ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #3
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 3

Leviticus 3

1 ቍርባኑም የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።

1 And if his oblation be a sacrifice of peace offering, if he offer it of the herd; whether it be a male or female, he shall offer it without blemish before the Lord.

2 እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

2 And he shall lay his hand upon the head of his offering, and kill it at the door of the tabernacle of the congregation: and Aaron’s sons the priests shall sprinkle the blood upon the altar round about.

3 ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርጎ ያቀርባል የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥

3 And he shall offer of the sacrifice of the peace offering an offering made by fire unto the Lord; the fat that covereth the inwards, and all the fat that is upon the inwards,

4 ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጕበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶች ጋር ይወስዳል።

4 And the two kidneys, and the fat that is on them, which is by the flanks, and the caul above the liver, with the kidneys, it shall he take away.

5 የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥሉታል የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ ነው።

5 And Aaron’s sons shall burn it on the altar upon the burnt sacrifice, which is upon the wood that is on the fire: it is an offering made by fire, of a sweet savour unto the Lord.

6 ለእግዚአብሔርም ለደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቍርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል።

6 And if his offering for a sacrifice of peace offering unto the Lord be of the flock; male or female, he shall offer it without blemish.

7 ለቍርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል

7 If he offer a lamb for his offering, then shall he offer it before the Lord.

8 እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛው ድንኳን ፊት ያርደዋል የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

8 And he shall lay his hand upon the head of his offering, and kill it before the tabernacle of the congregation: and Aaron’s sons shall sprinkle the blood thereof round about upon the altar.

9 ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርጎ ያቀርባል ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ላቱን ሁሉ፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥

9 And he shall offer of the sacrifice of the peace offering an offering made by fire unto the Lord; the fat thereof, and the whole rump, it shall he take off hard by the backbone; and the fat that covereth the inwards, and all the fat that is upon the inwards,

10 ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጕበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶች ጋር ይወስዳል።

10 And the two kidneys, and the fat that is upon them, which is by the flanks, and the caul above the liver, with the kidneys, it shall he take away.

11 ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል በእሳት ላይ ለእግዚአብሔር የተደረገ የቍርባን መብል ነው።

11 And the priest shall burn it upon the altar: it is the food of the offering made by fire unto the Lord.

12 ቍርባኑም ፍየል ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል

12 And if his offering be a goat, then he shall offer it before the Lord.

13 እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

13 And he shall lay his hand upon the head of it, and kill it before the tabernacle of the congregation: and the sons of Aaron shall sprinkle the blood thereof upon the altar round about.

14 ከእርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርጎ ያቀርበዋል ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥

14 And he shall offer thereof his offering, even an offering made by fire unto the Lord; the fat that covereth the inwards, and all the fat that is upon the inwards,

15 ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጕበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶች ጋር ይወስዳል።

15 And the two kidneys, and the fat that is upon them, which is by the flanks, and the caul above the liver, with the kidneys, it shall he take away.

16 ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል በእሳት ላይ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የተደረገ መብል ነው። ስቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው።

16 And the priest shall burn them upon the altar: it is the food of the offering made by fire for a sweet savour: all the fat is the Lord’s.

17 ስብና ደም እንዳትበሉ በምትኖሩበት ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።

17 It shall be a perpetual statute for your generations throughout all your dwellings, that ye eat neither fat nor blood.