ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #27
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘዳግም 27

Deuteronomy 27

1 ሙሴና የእስራኤል ሽማግሌዎችም እንዲህ ብለው ሕዝቡን አዘዙ። ዛሬ ያዘዝኋችሁን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ።

1 And Moses with the elders of Israel commanded the people, saying, Keep all the commandments which I command you this day.

2 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ዮርዳኖስን በተሻገርህ ጊዜ ታላላቅ ድንጋዮችን ለአንተ አቁም፥ በኖራም ምረጋቸው።

2 And it shall be on the day when ye shall pass over Jordan unto the land which the Lord thy God giveth thee, that thou shalt set thee up great stones, and plaister them with plaister:

3 የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ትገባ ዘንድ በተሻገርህ ጊዜ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ጻፍባቸው።

3 And thou shalt write upon them all the words of this law, when thou art passed over, that thou mayest go in unto the land which the Lord thy God giveth thee, a land that floweth with milk and honey; as the Lord God of thy fathers hath promised thee.

4 ዮርዳኖስንም በተሻገርህ ጊዜ፥ ዛሬ እንዳዘዝሁህ፥ እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ አቁም፥ በኖራም ምረጋቸው።

4 Therefore it shall be when ye be gone over Jordan, that ye shall set up these stones, which I command you this day, in mount Ebal, and thou shalt plaister them with plaister.

5 በዚያም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ መሠዊያውም ብረት ካልነካው ድንጋይ ይሁን።

5 And there shalt thou build an altar unto the Lord thy God, an altar of stones: thou shalt not lift up any iron tool upon them.

6 ካልተጠረበም ድንጋይ የአምላክህን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ሥራ ለአምላክም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብበት

6 Thou shalt build the altar of the Lord thy God of whole stones: and thou shalt offer burnt offerings thereon unto the Lord thy God:

7 የደኅንነትም መሥዋዕት ሠዋበት፥ በዚያም ብላ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።

7 And thou shalt offer peace offerings, and shalt eat there, and rejoice before the Lord thy God.

8 የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።

8 And thou shalt write upon the stones all the words of this law very plainly.

9 ሙሴና ሌዋውያን ካህናት ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ። እስራኤል ሆይ፥ ዝም ብላችሁ አድምጡ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል።

9 And Moses and the priests the Levites spake unto all Israel, saying, Take heed, and hearken, O Israel; this day thou art become the people of the Lord thy God.

10 ለአምላክህም ለእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ፥ ዛሬም የማዝዝህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን አድርግ።

10 Thou shalt therefore obey the voice of the Lord thy God, and do his commandments and his statutes, which I command thee this day.

11 ሙሴም በዚያን ቀን እንዲህ ብሎ ሕዝቡን አዘዘ።

11 And Moses charged the people the same day, saying,

12 ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ሕዝቡን ይባርኩ ዘንድ እነዚህ፥ ስምዖንና ሌዊ ይሁዳና ይሳኮር ዮሴፍና ብንያም፥ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ።

12 These shall stand upon mount Gerizim to bless the people, when ye are come over Jordan; Simeon, and Levi, and Judah, and Issachar, and Joseph, and Benjamin:

13 ይረግሙም ዘንድ እነዚህ፥ ሮቤልና ጋድ አሴርና ዛብሎን ዳንና ንፍታሌም፥ በጌባል ተራራ ላይ ይቁሙ።

13 And these shall stand upon mount Ebal to curse; Reuben, Gad, and Asher, and Zebulun, Dan, and Naphtali.

14 ሌዋውያንም ከፍ ባለች ድምፅ ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገራሉ።

14 And the Levites shall speak, and say unto all the men of Israel with a loud voice,

15 በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።

15 Cursed be the man that maketh any graven or molten image, an abomination unto the Lord, the work of the hands of the craftsman, and putteth it in a secret place. And all the people shall answer and say, Amen.

16 አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

16 Cursed be he that setteth light by his father or his mother. And all the people shall say, Amen.

17 የባልንጀራውን የድንበር ምልክት የሚገፋ ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

17 Cursed be he that removeth his neighbour’s landmark. And all the people shall say, Amen.

18 ዕውሩን ከመንገድ ፈቀቅ የሚያደርግ ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

18 Cursed be he that maketh the blind to wander out of the way. And all the people shall say, Amen.

19 በመጻተኛ በድሀ አደጉም በመበለቲቱም ላይ ፍርድን የሚያጣምም ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

19 Cursed be he that perverteth the judgment of the stranger, fatherless, and widow. And all the people shall say, Amen.

20 ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የአባቱን ልብስ ገልጦአልና ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

20 Cursed be he that lieth with his father’s wife; because he uncovereth his father’s skirt. And all the people shall say, Amen.

21 ከማናቸይቱም እንስሳ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

21 Cursed be he that lieth with any manner of beast. And all the people shall say, Amen.

22 ከአባቱ ወይም ከእናቱ ልጅ ከእኅቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

22 Cursed be he that lieth with his sister, the daughter of his father, or the daughter of his mother. And all the people shall say, Amen.

23 ከአማቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

23 Cursed be he that lieth with his mother in law. And all the people shall say, Amen.

24 ባልንጀራውን በስውር የሚመታ ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

24 Cursed be he that smiteth his neighbour secretly. And all the people shall say, Amen.

25 የንጹሑን ሰው ነፍስ ለመግደል ጉቦ የሚቀበል ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

25 Cursed be he that taketh reward to slay an innocent person. And all the people shall say, Amen.

26 የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

26 Cursed be he that confirmeth not all the words of this law to do them. And all the people shall say, Amen.