ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #20
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 20 |
Numbers 20 |
1 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች። |
1 Then came the children of Israel, even the whole congregation, into the desert of Zin in the first month: and the people abode in Kadesh; and Miriam died there, and was buried there. |
2 ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም በሙሴና በአሮንም ላይ ተሰበሰቡ። |
2 And there was no water for the congregation: and they gathered themselves together against Moses and against Aaron. |
3 ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት። ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ! |
3 And the people chode with Moses, and spake, saying, Would God that we had died when our brethren died before the Lord! |
4 እኛ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ የእግዚአብሔርን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ? |
4 And why have ye brought up the congregation of the Lord into this wilderness, that we and our cattle should die there? |
5 ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ነው የሚጠጣም ውኃ የለበትም። |
5 And wherefore have ye made us to come up out of Egypt, to bring us in unto this evil place? it is no place of seed, or of figs, or of vines, or of pomegranates; neither is there any water to drink. |
6 ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወደቁ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው። |
6 And Moses and Aaron went from the presence of the assembly unto the door of the tabernacle of the congregation, and they fell upon their faces: and the glory of the Lord appeared unto them. |
7 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
7 And the Lord spake unto Moses, saying, |
8 በትርህን ውሰድ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ። |
8 Take the rod, and gather thou the assembly together, thou, and Aaron thy brother, and speak ye unto the rock before their eyes; and it shall give forth his water, and thou shalt bring forth to them water out of the rock: so thou shalt give the congregation and their beasts drink. |
9 ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ። |
9 And Moses took the rod from before the Lord, as he commanded him. |
10 ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰብስበው። እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናወጣላችኋለን? አላቸው። |
10 And Moses and Aaron gathered the congregation together before the rock, and he said unto them, Hear now, ye rebels; must we fetch you water out of this rock? |
11 ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ። |
11 And Moses lifted up his hand, and with his rod he smote the rock twice: and the water came out abundantly, and the congregation drank, and their beasts also. |
12 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው። |
12 And the Lord spake unto Moses and Aaron, Because ye believed me not, to sanctify me in the eyes of the children of Israel, therefore ye shall not bring this congregation into the land which I have given them. |
13 የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ላይ ጠብ ያደረጉበት፥ እርሱም ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው። |
13 This is the water of Meribah; because the children of Israel strove with the Lord, and he was sanctified in them. |
14 ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ። ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል። ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ |
14 And Moses sent messengers from Kadesh unto the king of Edom, Thus saith thy brother Israel, Thou knowest all the travail that hath befallen us: |
15 አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወረዱ፥ በግብፅም እጅግ ዘመን ተቀመጥን ግብፃውያንም እኛንና አባቶቻችንን በደሉ |
15 How our fathers went down into Egypt, and we have dwelt in Egypt a long time; and the Egyptians vexed us, and our fathers: |
16 ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። |
16 And when we cried unto the Lord, he heard our voice, and sent an angel, and hath brought us forth out of Egypt: and, behold, we are in Kadesh, a city in the uttermost of thy border: |
17 እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም። |
17 Let us pass, I pray thee, through thy country: we will not pass through the fields, or through the vineyards, neither will we drink of the water of the wells: we will go by the king’s high way, we will not turn to the right hand nor to the left, until we have passed thy borders. |
18 ኤዶምያስም። በሰይፍ እንዳልገጥምህ በምድሬ ላይ አታልፍም አለው። |
18 And Edom said unto him, Thou shalt not pass by me, lest I come out against thee with the sword. |
19 የእስራኤልም ልጆች። በጐዳናው እንሄዳለን፥ እኔም ከብቶቼም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፥ ሌላም ምንም አናደርግም ብቻ በእግራችን እንለፍ አሉት። |
19 And the children of Israel said unto him, We will go by the high way: and if I and my cattle drink of thy water, then I will pay for it: I will only, without doing any thing else, go through on my feet. |
20 እርሱም፦ አታልፍም አለ። ኤዶምያስም በብዙ ሕዝብና በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ። |
20 And he said, Thou shalt not go through. And Edom came out against him with much people, and with a strong hand. |
21 ኤዶምያስም እስራኤል በዳርቻው እንዳያልፍ ከለከለ ስለዚህ እስራኤል ከእርሱ ተመለሰ። |
21 Thus Edom refused to give Israel passage through his border: wherefore Israel turned away from him. |
22 ከቃዴስም ተጓዙ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ወደ ሖር ተራራ መጡ። |
22 And the children of Israel, even the whole congregation, journeyed from Kadesh, and came unto mount Hor. |
23 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። |
23 And the Lord spake unto Moses and Aaron in mount Hor, by the coast of the land of Edom, saying, |
24 አሮን ወደ ወገኑ ይከማች በመሪባ ውኃ ዘንድ በቃሌ ላይ ስለ ዐመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም። |
24 Aaron shall be gathered unto his people: for he shall not enter into the land which I have given unto the children of Israel, because ye rebelled against my word at the water of Meribah. |
25 አሮንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው |
25 Take Aaron and Eleazar his son, and bring them up unto mount Hor: |
26 ከአሮንም ልብሱን አውጣ፥ ልጁንም አልዓዛርን አልብሰው አሮንም ወደ ወገኑ ይከማች፥ በዚያም ይሙት። |
26 And strip Aaron of his garments, and put them upon Eleazar his son: and Aaron shall be gathered unto his people, and shall die there. |
27 ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘ አደረገ ማኅበሩም ሁሉ እያዩ ወደ ሖር ተራራ ወጡ። |
27 And Moses did as the Lord commanded: and they went up into mount Hor in the sight of all the congregation. |
28 ሙሴም የአሮንን ልብስ አወጣ፥ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ። |
28 And Moses stripped Aaron of his garments, and put them upon Eleazar his son; and Aaron died there in the top of the mount: and Moses and Eleazar came down from the mount. |
29 ማኅበሩም ሁሉ አሮን እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ፥ የእስራኤል ቤት ሁሉ ለአሮን ሠላሳ ቀን አለቀሱ። |
29 And when all the congregation saw that Aaron was dead, they mourned for Aaron thirty days, even all the house of Israel. |