መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #95
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 95 |
Psalm 95 |
1 ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለአምላክ ለመድኃኒታችን እልል እንበል። |
1 O come, let us sing unto the Lord: let us make a joyful noise to the rock of our salvation. |
2 በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል |
2 Let us come before his presence with thanksgiving, and make a joyful noise unto him with psalms. |
3 እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና። |
3 For the Lord is a great God, and a great King above all gods. |
4 እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውም የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው። |
4 In his hand are the deep places of the earth: the strength of the hills is his also. |
5 ባሕር የእርሱ ናት እርሱም አደረጋት፥ የብስንም እጆቹ ሠሩአት። |
5 The sea is his, and he made it: and his hands formed the dry land. |
6 ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ |
6 O come, let us worship and bow down: let us kneel before the Lord our maker. |
7 እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና። |
7 For he is our God; and we are the people of his pasture, and the sheep of his hand. To day if ye will hear his voice, |
8 በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ። |
8 Harden not your heart, as in the provocation, and as in the day of temptation in the wilderness: |
9 የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ ሥራዬንም አዩ። |
9 When your fathers tempted me, proved me, and saw my work. |
10 ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር። ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ። |
10 Forty years long was I grieved with this generation, and said, It is a people that do err in their heart, and they have not known my ways: |
11 ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ። |
11 Unto whom I sware in my wrath that they should not enter into my rest. |