ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #34
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 34

Genesis 34

1 ለያዕቆብ የወለደችለት የልያ ልጅ ዲናም የዚያን አገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች።

1 And Dinah the daughter of Leah, which she bare unto Jacob, went out to see the daughters of the land.

2 የአገሩ አለቃ የኤዊያዊ ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት ወሰዳትም ከእርስዋም ጋር ተኛ፥ አስነወራትም።

2 And when Shechem the son of Hamor the Hivite, prince of the country, saw her, he took her, and lay with her, and defiled her.

3 ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፥ ብላቴናይቱንም ወደዳት፥ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት።

3 And his soul clave unto Dinah the daughter of Jacob, and he loved the damsel, and spake kindly unto the damsel.

4 ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፦ ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው።

4 And Shechem spake unto his father Hamor, saying, Get me this damsel to wife.

5 ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።

5 And Jacob heard that he had defiled Dinah his daughter: now his sons were with his cattle in the field: and Jacob held his peace until they were come.

6 የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ።

6 And Hamor the father of Shechem went out unto Jacob to commune with him.

7 የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከምድረ በዳ መጡ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ስንፍናን ስላደረገ አዘኑ፥ እጅግም ተቈጡ እንዲህ አይደረግምና።

7 And the sons of Jacob came out of the field when they heard it: and the men were grieved, and they were very wroth, because he had wrought folly in Israel in lying with Jacob’s daughter; which thing ought not to be done.

8 ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው። ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት።

8 And Hamor communed with them, saying, The soul of my son Shechem longeth for your daughter: I pray you give her him to wife.

9 ጋብቾችም ሁኑን ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፥ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ።

9 And make ye marriages with us, and give your daughters unto us, and take our daughters unto you.

10 ከእኛም ጋር ተቀመጡ፥ ምድሪቱም በፊታችሁ ናት ኑሩባት፥ ነግዱም፥ ግዙአትም።

10 And ye shall dwell with us: and the land shall be before you; dwell and trade ye therein, and get you possessions therein.

11 ሴኬምም አባትዋንና ወንድሞችዋን እንዲህ አለ፦ በፊታችሁ ሞገስን ባገኝ የምትሉኝን እሰጣለሁ።

11 And Shechem said unto her father and unto her brethren, Let me find grace in your eyes, and what ye shall say unto me I will give.

12 ብዙ ማጫና እጅ መንሻ አምጣ በሉኝ፥ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ ይህችን ብላቴና ግን አጋቡኝ።

12 Ask me never so much dowry and gift, and I will give according as ye shall say unto me: but give me the damsel to wife.

13 የያዕቆብም ልጆች ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መለሱ፥ እኅታቸውን ዲናን አርክሶአታልና

13 And the sons of Jacob answered Shechem and Hamor his father deceitfully, and said, because he had defiled Dinah their sister:

14 እንዲህም አሉአቸው፦ እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህንን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም ይህ ነውር ይሆንብናልና።

14 And they said unto them, We cannot do this thing, to give our sister to one that is uncircumcised; for that were a reproach unto us:

15 እንደ እኛ ሆናችሁ ወንዶቻችሁን ሁሉ ብትገርዙ በዚህ ብቻ እሺ እንላችኋለን

15 But in this will we consent unto you: If ye will be as we be, that every male of you be circumcised;

16 ሴቶች ልጆቻችንን እንሰጣችኋለን፥ የእናንተንም ሴቶች ልጆች እንወስዳለን አንድ ሕዝብም ሆነን ከእናንተ ጋር እንኖራለን።

16 Then will we give our daughters unto you, and we will take your daughters to us, and we will dwell with you, and we will become one people.

17 ትገረዙ ዘንድ እኛን ባትሰሙ ግን ልጃችንን ይዘን እንሄዳለን።

17 But if ye will not hearken unto us, to be circumcised; then will we take our daughter, and we will be gone.

18 ነገራቸውም በኤሞር ልጅ በሴኬምና በኤሞር ዘንድ የተወደደ ሆነ።

18 And their words pleased Hamor, and Shechem Hamor’s son.

19 ብላቴናውም ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም፥ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ።

19 And the young man deferred not to do the thing, because he had delight in Jacob’s daughter: and he was more honourable than all the house of his father.

20 ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ፥ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው ነገሩ።

20 And Hamor and Shechem his son came unto the gate of their city, and communed with the men of their city, saying,

21 እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ።

21 These men are peaceable with us; therefore let them dwell in the land, and trade therein; for the land, behold, it is large enough for them; let us take their daughters to us for wives, and let us give them our daughters.

22 ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ።

22 Only herein will the men consent unto us for to dwell with us, to be one people, if every male among us be circumcised, as they are circumcised.

23 ከብቶቻቸውም ያላቸውም ሁሉ እንስሶቻቸውም ሁሉ ለእኛ አይደሉምን? በዚህ ነገር ብቻ እሺ ያልናቸው እንደ ሆነ ከእኛ ጋር ይቀመጣሉ።

23 Shall not their cattle and their substance and every beast of theirs be ours? only let us consent unto them, and they will dwell with us.

24 ከከተማይቱም አደባባይ የሚወጡ ሁሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን እሺ አሉ ከከተማይቱ አደባባይ የሚወጡት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ።

24 And unto Hamor and unto Shechem his son hearkened all that went out of the gate of his city; and every male was circumcised, all that went out of the gate of his city.

25 ሦስተኛም ቀን በሆነ ጊዜ እጅግ ቆስለው ሳሉ፥ የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ፥ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ

25 And it came to pass on the third day, when they were sore, that two of the sons of Jacob, Simeon and Levi, Dinah’s brethren, took each man his sword, and came upon the city boldly, and slew all the males.

26 ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፥ እኅታቸውን ዲናንም ከሴኬም ቤት ይዘው ወጡ።

26 And they slew Hamor and Shechem his son with the edge of the sword, and took Dinah out of Shechem’s house, and went out.

27 የያዕቆብም ልጆች እኅታቸውን ዲናን ስለ አረከሱአት ወደ ሞቱት ገብተው ከተማይቱን ዘረፉ

27 The sons of Jacob came upon the slain, and spoiled the city, because they had defiled their sister.

28 በጎቻቸውንም ላሞቻቸውንም አህዮቻቸውንም በውጭም በከተማም ያለውን ወሰዱ።

28 They took their sheep, and their oxen, and their asses, and that which was in the city, and that which was in the field,

29 ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም ሁሉ ማረኩ፥ በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ።

29 And all their wealth, and all their little ones, and their wives took they captive, and spoiled even all that was in the house.

30 ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይመቱኛል እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ።

30 And Jacob said to Simeon and Levi, Ye have troubled me to make me to stink among the inhabitants of the land, among the Canaanites and the Perizzites: and I being few in number, they shall gather themselves together against me, and slay me; and I shall be destroyed, I and my house.

31 እርሱም፦ በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኅታችን ያደርግባትን? አሉ።

31 And they said, Should he deal with our sister as with an harlot?