መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #96
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 96

Psalm 96

1 ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ ምድር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

1 O sing unto the Lord a new song: sing unto the Lord, all the earth.

2 እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።

2 Sing unto the Lord, bless his name; shew forth his salvation from day to day.

3 ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ

3 Declare his glory among the heathen, his wonders among all people.

4 እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና።

4 For the Lord is great, and greatly to be praised: he is to be feared above all gods.

5 የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።

5 For all the gods of the nations are idols: but the Lord made the heavens.

6 ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

6 Honour and majesty are before him: strength and beauty are in his sanctuary.

7 የአሕዛብ ወገኖች፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ

7 Give unto the Lord, O ye kindreds of the people, give unto the Lord glory and strength.

8 ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ ቍርባን ያዙ ወደ አደባባዮችም ግቡ።

8 Give unto the Lord the glory due unto his name: bring an offering, and come into his courts.

9 በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ።

9 O worship the Lord in the beauty of holiness: fear before him, all the earth.

10 በአሕዛብ መካከል። እግዚአብሔር ነገሠ በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

10 Say among the heathen that the Lord reigneth: the world also shall be established that it shall not be moved: he shall judge the people righteously.

11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ

11 Let the heavens rejoice, and let the earth be glad; let the sea roar, and the fulness thereof.

12 በረሃ በእርስዋም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ የዱር ዛፎች ሁሉ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል

12 Let the field be joyful, and all that is therein: then shall all the trees of the wood rejoice

13 ይመጣልና በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

13 Before the Lord: for he cometh, for he cometh to judge the earth: he shall judge the world with righteousness, and the people with his truth.