ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #4
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 4 |
Genesis 4 |
1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች። |
1 And Adam knew Eve his wife; and she conceived, and bare Cain, and said, I have gotten a man from the Lord. |
2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበረ። |
2 And she again bare his brother Abel. And Abel was a keeper of sheep, but Cain was a tiller of the ground. |
3 ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ |
3 And in process of time it came to pass, that Cain brought of the fruit of the ground an offering unto the Lord. |
4 አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ |
4 And Abel, he also brought of the firstlings of his flock and of the fat thereof. And the Lord had respect unto Abel and to his offering: |
5 ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ። |
5 But unto Cain and to his offering he had not respect. And Cain was very wroth, and his countenance fell. |
6 እግዚአብሔርም ቃየንን አለው። ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ? |
6 And the Lord said unto Cain, Why art thou wroth? and why is thy countenance fallen? |
7 መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት። |
7 If thou doest well, shalt thou not be accepted? and if thou doest not well, sin lieth at the door. And unto thee shall be his desire, and thou shalt rule over him. |
8 ቃየንም ወንድሙን አቤልን፦ ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። |
8 And Cain talked with Abel his brother: and it came to pass, when they were in the field, that Cain rose up against Abel his brother, and slew him. |
9 እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ፦ አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? |
9 And the Lord said unto Cain, Where is Abel thy brother? And he said, I know not: Am I my brother’s keeper? |
10 አለውም፦ ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። |
10 And he said, What hast thou done? the voice of thy brother’s blood crieth unto me from the ground. |
11 አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ። |
11 And now art thou cursed from the earth, which hath opened her mouth to receive thy brother’s blood from thy hand; |
12 ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ። |
12 When thou tillest the ground, it shall not henceforth yield unto thee her strength; a fugitive and a vagabond shalt thou be in the earth. |
13 ቃየንም እግዚአብሔርን አለው፦ ኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት። |
13 And Cain said unto the Lord, My punishment is greater than I can bear. |
14 እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኸኝ ከፊትህም እሰወራለሁ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል። |
14 Behold, thou hast driven me out this day from the face of the earth; and from thy face shall I be hid; and I shall be a fugitive and a vagabond in the earth; and it shall come to pass, that every one that findeth me shall slay me. |
15 እግዚአብሔርም እርሱን አለው፦ እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት። |
15 And the Lord said unto him, Therefore whosoever slayeth Cain, vengeance shall be taken on him sevenfold. And the Lord set a mark upon Cain, lest any finding him should kill him. |
16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ። |
16 And Cain went out from the presence of the Lord, and dwelt in the land of Nod, on the east of Eden. |
17 ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም፥ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፥ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖሕ አላት። |
17 And Cain knew his wife; and she conceived, and bare Enoch: and he builded a city, and called the name of the city, after the name of his son, Enoch. |
18 ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ ሜኤልም ማቱሣኤልን ወለደ ማቱሣኤልም ላሜሕን ወለደ። |
18 And unto Enoch was born Irad: and Irad begat Mehujael: and Mehujael begat Methusael: and Methusael begat Lamech. |
19 ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ የአንዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁለተኛይቱ ስም ሴላ ነበረ። |
19 And Lamech took unto him two wives: the name of the one was Adah, and the name of the other Zillah. |
20 ዓዳም ያባልን ወለደች እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ። |
20 And Adah bare Jabal: he was the father of such as dwell in tents, and of such as have cattle. |
21 የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ። |
21 And his brother’s name was Jubal: he was the father of all such as handle the harp and organ. |
22 ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች። |
22 And Zillah, she also bare Tubal–cain, an instructer of every artificer in brass and iron: and the sister of Tubal–cain was Naamah. |
23 ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው። እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፥ ነገሬንም አድምጡ እኔ ጕልማሳውን ለቍስሌ፥ ብላቴናውንም ለመወጋቴ ገድዬዋለሁና |
23 And Lamech said unto his wives, Adah and Zillah, Hear my voice; ye wives of Lamech, hearken unto my speech: for I have slain a man to my wounding, and a young man to my hurt. |
24 ቃየንን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ። ይበቀሉታል |
24 If Cain shall be avenged sevenfold, truly Lamech seventy and sevenfold. |
25 አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም፦ ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው። |
25 And Adam knew his wife again; and she bare a son, and called his name Seth: For God, said she, hath appointed me another seed instead of Abel, whom Cain slew. |
26 ለሴት ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት ስሙንም ሄኖስ አለው በዚያን ጊዜም በእግዚአብሔር ስም መጠራት ተጀመረ። |
26 And to Seth, to him also there was born a son; and he called his name Enos: then began men to call upon the name of the Lord. |