ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #5
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 5

Genesis 5

1 የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው

1 This is the book of the generations of Adam. In the day that God created man, in the likeness of God made he him;

2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው።

2 Male and female created he them; and blessed them, and called their name Adam, in the day when they were created.

3 አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

3 And Adam lived an hundred and thirty years, and begat a son in his own likeness, after his image; and called his name Seth:

4 አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

4 And the days of Adam after he had begotten Seth were eight hundred years: and he begat sons and daughters:

5 አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም።

5 And all the days that Adam lived were nine hundred and thirty years: and he died.

6 ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ

6 And Seth lived an hundred and five years, and begat Enos:

7 ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

7 And Seth lived after he begat Enos eight hundred and seven years, and begat sons and daughters:

8 ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም።

8 And all the days of Seth were nine hundred and twelve years: and he died.

9 ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፥ ቃይናንንም ወለደ

9 And Enos lived ninety years, and begat Cainan:

10 ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ አሥራ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

10 And Enos lived after he begat Cainan eight hundred and fifteen years, and begat sons and daughters:

11 ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ ሞተም።

11 And all the days of Enos were nine hundred and five years: and he died.

12 ቃይናንም መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ መላልኤልንም ወለደ

12 And Cainan lived seventy years, and begat Mahalaleel:

13 ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

13 And Cainan lived after he begat Mahalaleel eight hundred and forty years, and begat sons and daughters:

14 ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥር ዓመት ሆነ ሞተም።

14 And all the days of Cainan were nine hundred and ten years: and he died.

15 መላልኤልም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ያሬድንም ወለደ

15 And Mahalaleel lived sixty and five years, and begat Jared:

16 መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

16 And Mahalaleel lived after he begat Jared eight hundred and thirty years, and begat sons and daughters:

17 መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ ሞተም።

17 And all the days of Mahalaleel were eight hundred ninety and five years: and he died.

18 ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሄኖክንም ወለደ

18 And Jared lived an hundred sixty and two years, and he begat Enoch:

19 ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

19 And Jared lived after he begat Enoch eight hundred years, and begat sons and daughters:

20 ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም።

20 And all the days of Jared were nine hundred sixty and two years: and he died.

21 ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ማቱሳላንም ወለደ

21 And Enoch lived sixty and five years, and begat Methuselah:

22 ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ ማቱሳላንም ከወለደ በኋላ የኖረው ሁለት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

22 And Enoch walked with God after he begat Methuselah three hundred years, and begat sons and daughters:

23 ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ።

23 And all the days of Enoch were three hundred sixty and five years:

24 ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታልና።

24 And Enoch walked with God: and he was not; for God took him.

25 ማቱሳላም መቶ ሰማኒያ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ላሜሕንም ወለደ

25 And Methuselah lived an hundred eighty and seven years, and begat Lamech:

26 ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

26 And Methuselah lived after he begat Lamech seven hundred eighty and two years, and begat sons and daughters:

27 ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ ሞተም።

27 And all the days of Methuselah were nine hundred sixty and nine years: and he died.

28 ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ልጅንም ወለደ።

28 And Lamech lived an hundred eighty and two years, and begat a son:

29 ስሙንም፦ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው።

29 And he called his name Noah, saying, This same shall comfort us concerning our work and toil of our hands, because of the ground which the Lord hath cursed.

30 ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ የኖረው አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

30 And Lamech lived after he begat Noah five hundred ninety and five years, and begat sons and daughters:

31 ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ ሞተም።

31 And all the days of Lamech were seven hundred seventy and seven years: and he died.

32 ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።

32 And Noah was five hundred years old: and Noah begat Shem, Ham, and Japheth.