ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #27
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 27

Leviticus 27

1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ማናቸውም ሰው ሰውን ለእግዚአብሔር ሊሰጥ ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰው ዋጋውን ይስጥ።

2 Speak unto the children of Israel, and say unto them, When a man shall make a singular vow, the persons shall be for the Lord by thy estimation.

3 ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ሰቅል ይሁን።

3 And thy estimation shall be of the male from twenty years old even unto sixty years old, even thy estimation shall be fifty shekels of silver, after the shekel of the sanctuary.

4 ሴትም ብትሆን ግምትዋ ሠላሳ ሰቅል ይሁን።

4 And if it be a female, then thy estimation shall be thirty shekels.

5 ከአምስት ዓመትም ጀምሮ እስከ ሀያ ዓመት ድረስ ግምቱ ለወንድ ሀያ ሰቅል፥ ለሴትም አሥር ሰቅል ይሁን።

5 And if it be from five years old even unto twenty years old, then thy estimation shall be of the male twenty shekels, and for the female ten shekels.

6 ከአንድ ወርም እስከ አምስት ዓመት ድረስ ለወንድ ግምቱ አምስት የብር ሰቅል፥ ለሴትም ግምትዋ ሦስት የብር ሰቅል ይሁን።

6 And if it be from a month old even unto five years old, then thy estimation shall be of the male five shekels of silver, and for the female thy estimation shall be three shekels of silver.

7 ከስድሳ ዓመትም ጀምሮ ከዚያም በላይ ወንድ ቢሆን ግምቱ አሥራ አምስት ሰቅል፥ ለሴትም አሥር ሰቅል ይሁን።

7 And if it be from sixty years old and above; if it be a male, then thy estimation shall be fifteen shekels, and for the female ten shekels.

8 ለግምቱም የሚከፍለውን ቢያጣ ግን በካህኑ ፊት ይቁም፥ ካህኑም የተሳለውን ሰው ይገምተው ካህኑም የተሳለው ሰው እንደሚችል መጠን ይገምተው።

8 But if he be poorer than thy estimation, then he shall present himself before the priest, and the priest shall value him; according to his ability that vowed shall the priest value him.

9 ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።

9 And if it be a beast, whereof men bring an offering unto the Lord, all that any man giveth of such unto the Lord shall be holy.

10 መልካሙን በክፉ፥ ክፉውንም በመልካም አይለውጥ እንስሳንም በእንስሳ ቢለውጥ እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ።

10 He shall not alter it, nor change it, a good for a bad, or a bad for a good: and if he shall at all change beast for beast, then it and the exchange thereof shall be holy.

11 እንስሳው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት መሆን የማይገባው ርኩስ ቢሆን፥ እንስሳውን በካህኑ ፊት ያኑረው።

11 And if it be any unclean beast, of which they do not offer a sacrifice unto the Lord, then he shall present the beast before the priest:

12 መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ካህኑ ይገምተው ካህኑም እነሚገምተው መጠን እንዲሁ ይሁን።

12 And the priest shall value it, whether it be good or bad: as thou valuest it, who art the priest, so shall it be.

13 ይቤዠውም ዘንድ ቢወድድ ከግምቱ በላይ አምስተኛ ይጨምር።

13 But if he will at all redeem it, then he shall add a fifth part thereof unto thy estimation.

14 ሰውም ለእግዚአብሔር ቅዱስ ይሆን ዘንድ ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም ክፉ እንደ ሆነ ይገምተዋል ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይቆማል።

14 And when a man shall sanctify his house to be holy unto the Lord, then the priest shall estimate it, whether it be good or bad: as the priest shall estimate it, so shall it stand.

15 የቀደሰውም ሰው ቤቱን ይቤዠው ዘንድ ቢወድድ ከግምቱ ገንዘብ በላይ አምስተኛ ይጨምር ቤቱም ለእርሱ ይሆናል።

15 And if he that sanctified it will redeem his house, then he shall add the fifth part of the money of thy estimation unto it, and it shall be his.

16 ሰውም ከርስቱ እርሻ ለእግዚአብሔር ቢቀድስ፥ እንደ መዘራቱ መጠን ይገመት አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የሚዘራበት እርሻ አምሳ የብር ሰቅል ይገመታል።

16 And if a man shall sanctify unto the Lord some part of a field of his possession, then thy estimation shall be according to the seed thereof: an homer of barley seed shall be valued at fifty shekels of silver.

17 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢቀድስ፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆማል።

17 If he sanctify his field from the year of jubile, according to thy estimation it shall stand.

18 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ገንዘቡን ይቈጥርለታል ከግምቱም ይጐድላል።

18 But if he sanctify his field after the jubile, then the priest shall reckon unto him the money according to the years that remain, even unto the year of the jubile, and it shall be abated from thy estimation.

19 እርሻውንም የቀደሰ ሰው ይቤዠው ዘንድ ቢወድድ፥ ከግምቱ ገንዘብ በላይ አምስተኛ ይጨምር ለእርሱም ይሆናል።

19 And if he that sanctified the field will in any wise redeem it, then he shall add the fifth part of the money of thy estimation unto it, and it shall be assured to him.

20 እርሻውንም ባይቤዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ፥ እንደገና ይቤዠው ዘንድ አይቻለውም።

20 And if he will not redeem the field, or if he have sold the field to another man, it shall not be redeemed any more.

21 እርሻው ግን በኢዮቤልዩ ሲወጣ እንደ እርም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ እርሻ ይሆናል ርስቱ ለካህኑ ይሆናል።

21 But the field, when it goeth out in the jubile, shall be holy unto the Lord, as a field devoted; the possession thereof shall be the priest’s.

22 ከርስቱ እርሻ ያልሆነውን የገዛውን እርሻ ለእግዚአብሔር ቢቀድስ፥

22 And if a man sanctify unto the Lord a field which he hath bought, which is not of the fields of his possession;

23 ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የግምቱን ዋጋ ይቈጥርለታል በዚያም ቀን ግምቱን እንደ ተቀደሰ ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጣል።

23 Then the priest shall reckon unto him the worth of thy estimation, even unto the year of the jubile: and he shall give thine estimation in that day, as a holy thing unto the Lord.

24 በኢዮቤልዩ ዓመት እርሻው የምድሪቱ ባለ ርስት ወደ ነበረው ወደ ሸጠው ሰው ይመለሳል።

24 In the year of the jubile the field shall return unto him of whom it was bought, even to him to whom the possession of the land did belong.

25 ግምቱም ሁሉ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ይሆናል ሰቅሉ ሀያ አቦሊ ይሆናል።

25 And all thy estimations shall be according to the shekel of the sanctuary: twenty gerahs shall be the shekel.

26 ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን የእንስሳ በኵራት ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።

26 Only the firstling of the beasts, which should be the Lord’s firstling, no man shall sanctify it; whether it be ox, or sheep: it is the Lord’s.

27 የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤዠው፥ በእርሱም የዋጋውን አምስተኛ ይጨምርበታል ባይቤዠውም እንደ ግምቱ ይሸጣል።

27 And if it be of an unclean beast, then he shall redeem it according to thine estimation, and shall add a fifth part of it thereto: or if it be not redeemed, then it shall be sold according to thy estimation.

28 ለእግዚአብሔርም የተለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፥ አይቤዥም እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።

28 Notwithstanding no devoted thing, that a man shall devote unto the Lord of all that he hath, both of man and beast, and of the field of his possession, shall be sold or redeemed: every devoted thing is most holy unto the Lord.

29 ከሰዎችም እርም የሆነ ሁሉ አይቤዥም ፈጽሞ ይገደላል።

29 None devoted, which shall be devoted of men, shall be redeemed; but shall surely be put to death.

30 የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።

30 And all the tithe of the land, whether of the seed of the land, or of the fruit of the tree, is the Lord’s: it is holy unto the Lord.

31 ሰውም አሥራቱን ሊቤዥ ቢወድድ፥ አምስተኛ ይጨምርበታል።

31 And if a man will at all redeem ought of his tithes, he shall add thereto the fifth part thereof.

32 ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።

32 And concerning the tithe of the herd, or of the flock, even of whatsoever passeth under the rod, the tenth shall be holy unto the Lord.

33 መልካም ወይም ክፉ እንዲሆን አይመርምር፥ አይለውጥም ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ አይቤዠውም።

33 He shall not search whether it be good or bad, neither shall he change it: and if he change it at all, then both it and the change thereof shall be holy; it shall not be redeemed.

34 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለእስራኤል ልጆች ሙሴን ያዘዘው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።

34 These are the commandments, which the Lord commanded Moses for the children of Israel in mount Sinai.