ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #35
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 35 |
Genesis 35 |
1 እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው። ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን አድርግ። |
1 And God said unto Jacob, Arise, go up to Beth–el, and dwell there: and make there an altar unto God, that appeared unto thee when thou fleddest from the face of Esau thy brother. |
2 ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ |
2 Then Jacob said unto his household, and to all that were with him, Put away the strange gods that are among you, and be clean, and change your garments: |
3 ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ። |
3 And let us arise, and go up to Beth–el; and I will make there an altar unto God, who answered me in the day of my distress, and was with me in the way which I went. |
4 በእጃቸው ያሉትንም እንግዶችን አማልክት ሁሉ በጆሮአቸውም ያሉትን ጕትቾች ለያዕቆብ ሰጡት ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የአድባር ዛፍ በታች ቀበራቸው። |
4 And they gave unto Jacob all the strange gods which were in their hand, and all their earrings which were in their ears; and Jacob hid them under the oak which was by Shechem. |
5 ተነሥተውም ሄዱ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም። |
5 And they journeyed: and the terror of God was upon the cities that were round about them, and they did not pursue after the sons of Jacob. |
6 ያዕቆብም፥ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሎዛ መጡ እርስዋም ቤቴል ናት። |
6 So Jacob came to Luz, which is in the land of Canaan, that is, Beth–el, he and all the people that were with him. |
7 በዚያም መሰውያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም ኤልቤቴል ብሎ ጠራው እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና። |
7 And he built there an altar, and called the place El–beth–el: because there God appeared unto him, when he fled from the face of his brother. |
8 የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፥ በቤቴልም ከአድባር ዛፍ በታች ተቀበረች ስሙም አሎንባኩት ተብሎ ተጠራ። |
8 But Deborah Rebekah’s nurse died, and she was buried beneath Beth–el under an oak: and the name of it was called Allon–bachuth. |
9 እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርያ ከተመለሰ በኋላ እንደ ገና ተገለጠለት፥ ባረከውም። |
9 And God appeared unto Jacob again, when he came out of Padan–aram, and blessed him. |
10 እግዚአብሔርም፦ ስምህ ያዕቆብ ነው ከእንግዲህም ወዲህ ስምህ ያዕቆብ ተብሎ አይጠራ፥ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ አለ ስሙንም እስራኤል ብሎ ጠራው። |
10 And God said unto him, Thy name is Jacob: thy name shall not be called any more Jacob, but Israel shall be thy name: and he called his name Israel. |
11 እግዚአብሔርም አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ፥ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ። |
11 And God said unto him, I am God Almighty: be fruitful and multiply; a nation and a company of nations shall be of thee, and kings shall come out of thy loins; |
12 ለአብርሃምና ለይስሐቅም የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፥ ከአንተም በኋላ ለዘርህ ምድሪቱን እሰጣለሁ። |
12 And the land which I gave Abraham and Isaac, to thee I will give it, and to thy seed after thee will I give the land. |
13 እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። |
13 And God went up from him in the place where he talked with him. |
14 ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ ዘይትንም አፈሰሰበት። |
14 And Jacob set up a pillar in the place where he talked with him, even a pillar of stone: and he poured a drink offering thereon, and he poured oil thereon. |
15 ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ያን ቦታ ቤቴል ብሎ ጠራው። |
15 And Jacob called the name of the place where God spake with him, Beth–el. |
16 ከቤቴልም ተነሡ ወደ ኤፍራታም ሊደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፥ በምጡም ተጨነቀች። |
16 And they journeyed from Beth–el; and there was but a little way to come to Ephrath: and Rachel travailed, and she had hard labour. |
17 ምጡም ባስጨነቃት ጊዜ አዋላጂቱ። አትፍሪ፥ ይኸኛው ደግሞ ወንድ ልጅ ይሆንሻልና አለቻት። |
17 And it came to pass, when she was in hard labour, that the midwife said unto her, Fear not; thou shalt have this son also. |
18 እርስዋም ስትሞት ነፍስዋ በምትወጣበት ጊዜ ስሙን ቤንኦኒ ብላ ጠራችው አባቱ ግን ብንያም አለው። |
18 And it came to pass, as her soul was in departing, (for she died) that she called his name Ben–oni: but his father called him Benjamin. |
19 ራሔልም ሞተች፥ ወደ ኤፍራታ በምትወስድም መንገድ ተቀበረች እርስዋም ቤተልሔም ናት። |
19 And Rachel died, and was buried in the way to Ephrath, which is Beth–lehem. |
20 ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው። |
20 And Jacob set a pillar upon her grave: that is the pillar of Rachel’s grave unto this day. |
21 እስራኤልም ከዚያ ተነሣ፥ ድንኳኑንም ከጋዴር ግንብ በስተ ወዲያ ተከለ። |
21 And Israel journeyed, and spread his tent beyond the tower of Edar. |
22 እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው |
22 And it came to pass, when Israel dwelt in that land, that Reuben went and lay with Bilhah his father’s concubine: and Israel heard it. Now the sons of Jacob were twelve: |
23 የልያ ልጆች የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን |
23 The sons of Leah; Reuben, Jacob’s firstborn, and Simeon, and Levi, and Judah, and Issachar, and Zebulun: |
24-25 የራሔል ልጆች ዮሴፍ፥ ብንያም የራሔል ባርያ የባላ ልጆችም ዳን፥ ንፍታሌም |
24 The sons of Rachel; Joseph, and Benjamin: |
26 የልያ ባሪያ የዘለፋ ልጆችም ጋድ፥ አሴር እነዚህ በሁለቱ ወንዞች መካከል በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው። |
26 And the sons of Zilpah, Leah’s handmaid; Gad, and Asher: these are the sons of Jacob, which were born to him in Padan–aram. |
27 ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት ወደ መምሬ ወደ ቂርያትአርባቅ እርስዋም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ። |
27 And Jacob came unto Isaac his father unto Mamre, unto the city of Arbah, which is Hebron, where Abraham and Isaac sojourned. |
28 የይስሐቅም ዕድሜ መቶ ሰማንያ ዓመት ሆነ። |
28 And the days of Isaac were an hundred and fourscore years. |
29 ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠ፥ ሞተም ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት። |
29 And Isaac gave up the ghost, and died, and was gathered unto his people, being old and full of days: and his sons Esau and Jacob buried him. |