ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #19
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 19

Numbers 19

1 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።

1 And the Lord spake unto Moses and unto Aaron, saying,

2 እግዚአብሔር ያዘዘው የሕጉ ትእዛዝ ይህ ነው መልካሚቱን፥ ነውርም የሌለባትን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ቀይ ጊደር ያመጡልህ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።

2 This is the ordinance of the law which the Lord hath commanded, saying, Speak unto the children of Israel, that they bring thee a red heifer without spot, wherein is no blemish, and upon which never came yoke:

3 እርስዋንም ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጣላችሁ፥ እርስዋንም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወስዳታል፥ አንድ ሰውም በፊቱ ያርዳታል።

3 And ye shall give her unto Eleazar the priest, that he may bring her forth without the camp, and one shall slay her before his face:

4 ካህኑም አልዓዛር ከደምዋ በጣቱ ይወስዳል፥ ከደምዋም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል።

4 And Eleazar the priest shall take of her blood with his finger, and sprinkle of her blood directly before the tabernacle of the congregation seven times:

5 ጊደሪቱም በፊቱ ትቃጠላለች ቁርበትዋም ሥጋዋም ደምዋም ፈርስዋም ይቃጠላል።

5 And one shall burn the heifer in his sight; her skin, and her flesh, and her blood, with her dung, shall he burn:

6 ካህኑም የዝግባ እንጨት ሂሶጵም ቀይ ግምጃም ወስዶ ጊደሪቱ በምትቃጠልበት እሳት መካከል ይጥለዋል።

6 And the priest shall take cedar wood, and hyssop, and scarlet, and cast it into the midst of the burning of the heifer.

7 ካህኑም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል ካህኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል።

7 Then the priest shall wash his clothes, and he shall bathe his flesh in water, and afterward he shall come into the camp, and the priest shall be unclean until the even.

8 ያቃጠላትም ሰው ልብሱን በውኃ ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።

8 And he that burneth her shall wash his clothes in water, and bathe his flesh in water, and shall be unclean until the even.

9 ንጹሕም ሰው የጊደሪቱን አመድ ያከማቻል ከሰፈሩም ውጭ በንጹሕ ስፍራ ያኖረዋል ርኵሰትም ለሚያነጻ ውኃ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ይጠበቃል ከኃጢአት ለማንጻት የሚሆን ነው።

9 And a man that is clean shall gather up the ashes of the heifer, and lay them up without the camp in a clean place, and it shall be kept for the congregation of the children of Israel for a water of separation: it is a purification for sin.

10 የጊደሪቱንም አመድ ያከማቸ ሰው ልብሱን ያጥባል እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል ይህም ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ለሚኖር መጻተኛ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል።

10 And he that gathereth the ashes of the heifer shall wash his clothes, and be unclean until the even: and it shall be unto the children of Israel, and unto the stranger that sojourneth among them, for a statute for ever.

11 የሞተውን ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኵስ ይሆናል

11 He that toucheth the dead body of any man shall be unclean seven days.

12 በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፥ ንጹሕም ይሆናል ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም።

12 He shall purify himself with it on the third day, and on the seventh day he shall be clean: but if he purify not himself the third day, then the seventh day he shall not be clean.

13 የሞተውን ሰው በድን የነካ ሁለመናውን ባያጠራ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ያረክሳል ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል በእርሱም ላይ የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል ርኵሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።

13 Whosoever toucheth the dead body of any man that is dead, and purifieth not himself, defileth the tabernacle of the Lord; and that soul shall be cut off from Israel: because the water of separation was not sprinkled upon him, he shall be unclean; his uncleanness is yet upon him.

14 ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኵስ ይሆናል።

14 This is the law, when a man dieth in a tent: all that come into the tent, and all that is in the tent, shall be unclean seven days.

15 መክደኛው ያልታሰረ የተከፈተ ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።

15 And every open vessel, which hath no covering bound upon it, is unclean.

16 በሜዳም በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን አጥንት ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።

16 And whosoever toucheth one that is slain with a sword in the open fields, or a dead body, or a bone of a man, or a grave, shall be unclean seven days.

17 ከኃጢአት ለማንጻት እንድትሆን ከተቃጠለችው ጊደር አመድ ለርኩሱ ይወስዱለታል፥ በዕቃውም ውስጥ የምንጭ ውኃ ይቀላቀልበታል።

17 And for an unclean person they shall take of the ashes of the burnt heifer of purification for sin, and running water shall be put thereto in a vessel:

18 ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ያጠልቀዋል በድንኳኑም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥንቱንም ወይም የተገደለውን ወይም የሞተውን ወይም መቃብሩን በነካው ላይ ይረጨዋል

18 And a clean person shall take hyssop, and dip it in the water, and sprinkle it upon the tent, and upon all the vessels, and upon the persons that were there, and upon him that touched a bone, or one slain, or one dead, or a grave:

19 ንጹሑም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን በርኩሱ ላይ ይረጨዋል ባሰባተኛውም ቀን ያጠራዋል እርሱም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ በማታም ጊዜ ንጹሕ ይሆናል።

19 And the clean person shall sprinkle upon the unclean on the third day, and on the seventh day: and on the seventh day he shall purify himself, and wash his clothes, and bathe himself in water, and shall be clean at even.

20 ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያጠራ፥ ያ ሰው የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል በሚያነጻ ውኃ አልተረጨም ርኩስ ነው።

20 But the man that shall be unclean, and shall not purify himself, that soul shall be cut off from among the congregation, because he hath defiled the sanctuary of the Lord: the water of separation hath not been sprinkled upon him; he is unclean.

21 ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሆንላችኋል የሚያነጻውን ውኃ የሚረጭ ሰው ልብሱን ያጥባል የሚያነጻውንም ውኃ የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

21 And it shall be a perpetual statute unto them, that he that sprinkleth the water of separation shall wash his clothes; and he that toucheth the water of separation shall be unclean until even.

22 ርኩሱም የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

22 And whatsoever the unclean person toucheth shall be unclean; and the soul that toucheth it shall be unclean until even.