ሥራን ሁሉ ለመፈጸም በቅቶ ገና ይተርፍ ስለ ነበረ ሙሴ አዘዘና። ወንድ ወይም ሴት ለመቅደስ ስጦታ ከዚህ የበለጠ የሚያመጣ አይኑር ብሎ በሰፈሩ ውስጥ አሳወጀ። ሕዝቡም እንዳያመጡ ተከለከሉ።

6 And Moses gave commandment, and they caused it to be proclaimed throughout the camp, saying, Let neither man nor woman make any more work for the offering of the sanctuary. So the people were restrained from bringing.
7 For the stuff they had was sufficient for all the work to make it, and too much.

8 በእነርሱም ዘንድ ያሉት ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ማደሪያውን ከአሥር መጋረጆች ሠሩ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ሠሩ በእነርሱም ላይ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው።

8 And every wise hearted man among them that wrought the work of the tabernacle made ten curtains of fine twined linen, and blue, and purple, and scarlet: with cherubims of cunning work made he them.

9 የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሀያ ስምንት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ የመጋረጆቹ ሁሉ ልክ ትክክል ነበረ።

9 The length of one curtain was twenty and eight cubits, and the breadth of one curtain four cubits: the curtains were all of one size.

10 አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አጋጠሙ አምስቱንም መጋረጆች እንዲሁ እርስ በርሳቸው አጋጠሙ።

10 And he coupled the five curtains one unto another: and the other five curtains he coupled one unto another.

11 ከሚጋጠሙትም መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አደረጉ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አደረጉ።

11 And he made loops of blue on the edge of one curtain from the selvedge in the coupling: likewise he made in the uttermost side of another curtain, in the coupling of the second.

12 አምሳ ቀለበቶችንችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ።

12 Fifty loops made he in one curtain, and fifty loops made he in the edge of the curtain which was in the coupling of the second: the loops held one curtain to another.

13 አምሳም የወርቅ መያዣዎች ሠሩ መጋረጆችንም እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጠሙአቸው አንድ ማደሪያም ሆነ።

13 And he made fifty taches of gold, and coupled the curtains one unto another with the taches: so it became one tabernacle.

14 ከማደሪያውም በላይ ለድንኳን የሚሆኑ መጋረጆችን ከፍየል ጠጕር አደረጉ አሥራ አንድ መጋረጆች አደረጉ።

14 And he made curtains of goats’ hair for the tent over the tabernacle: eleven curtains he made them.

15 እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ የአሥራ አንዱም መጋረጆች መጠናቸው ትክክል ነበረ።

15 The length of one curtain was thirty cubits, and four cubits was the breadth of one curtain: the eleven curtains were of one size.

16 አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አንድ አድርገው፥ ስድስቱንም መጋረጆች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው።

16 And he coupled five curtains by themselves, and six curtains by themselves.

17 ከተጋጠሙትም መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረጉ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረጉ።

17 And he made fifty loops upon the uttermost edge of the curtain in the coupling, and fifty loops made he upon the edge of the curtain which coupleth the second.

18 ድንኳኑም አንድ እንዲሆን ያጋጥሙት ዘንድ አምሳ የናስ መያዣዎችን ሠሩ።

18 And he made fifty taches of brass to couple the tent together, that it might be one.
19 And he made a covering for the tent of rams’ skins dyed red, and a covering of badgers’ skins above that.

20 ለማደሪያውም ከግራር እንጨት የሚቆሙትን ሳንቆች አደረጉ።

20 And he made boards for the tabernacle of shittim wood, standing up.

21 የሳንቃው ሁሉ ርዝመቱ አሥር ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።

21 The length of a board was ten cubits, and the breadth of a board one cubit and a half.

22 ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ነበሩ ለማደሪያው ሳንቆች ሁሉ እንዲሁ አደረጉ።

22 One board had two tenons, equally distant one from another: thus did he make for all the boards of the tabernacle.

23 ለማደሪያውም በደቡብ ወገን ሀያ ሳንቆችን አደረጉ

23 And he made boards for the tabernacle; twenty boards for the south side southward:

24 ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮች አደረጉ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ነበሩ።

24 And forty sockets of silver he made under the twenty boards; two sockets under one board for his two tenons, and two sockets under another board for his two tenons.

25 ለማደሪያው ለሁለተኛው ወገን በሰሜን በኩል ሀያ ሳንቆች አደረጉ

25 And for the other side of the tabernacle, which is toward the north corner, he made twenty boards,

26 ለእነርሱም አርባ የብር እግሮች፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች አደረጉ።

26 And their forty sockets of silver; two sockets under one board, and two sockets under another board.

27 ለማደሪያውም በምዕራቡ ወገበስተ ኋላ ስድስት ሳንቆች አደረጉ።

27 And for the sides of the tabernacle westward he made six boards.

28 ለማደሪያውም ለሁለቱ ማዕዘን በስተ ኋላ ሁለት ሳንቆች አደረጉ።

28 And two boards made he for the corners of the tabernacle in the two sides.

29 ከታችም እስከ ላይ እስከ አንደኛው ቀለበት ድረስ አንድ ሳንቃ ድርብ ነበረ ለሁለቱም ማዕዘን እንዲሁ ሁለት ነበሩ።

29 And they were coupled beneath, and coupled together at the head thereof, to one ring: thus he did to both of them in both the corners.

30 ስምንት ሳንቆችና አሥራ ስድስቱ የብር እግሮቻቸው፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት ሁለት እግሮች ነበሩ።

30 And there were eight boards; and their sockets were sixteen sockets of silver, under every board two sockets.

31 ከግራርም እንጨት በማደሪያው በአንደኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥

31 And he made bars of shittim wood; five for the boards of the one side of the tabernacle,

32 በማደሪያውም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥ ከማደሪያውም በስተ ኋላ በምዕራቡ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች አደረጉ።

32 And five bars for the boards of the other side of the tabernacle, and five bars for the boards of the tabernacle for the sides westward.

33 መካከለኛውንም መወርወሪያ በሳንቆቹ መካከል ከዳር እስከ ዳር አሳለፉ።

33 And he made the middle bar to shoot through the boards from the one end to the other.

34 ሳንቆቹንም በወርቅ ለበጡአቸው ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያ ቤት እንዲሆኑላቸው ከወርቅ አደረጉ መወርወሪያዎቹንም በወርቅ ለበጡአቸው።

34 And he overlaid the boards with gold, and made their rings of gold to be places for the bars, and overlaid the bars with gold.

35 መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረጉ።

35 And he made a vail of blue, and purple, and scarlet, and fine twined linen: with cherubims made he it of cunning work.

36 ከግራርም እንጨት አራት ምሰሶች አደረጉለት፥ በወርቅም ለበጡአቸው ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች አደረጉ።

36 And he made thereunto four pillars of shittim wood, and overlaid them with gold: their hooks were of gold; and he cast for them four sockets of silver.

37 ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊና ከሐምራዊ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አደረጉ

37 And he made an hanging for the tabernacle door of blue, and purple, and scarlet, and fine twined linen, of needlework;

38 አምስቱንም ምሰሶች፥ ኩላቦቻቸውንም አደረጉ ጕልላቶቻቸውንና ዘንጎቻቸውንም በወርቅ ለበጡአቸው አምስቱም እግሮቻቸው የናስ ነበሩ።

38 And the five pillars of it with their hooks: and he overlaid their chapiters and their fillets with gold: but their five sockets were of brass.