መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #103
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 103 |
Psalm 103 |
1 ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። |
1 Bless the Lord, O my soul: and all that is within me, bless his holy name. |
2 ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ |
2 Bless the Lord, O my soul, and forget not all his benefits: |
3 ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ |
3 Who forgiveth all thine iniquities; who healeth all thy diseases; |
4 ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥ |
4 Who redeemeth thy life from destruction; who crowneth thee with lovingkindness and tender mercies; |
5 ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል። |
5 Who satisfieth thy mouth with good things; so that thy youth is renewed like the eagle’s. |
6 እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል። |
6 The Lord executeth righteousness and judgment for all that are oppressed. |
7 ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን። |
7 He made known his ways unto Moses, his acts unto the children of Israel. |
8 እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ። |
8 The Lord is merciful and gracious, slow to anger, and plenteous in mercy. |
9 ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም። |
9 He will not always chide: neither will he keep his anger for ever. |
10 እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም። |
10 He hath not dealt with us after our sins; nor rewarded us according to our iniquities. |
11 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ። |
11 For as the heaven is high above the earth, so great is his mercy toward them that fear him. |
12 ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ። |
12 As far as the east is from the west, so far hath he removed our transgressions from us. |
13 አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል |
13 Like as a father pitieth his children, so the Lord pitieth them that fear him. |
14 ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ። |
14 For he knoweth our frame; he remembereth that we are dust. |
15 ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል |
15 As for man, his days are as grass: as a flower of the field, so he flourisheth. |
16 ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥ ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና። |
16 For the wind passeth over it, and it is gone; and the place thereof shall know it no more. |
17 የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው |
17 But the mercy of the Lord is from everlasting to everlasting upon them that fear him, and his righteousness unto children’s children; |
18 ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ፥ ትእዛዙንም ያደርጉአት ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው። |
18 To such as keep his covenant, and to those that remember his commandments to do them. |
19 እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። |
19 The Lord hath prepared his throne in the heavens; and his kingdom ruleth over all. |
20 ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። |
20 Bless the Lord, ye his angels, that excel in strength, that do his commandments, hearkening unto the voice of his word. |
21 ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። |
21 Bless ye the Lord, all ye his hosts; ye ministers of his, that do his pleasure. |
22 ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ። |
22 Bless the Lord, all his works in all places of his dominion: bless the Lord, O my soul. |