መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #86
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 86 |
Psalm 86 |
1 አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ችግረኛና ምስኪን ነኝና። |
1 Bow down thine ear, O Lord, hear me: for I am poor and needy. |
2 ቅዱስ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ አምላኬ ሆይ፥ አንተን የታመነውን ባሪያህን አድነው። |
2 Preserve my soul; for I am holy: O thou my God, save thy servant that trusteth in thee. |
3 አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ማረኝ። |
3 Be merciful unto me, O Lord: for I cry unto thee daily. |
4 የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና። |
4 Rejoice the soul of thy servant: for unto thee, O Lord, do I lift up my soul. |
5 አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ምሕረትህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና። |
5 For thou, Lord, art good, and ready to forgive; and plenteous in mercy unto all them that call upon thee. |
6 አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ድምፅ ስማ። |
6 Give ear, O Lord, unto my prayer; and attend to the voice of my supplications. |
7 ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ። |
7 In the day of my trouble I will call upon thee: for thou wilt answer me. |
8 አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ እንደ ሥራህም ያለ የለም። |
8 Among the gods there is none like unto thee, O Lord; neither are there any works like unto thy works. |
9 ያደረግሃቸው አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፥ አቤቱ፥ በፊትህም ይሰግዳሉ፥ ስምህንም ያከብራሉ |
9 All nations whom thou hast made shall come and worship before thee, O Lord; and shall glorify thy name. |
10 አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና። |
10 For thou art great, and doest wondrous things: thou art God alone. |
11 አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል። |
11 Teach me thy way, O Lord; I will walk in thy truth: unite my heart to fear thy name. |
12 አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለዘላለምም ስምህን አከብራለሁ |
12 I will praise thee, O Lord my God, with all my heart: and I will glorify thy name for evermore. |
13 ምሕረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና። |
13 For great is thy mercy toward me: and thou hast delivered my soul from the lowest hell. |
14 አቤቱ፥ ዓመፀኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችንም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት በፊታቸውም አላደረጉህም። |
14 O God, the proud are risen against me, and the assemblies of violent men have sought after my soul; and have not set thee before them. |
15 አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ |
15 But thou, O Lord, art a God full of compassion, and gracious, longsuffering, and plenteous in mercy and truth. |
16 ወደ እኔ ተመልከት ማረኝም ለባሪያህ ኃይልህን ስጥ፥ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን። |
16 O turn unto me, and have mercy upon me; give thy strength unto thy servant, and save the son of thine handmaid. |
17 ምልክትንም ለመልካም ከእኔ ጋር አድርግ የሚጠሉኝ ይዩ ይፈሩም፥ አቤቱ፥ አንተ ረድተኸኛልና፥ አጽንተኸኛልምና። |
17 Shew me a token for good; that they which hate me may see it, and be ashamed: because thou, Lord, hast holpen me, and comforted me. |