ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #12
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 12 |
Genesis 12 |
1 እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። |
1 Now the Lord had said unto Abram, Get thee out of thy country, and from thy kindred, and from thy father’s house, unto a land that I will shew thee: |
2 ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ ለበረከትም ሁን |
2 And I will make of thee a great nation, and I will bless thee, and make thy name great; and thou shalt be a blessing: |
3 የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። |
3 And I will bless them that bless thee, and curse him that curseth thee: and in thee shall all families of the earth be blessed. |
4 አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። |
4 So Abram departed, as the Lord had spoken unto him; and Lot went with him: and Abram was seventy and five years old when he departed out of Haran. |
5 አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ። |
5 And Abram took Sarai his wife, and Lot his brother’s son, and all their substance that they had gathered, and the souls that they had gotten in Haran; and they went forth to go into the land of Canaan; and into the land of Canaan they came. |
6 አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። |
6 And Abram passed through the land unto the place of Sichem, unto the plain of Moreh. And the Canaanite was then in the land. |
7 እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። |
7 And the Lord appeared unto Abram, and said, Unto thy seed will I give this land: and there builded he an altar unto the Lord, who appeared unto him. |
8 ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ። |
8 And he removed from thence unto a mountain on the east of Beth–el, and pitched his tent, having Beth–el on the west, and Hai on the east: and there he builded an altar unto the Lord, and called upon the name of the Lord. |
9 አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ። |
9 And Abram journeyed, going on still toward the south. |
10 በምድርም ራብ ሆነ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና። |
10 And there was a famine in the land: and Abram went down into Egypt to sojourn there; for the famine was grievous in the land. |
11 ወደ ግብፅም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፦ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ |
11 And it came to pass, when he was come near to enter into Egypt, that he said unto Sarai his wife, Behold now, I know that thou art a fair woman to look upon: |
12 የግብፅ ሰዎች ያዩሽ እንደ ሆነ፦ ሚስቱ ናት ይላሉ እኔንም ይገድሉኛል፥ አንቺንም በሕይወት ይተዉሻል። |
12 Therefore it shall come to pass, when the Egyptians shall see thee, that they shall say, This is his wife: and they will kill me, but they will save thee alive. |
13 እንግዲህ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ፥ ስለ አንቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ፦ እኅቱ ነኝ በዪ። |
13 Say, I pray thee, thou art my sister: that it may be well with me for thy sake; and my soul shall live because of thee. |
14 አብራምም ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ የግብፅ ሰዎች ሴቲቱን እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ |
14 And it came to pass, that, when Abram was come into Egypt, the Egyptians beheld the woman that she was very fair. |
15 የፈርዖንም አለቆች አዩአት፥ በፈርዖንም ፊት አመሰገኑአት ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት። |
15 The princes also of Pharaoh saw her, and commended her before Pharaoh: and the woman was taken into Pharaoh’s house. |
16 ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረገለት ለእርሱ በጎችም በሬዎችም አህዮችም ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም ግመሎችም ነበሩት። |
16 And he entreated Abram well for her sake: and he had sheep, and oxen, and he asses, and menservants, and maidservants, and she asses, and camels. |
17 እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ። |
17 And the Lord plagued Pharaoh and his house with great plagues because of Sarai Abram’s wife. |
18 ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው። ይህ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም? |
18 And Pharaoh called Abram, and said, What is this that thou hast done unto me? why didst thou not tell me that she was thy wife? |
19 ለምንስ፦ እኅቴ ናት አልህ? እኔ ሚስት ላደርጋት ወስጄአት ነበር። አሁንም ሚስትህ እነኋት ይዘሃት ሂድ። |
19 Why saidst thou, She is my sister? so I might have taken her to me to wife: now therefore behold thy wife, take her, and go thy way. |
20 ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው። |
20 And Pharaoh commanded his men concerning him: and they sent him away, and his wife, and all that he had. |