ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #43
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 43

Genesis 43

1-2 ራብም በምድር ጸና። ከግብፅም ያመጡትን እህል በልተው ከፈጸሙ በኋላ አባታቸው። እንደ ገና ሂዱ ጥቂት እህል ሸምቱልን አላቸው።

1 And the famine was sore in the land.
2 And it came to pass, when they had eaten up the corn which they had brought out of Egypt, their father said unto them, Go again, buy us a little food.

3 ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው። ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዩም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን።

3 And Judah spake unto him, saying, The man did solemnly protest unto us, saying, Ye shall not see my face, except your brother be with you.

4 ወንድማችንን ከእኛ ጋር ብትሰድደው እንወርዳለን፥ እህልም እንሸምትልሃለን

4 If thou wilt send our brother with us, we will go down and buy thee food:

5 ባትሰድደው ግን አንሄድም ያ ሰው። ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዩም ብሎናልና።

5 But if thou wilt not send him, we will not go down: for the man said unto us, Ye shall not see my face, except your brother be with you.

6 እስራኤልም አላቸው። ለምን በደላችሁኝ? ለዚያውስ። ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁት?

6 And Israel said, Wherefore dealt ye so ill with me, as to tell the man whether ye had yet a brother?

7 እነርሱም አሉ፦ ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ወገናችን ፈጽሞ ጠየቀን እንዲህም አለን፦ አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን? እኛም እንደዚሁ እንደ ጥያቄው መለስንለት በውኑ። ወንድማችሁን አምጡ እንዲለን እናውቅ ነበርነን?

7 And they said, The man asked us straitly of our state, and of our kindred, saying, Is your father yet alive? have ye another brother? and we told him according to the tenor of these words: could we certainly know that he would say, Bring your brother down?

8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው። እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ስደደው፥ እኛም ተነሥተን እንሄዳለን።

8 And Judah said unto Israel his father, Send the lad with me, and we will arise and go; that we may live, and not die, both we, and thou, and also our little ones.

9 እኔ ስለ እርሱ እዋሳለሁ ከእጄ ትሻዋለህ ወደ አንተ ባላመጣው፥ በፊትህም ባላቆመው፥ በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁ ልሁን።

9 I will be surety for him; of my hand shalt thou require him: if I bring him not unto thee, and set him before thee, then let me bear the blame for ever:

10 ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር።

10 For except we had lingered, surely now we had returned this second time.

11 እስራኤልም አባታቸው እንዲህ አላቸው፦ ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህንን አድርጉ ከተመሰገነው ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፥ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ከርቤ፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።

11 And their father Israel said unto them, If it must be so now, do this; take of the best fruits in the land in your vessels, and carry down the man a present, a little balm, and a little honey, spices, and myrrh, nuts, and almonds:

12 ብሩን በአጠፌታ አድርጋችሁ በእጃችሁ ውሰዱ በዓይበታችሁ አፍ የተመለሰውንም ብር መልሳችሁ ውሰዱ ምናልባት በስሕተት ይሆናል።

12 And take double money in your hand; and the money that was brought again in the mouth of your sacks, carry it again in your hand; peradventure it was an oversight:

13 ወንድማችሁንም ውሰዱ፥ ተነሥታችሁም ወደዚያ ሰው ተመለሱ።

13 Take also your brother, and arise, go again unto the man:

14 ሁሉን የሚችል አምላክም ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ከእናንተ ጋር ይሰድድ ዘንድ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይስጣችሁ እኔም ልጆቼን እንዳጣሁ አጣሁ።

14 And God Almighty give you mercy before the man, that he may send away your other brother, and Benjamin. If I be bereaved of my children, I am bereaved.

15 ሰዎቹም በእጃቸው ያችን እጅ መንሻና አጠፌታውን ብር ብንያምንም ወሰዱ ተነሥተውም ወደ ግብፅ ወረዱ፥ በዮሴፍም ፊት ቆሙ።

15 And the men took that present, and they took double money in their hand, and Benjamin; and rose up, and went down to Egypt, and stood before Joseph.

16 ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፥ እርድም እረድ አዘጋጅም፥ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።

16 And when Joseph saw Benjamin with them, he said to the ruler of his house, Bring these men home, and slay, and make ready; for these men shall dine with me at noon.

17 ያ ሰውም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ ያ ሰውም ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባ።

17 And the man did as Joseph bade; and the man brought the men into Joseph’s house.

18 እነርሱም ወደ ዮሴፍ ቤት ስለ ገቡ ፈሩ እንዲህም አሉ። በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኰልብን ሊወድቅብንም፥ እኛንም በባርነት ሊገዛ አህዮቻችንንም ሊወስድ ወደዚህ አስገባን።

18 And the men were afraid, because they were brought into Joseph’s house; and they said, Because of the money that was returned in our sacks at the first time are we brought in; that he may seek occasion against us, and fall upon us, and take us for bondmen, and our asses.

19 ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥም ቀረቡ፥ በቤቱም ደጅ ተናገሩት፥

19 And they came near to the steward of Joseph’s house, and they communed with him at the door of the house,

20 እንዲህም አሉት፦ ጌታዬ ሆይ፥ ቀድሞ እህልን ልንሸምት ወርደን ነበር

20 And said, O sir, we came indeed down at the first time to buy food:

21 ወደምናድርበትም ስፍራ በደረስን ጊዜ ዓይበታችንን ከፈትን፥ እነሆም፥ የእያንዳንዱ ሰው ብር በየዓይበቱ አፍ እንደ ሚዛኑ ብራችን ነበረ አሁንም በእጃችን መለስነው።

21 And it came to pass, when we came to the inn, that we opened our sacks, and, behold, every man’s money was in the mouth of his sack, our money in full weight: and we have brought it again in our hand.

22 እህል እንሸምትበት ዘንድ ሌላም ብር በእጃችን አመጣን ብራችንንም በዓይበታችን ማን እንደ ጨመረው አናውቅም።

22 And other money have we brought down in our hands to buy food: we cannot tell who put our money in our sacks.

23 እርሱም አላቸው። ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ ብራችሁስ ደርሶኛል።

23 And he said, Peace be to you, fear not: your God, and the God of your father, hath given you treasure in your sacks: I had your money. And he brought Simeon out unto them.

24 ስምዖንንም አወጣላቸው። ሰውዮውም እነዚያን ስዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው ውኃ አመጣላቸው፥ እግራቸውንም ታጠቡ ለአህዮቻቸው አበቅ ሰጣቸው።

24 And the man brought the men into Joseph’s house, and gave them water, and they washed their feet; and he gave their asses provender.

25 ዮሴፍም በእኩለ ቀን እስኪገባ ድረስ እነርሱ እጅ መንሻቸውን አዘጋጁ፥ ከዚያ እንጀራን እንደሚበሉ ሰምተዋልና።

25 And they made ready the present against Joseph came at noon: for they heard that they should eat bread there.

26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት፥ ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት።

26 And when Joseph came home, they brought him the present which was in their hand into the house, and bowed themselves to him to the earth.

27 እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው፥እንዲህም አለ፦ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን?

27 And he asked them of their welfare, and said, Is your father well, the old man of whom ye spake? Is he yet alive?

28 እነርሱም አሉት። ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው ገና በሕይወት አለ። አጐንብሰውም ሰገዱለት።

28 And they answered, Thy servant our father is in good health, he is yet alive. And they bowed down their heads, and made obeisance.

29 ዓይኑንም አንሥቶ የእናቱን ልጅ ብንያምን አየው፥ እርሱም አለ፦ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን? እንዲህም አለው፦ ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ።

29 And he lifted up his eyes, and saw his brother Benjamin, his mother’s son, and said, Is this your younger brother, of whom ye spake unto me? And he said, God be gracious unto thee, my son.

30 ዮሴፍም ቸኮለ፥ አንጀቱ ወንድሙን ናፍቆታልና ሊያለቅስም ወደደ ወደ እልፍኙም ገብቶ ከዚያ አለቀሰ።

30 And Joseph made haste; for his bowels did yearn upon his brother: and he sought where to weep; and he entered into his chamber, and wept there.

31 ፊቱንም ታጥቦ ወጣ፥ ልቡንም አስታግሦ። እንጀራ አቅርቡ አለ።

31 And he washed his face, and went out, and refrained himself, and said, Set on bread.

32 ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ፥ ለእነርሱም ለብቻቸው፥ ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና፥ ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።

32 And they set on for him by himself, and for them by themselves, and for the Egyptians, which did eat with him, by themselves: because the Egyptians might not eat bread with the Hebrews; for that is an abomination unto the Egyptians.

33 በፊቱም በኵሩ እንደ ታላቅነቱ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ ተቀመጡ ሰዎቹም እርስ በርሳቸው ተደነቁ።

33 And they sat before him, the firstborn according to his birthright, and the youngest according to his youth: and the men marvelled one at another.

34 በፊቱም ካለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው የብንያምም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ። እነርሱም ጠጡ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው።

34 And he took and sent messes unto them from before him: but Benjamin’s mess was five times so much as any of theirs. And they drank, and were merry with him.