መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #135
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 135

Psalm 135

1 ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥

1 Praise ye the Lord. Praise ye the name of the Lord; praise him, O ye servants of the Lord.

2 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።

2 Ye that stand in the house of the Lord, in the courts of the house of our God,

3 እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና

3 Praise the Lord; for the Lord is good: sing praises unto his name; for it is pleasant.

4 እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ እስራኤልንም ለመዝገቡ መርጦታልና

4 For the Lord hath chosen Jacob unto himself, and Israel for his peculiar treasure.

5 እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አውቄአለሁና።

5 For I know that the Lord is great, and that our Lord is above all gods.

6 በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ።

6 Whatsoever the Lord pleased, that did he in heaven, and in earth, in the seas, and all deep places.

7 ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል በዝናብ ጊዜ መብረቅን አደረገ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።

7 He causeth the vapours to ascend from the ends of the earth; he maketh lightnings for the rain; he bringeth the wind out of his treasuries.

8 የግብጽን በኵር ልጆች ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ መታ።

8 Who smote the firstborn of Egypt, both of man and beast.

9 ግብጽ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ ተኣምራትንና ድንቅን ሰደደ።

9 Who sent tokens and wonders into the midst of thee, O Egypt, upon Pharaoh, and upon all his servants.

10 ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።

10 Who smote great nations, and slew mighty kings;

11 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ የባሳንንም ንጉሥ ዐግን፥ የከነዓንን መንግሥታት ሁሉ ገደለ

11 Sihon king of the Amorites, and Og king of Bashan, and all the kingdoms of Canaan:

12 ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ለሕዝቡ ርስት ሰጠ።

12 And gave their land for an heritage, an heritage unto Israel his people.

13 አቤቱ፥ ስምህ ለዘላለም ነው፥ ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነው

13 Thy name, O Lord, endureth for ever; and thy memorial, O Lord, throughout all generations.

14 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባሪያዎቹንም ይረዳልና።

14 For the Lord will judge his people, and he will repent himself concerning his servants.

15 የአሕዛብ ጣዖታት የብርና የወርቅ፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።

15 The idols of the heathen are silver and gold, the work of men’s hands.

16 አፍ አላቸው፥ አይናገሩምም ዓይን አላቸው፥ አያዩምም

16 They have mouths, but they speak not; eyes have they, but they see not;

17 ጆሮ አላቸው፥ አይሰሙምም እስትንፋስም በአፋቸው የለም።

17 They have ears, but they hear not; neither is there any breath in their mouths.

18 የሚሠሩአቸው ሁሉ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁን።

18 They that make them are like unto them: so is every one that trusteth in them.

19 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት። የአሮን ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት

19 Bless the Lord, O house of Israel: bless the Lord, O house of Aaron:

20 የሌዊ ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት።

20 Bless the Lord, O house of Levi: ye that fear the Lord, bless the Lord.

21 በኢየሩሳሌም የሚያድር እግዚአብሔር ከጽዮን የተባረከ ነው። ሃሌ ሉያ።

21 Blessed be the Lord out of Zion, which dwelleth at Jerusalem. Praise ye the Lord.