ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #26
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘሌዋውያን 26 |
Leviticus 26 |
1 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ። |
1 Ye shall make you no idols nor graven image, neither rear you up a standing image, neither shall ye set up any image of stone in your land, to bow down unto it: for I am the Lord your God. |
2 ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም ፍሩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
2 Ye shall keep my sabbaths, and reverence my sanctuary: I am the Lord. |
3 በሥርዓቴ ብትሄዱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም፥ |
3 If ye walk in my statutes, and keep my commandments, and do them; |
4 ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም እህልዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ። |
4 Then I will give you rain in due season, and the land shall yield her increase, and the trees of the field shall yield their fruit. |
5 የእህሉም ማበራየት በእናንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቍረጥ ይደርሳል፥ የወይኑም መቍረጥ እስከ እህሉ መዝራት ይደርሳል እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በጸጥታ ትኖራላችሁ። |
5 And your threshing shall reach unto the vintage, and the vintage shall reach unto the sowing time: and ye shall eat your bread to the full, and dwell in your land safely. |
6 በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም። |
6 And I will give peace in the land, and ye shall lie down, and none shall make you afraid: and I will rid evil beasts out of the land, neither shall the sword go through your land. |
7 ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። |
7 And ye shall chase your enemies, and they shall fall before you by the sword. |
8 ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም አሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። |
8 And five of you shall chase an hundred, and an hundred of you shall put ten thousand to flight: and your enemies shall fall before you by the sword. |
9 ፊቴም ወደ እናንተ ይሆናል፥ እንድታፈሩም አደርጋችኋለሁ፥ አበዛችሁማለሁ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ። |
9 For I will have respect unto you, and make you fruitful, and multiply you, and establish my covenant with you. |
10 ብዙ ጊዜ የተቀመጠውንም አሮጌውን እህል ትበላላችሁ ከአዲሱም በፊት አሮጌውን ታወጣላችሁ። |
10 And ye shall eat old store, and bring forth the old because of the new. |
11 ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ ነፍሴም አትጸየፋችሁም። |
11 And I will set my tabernacle among you: and my soul shall not abhor you. |
12 በመካከላችሁም እሄዳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። |
12 And I will walk among you, and will be your God, and ye shall be my people. |
13 ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ። |
13 I am the Lord your God, which brought you forth out of the land of Egypt, that ye should not be their bondmen; and I have broken the bands of your yoke, and made you go upright. |
14 ነገር ግን ባትሰሙኝ፥ እነዚህንም ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ |
14 But if ye will not hearken unto me, and will not do all these commandments; |
15 ሥርዓቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ነፍሳችሁ ፍርዴን ብትጸየፍ፥ |
15 And if ye shall despise my statutes, or if your soul abhor my judgments, so that ye will not do all my commandments, but that ye break my covenant: |
16 እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ ፍርሃትን፥ ክሳትንም፥ ዓይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፥ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና። |
16 I also will do this unto you; I will even appoint over you terror, consumption, and the burning ague, that shall consume the eyes, and cause sorrow of heart: and ye shall sow your seed in vain, for your enemies shall eat it. |
17 ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፥ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ። |
17 And I will set my face against you, and ye shall be slain before your enemies: they that hate you shall reign over you; and ye shall flee when none pursueth you. |
18 እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ ስለ ኃጢአታችሁ በቅጣታችሁ ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ። |
18 And if ye will not yet for all this hearken unto me, then I will punish you seven times more for your sins. |
19 የኃይላችሁንም ትዕቢት እሰብራለሁ ሰማያችሁንም እንደ ብረት፥ ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ። |
19 And I will break the pride of your power; and I will make your heaven as iron, and your earth as brass: |
20 ጕልበታችሁም በከንቱ ያልቃል ምድራችሁም እህልዋን አትሰጥም፥ የምድርም ዛፎች ፍሬአቸውን አይሰጡም። |
20 And your strength shall be spent in vain: for your land shall not yield her increase, neither shall the trees of the land yield their fruits. |
21 በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ ባትሰሙኝም፥ እንደ ኃጢአታችሁ መጠን በመቅሠፍት ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ። |
21 And if ye walk contrary unto me, and will not hearken unto me; I will bring seven times more plagues upon you according to your sins. |
22 በመካከላችሁም የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ ልጆቻችሁንም ይነጥቃሉ፥ እንስሶቻችሁንም ያጠፋሉ፥ እናንተንም ያሳንሳሉ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ። |
22 I will also send wild beasts among you, which shall rob you of your children, and destroy your cattle, and make you few in number; and your high ways shall be desolate. |
23 እስከዚህም ድረስ ባትቀጡ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱ፥ |
23 And if ye will not be reformed by me by these things, but will walk contrary unto me; |
24 እኔ ደግሞ በእንቢተኝነት እሄድባችኋለሁ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። |
24 Then will I also walk contrary unto you, and will punish you yet seven times for your sins. |
25 የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ ወደ ከተማችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ በጠላትም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ። |
25 And I will bring a sword upon you, that shall avenge the quarrel of my covenant: and when ye are gathered together within your cities, I will send the pestilence among you; and ye shall be delivered into the hand of the enemy. |
26 የእህላችሁንም ድጋፍ በሰበርሁ ጊዜ፥ አሥር ሴቶች እንጀራቸውን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው እንጀራችሁን ይመልሱላችኋል በበላችሁም ጊዜ አትጠግቡም። |
26 And when I have broken the staff of your bread, ten women shall bake your bread in one oven, and they shall deliver you your bread again by weight: and ye shall eat, and not be satisfied. |
27 እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ፥ |
27 And if ye will not for all this hearken unto me, but walk contrary unto me; |
28 እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። |
28 Then I will walk contrary unto you also in fury; and I, even I, will chastise you seven times for your sins. |
29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። |
29 And ye shall eat the flesh of your sons, and the flesh of your daughters shall ye eat. |
30 የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። |
30 And I will destroy your high places, and cut down your images, and cast your carcases upon the carcases of your idols, and my soul shall abhor you. |
31 ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፥ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ መልካሙንም መዓዛችሁን አላሸትትም። |
31 And I will make your cities waste, and bring your sanctuaries unto desolation, and I will not smell the savour of your sweet odours. |
32 ምድሪቱንም የተፈታች አደርጋለሁ የሚቀመጡባት ጠላቶቻችሁም በእርስዋ የተነሣ ይደነቃሉ። |
32 And I will bring the land into desolation: and your enemies which dwell therein shall be astonished at it. |
33 እናንተንም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ። |
33 And I will scatter you among the heathen, and will draw out a sword after you: and your land shall be desolate, and your cities waste. |
34 በዚያም በተፈታችበት ዘመን ሁሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር ሳላችሁ፥ ምድሪቱ ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች በዚያም ጊዜ ምድሪቱ ታርፋለች፥ ሰንበትንም በማድረግዋ ትደሰታለች። |
34 Then shall the land enjoy her sabbaths, as long as it lieth desolate, and ye be in your enemies’ land; even then shall the land rest, and enjoy her sabbaths. |
35 እናንተ ተቀምጣችሁባት በነበረ ጊዜ በሰንበቶቻችሁ አላረፈችም ነበርና በተፈታችበት ዘመን ሁሉ ታርፋለች። |
35 As long as it lieth desolate it shall rest; because it did not rest in your sabbaths, when ye dwelt upon it. |
36 በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ። |
36 And upon them that are left alive of you I will send a faintness into their hearts in the lands of their enemies; and the sound of a shaken leaf shall chase them; and they shall flee, as fleeing from a sword; and they shall fall when none pursueth. |
37 ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንዲሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም። |
37 And they shall fall one upon another, as it were before a sword, when none pursueth: and ye shall have no power to stand before your enemies. |
38 በአሕዛብም መካከል ታልቃላችሁ፥ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። |
38 And ye shall perish among the heathen, and the land of your enemies shall eat you up. |
39 ከእናንተም ተለይተው የቀሩት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይከሳሉ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይከሳሉ። |
39 And they that are left of you shall pine away in their iniquity in your enemies’ lands; and also in the iniquities of their fathers shall they pine away with them. |
40 በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ። |
40 If they shall confess their iniquity, and the iniquity of their fathers, with their trespass which they trespassed against me, and that also they have walked contrary unto me; |
41 እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ |
41 And that I also have walked contrary unto them, and have brought them into the land of their enemies; if then their uncircumcised hearts be humbled, and they then accept of the punishment of their iniquity: |
42 እኔ ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ ደግሞ ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ ምድሪቱንም አስባለሁ። |
42 Then will I remember my covenant with Jacob, and also my covenant with Isaac, and also my covenant with Abraham will I remember; and I will remember the land. |
43 ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የኃጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ። |
43 The land also shall be left of them, and shall enjoy her sabbaths, while she lieth desolate without them: and they shall accept of the punishment of their iniquity: because, even because they despised my judgments, and because their soul abhorred my statutes. |
44 ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝኛ እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም። |
44 And yet for all that, when they be in the land of their enemies, I will not cast them away, neither will I abhor them, to destroy them utterly, and to break my covenant with them: for I am the Lord their God. |
45 እኔ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸውን የአባቶቻቸውን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስባለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
45 But I will for their sakes remember the covenant of their ancestors, whom I brought forth out of the land of Egypt in the sight of the heathen, that I might be their God: I am the Lord. |
46 እግዚአብሔርም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ ያደረጋቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው። |
46 These are the statutes and judgments and laws, which the Lord made between him and the children of Israel in mount Sinai by the hand of Moses. |