ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #39
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 39

Gen 39

1 ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው።

1 And Joseph was brought down to Egypt; and Potiphar, an officer of Pharaoh, captain of the guard, an Egyptian, bought him of the hands of the Ishmeelites, which had brought him down thither.

2 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ።

2 And the Lord was with Joseph, and he was a prosperous man; and he was in the house of his master the Egyptian.

3 ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።

3 And his master saw that the Lord was with him, and that the Lord made all that he did to prosper in his hand.

4 ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ፥ እርሱንም ያገለግለው ነበር በቤቱም ላይ ሾመው፥ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።

4 And Joseph found grace in his sight, and he served him: and he made him overseer over his house, and all that he had he put into his hand.

5 እንዲህም ሆነ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።

5 And it came to pass from the time that he had made him overseer in his house, and over all that he had, that the Lord blessed the Egyptian’s house for Joseph’s sake; and the blessing of the Lord was upon all that he had in the house, and in the field.

6 ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ።

6 And he left all that he had in Joseph’s hand; and he knew not ought he had, save the bread which he did eat. And Joseph was a goodly person, and well favoured.

7 ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይንዋን ጣለች። ከእኔም ጋር ተኛ አለችው።

7 And it came to pass after these things, that his master’s wife cast her eyes upon Joseph; and she said, Lie with me.

8 እርሱም እንቢ አለ፥ ለጌታውም ሚስት እንዲህ አላት፦ እነሆ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፥ ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል

8 But he refused, and said unto his master’s wife, Behold, my master wotteth not what is with me in the house, and he hath committed all that he hath to my hand;

9 ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም ሚስቱ ስለ ሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?

9 There is none greater in this house than I; neither hath he kept back any thing from me but thee, because thou art his wife: how then can I do this great wickedness, and sin against God?

10 ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር እርሱም ከእርስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።

10 And it came to pass, as she spake to Joseph day by day, that he hearkened not unto her, to lie by her, or to be with her.

11 እንዲህም ሆነ በዚያን ጊዜ ሥራውን እንዲሠራ ወደ ቤቱ ገባ በቤትም ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም አልነበረም።

11 And it came to pass about this time, that Joseph went into the house to do his business; and there was none of the men of the house there within.

12 ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ።

12 And she caught him by his garment, saying, Lie with me: and he left his garment in her hand, and fled, and got him out.

13 እንዲህም ሆነ ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ ባየች ጊዜ፥

13 And it came to pass, when she saw that he had left his garment in her hand, and was fled forth,

14 የቤትዋን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው። እዩ ዕብራዊው ሰው በእኛ እንዲሣለቅ አግብቶብናል እርሱ ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ፥ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ

14 That she called unto the men of her house, and spake unto them, saying, See, he hath brought in an Hebrew unto us to mock us; he came in unto me to lie with me, and I cried with a loud voice:

15 ድምፄንም ከፍ አድርጌ እንደ ጮኽሁ ቢሰማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ።

15 And it came to pass, when he heard that I lifted up my voice and cried, that he left his garment with me, and fled, and got him out.

16 ጌታው ወደ ቤቱ እስኪገባ ድረስም ልብሱን ከእርስዋ ዘንድ አኖረች።

16 And she laid up his garment by her, until his lord came home.

17 ይህንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው። ያገባህልን ዕብራዊው ባሪያ ሊሣለቅብኝ ወደ እኔ ገባ

17 And she spake unto him according to these words, saying, The Hebrew servant, which thou hast brought unto us, came in unto me to mock me:

18 እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ።

18 And it came to pass, as I lifted up my voice and cried, that he left his garment with me, and fled out.

19 ጌታውም። ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ ብላ የነገረችውን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ።

19 And it came to pass, when his master heard the words of his wife, which she spake unto him, saying, After this manner did thy servant to me; that his wrath was kindled.

20 የዮሴፍም ጌታ ወሰደው፥ የንጉሡ እስረኞችም ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤት አገባው ከዚያም በግዞት ነበረ።

20 And Joseph’s master took him, and put him into the prison, a place where the king’s prisoners were bound: and he was there in the prison.

21 እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው።

21 But the Lord was with Joseph, and shewed him mercy, and gave him favour in the sight of the keeper of the prison.

22 የግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ።

22 And the keeper of the prison committed to Joseph’s hand all the prisoners that were in the prison; and whatsoever they did there, he was the doer of it.

23 የግዞት ቤቱም አለቃ በእጁ ያለውን ነገር ከቶ አላሰበም፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር።

23 The keeper of the prison looked not to any thing that was under his hand; because the Lord was with him, and that which he did, the Lord made it to prosper.