ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #13
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 13

Genesis 13

1 አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ።

1 And Abram went up out of Egypt, he, and his wife, and all that he had, and Lot with him, into the south.

2 አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ።

2 And Abram was very rich in cattle, in silver, and in gold.

3 ከአዜብ ባደረገው በጕዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው

3 And he went on his journeys from the south even to Beth–el, unto the place where his tent had been at the beginning, between Beth–el and Hai;

4 ያም ስፍራ አስቀድሞ መሠውያ የሠራበት ነው በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።

4 Unto the place of the altar, which he had made there at the first: and there Abram called on the name of the Lord.

5 ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው።

5 And Lot also, which went with Abram, had flocks, and herds, and tents.

6 በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም የነበራቸው እጅግ ነበረና በአንድነት ሊቀመጡ አልቻሉም።

6 And the land was not able to bear them, that they might dwell together: for their substance was great, so that they could not dwell together.

7 የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ በዚያም ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።

7 And there was a strife between the herdmen of Abram’s cattle and the herdmen of Lot’s cattle: and the Canaanite and the Perizzite dwelled then in the land.

8 አብራምም ሎጥን አለው፦ እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ።

8 And Abram said unto Lot, Let there be no strife, I pray thee, between me and thee, and between my herdmen and thy herdmen; for we be brethren.

9 ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።

9 Is not the whole land before thee? separate thyself, I pray thee, from me: if thou wilt take the left hand, then I will go to the right; or if thou depart to the right hand, then I will go to the left.

10 ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ዞዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።

10 And Lot lifted up his eyes, and beheld all the plain of Jordan, that it was well watered every where, before the Lord destroyed Sodom and Gomorrah, even as the garden of the Lord, like the land of Egypt, as thou comest unto Zoar.

11 ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ።

11 Then Lot chose him all the plain of Jordan; and Lot journeyed east: and they separated themselves the one from the other.

12 አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜዳ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ሰዶምም ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ።

12 Abram dwelled in the land of Canaan, and Lot dwelled in the cities of the plain, and pitched his tent toward Sodom.

13 የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ።

13 But the men of Sodom were wicked and sinners before the Lord exceedingly.

14 ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው። ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ

14 And the Lord said unto Abram, after that Lot was separated from him, Lift up now thine eyes, and look from the place where thou art northward, and southward, and eastward, and westward:

15 የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና።

15 For all the land which thou seest, to thee will I give it, and to thy seed for ever.

16 ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል።

16 And I will make thy seed as the dust of the earth: so that if a man can number the dust of the earth, then shall thy seed also be numbered.

17 ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና።

17 Arise, walk through the land in the length of it and in the breadth of it; for I will give it unto thee.

18 አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።

18 Then Abram removed his tent, and came and dwelt in the plain of Mamre, which is in Hebron, and built there an altar unto the Lord.