መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #97
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 97

Psalm 97

1 እግዚአብሔር ነገሠ ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው።

1 The Lord reigneth; let the earth rejoice; let the multitude of isles be glad thereof.

2 ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

2 Clouds and darkness are round about him: righteousness and judgment are the habitation of his throne.

3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

3 A fire goeth before him, and burneth up his enemies round about.

4 መብረቆቹ ለዓለም አበሩ ምድር አየችና ተናወጠች።

4 His lightnings enlightened the world: the earth saw, and trembled.

5 ተራሮችም ከእግዚአብሔር ፊት፥ ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።

5 The hills melted like wax at the presence of the Lord, at the presence of the Lord of the whole earth.

6 ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።

6 The heavens declare his righteousness, and all the people see his glory.

7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።

7 Confounded be all they that serve graven images, that boast themselves of idols: worship him, all ye gods.

8 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው

8 Zion heard, and was glad; and the daughters of Judah rejoiced because of thy judgments, O Lord.

9 አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።

9 For thou, Lord, art high above all the earth: thou art exalted far above all gods.

10 እግዚአብሔርን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።

10 Ye that love the Lord, hate evil: he preserveth the souls of his saints; he delivereth them out of the hand of the wicked.

11 ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።

11 Light is sown for the righteous, and gladness for the upright in heart.

12 ጻድቃን፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።

12 Rejoice in the Lord, ye righteous; and give thanks at the remembrance of his holiness.