ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #10
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 10

Numbers 10

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።

2 Make thee two trumpets of silver; of a whole piece shalt thou make them: that thou mayest use them for the calling of the assembly, and for the journeying of the camps.

3 ሁለቱም መለከቶች በተነፉ ጊዜ ማኅበሩ ሁሉ ወደ አንተ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይሰብሰቡ።

3 And when they shall blow with them, all the assembly shall assemble themselves to thee at the door of the tabernacle of the congregation.

4 አንድ መለከት ሲነፋ ታላላቆቹ የእስራኤል አእላፍ አለቆች ወደ አንተ ይሰብሰቡ።

4 And if they blow but with one trumpet, then the princes, which are heads of the thousands of Israel, shall gather themselves unto thee.

5 መለከትንም ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በምሥራቅ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ።

5 When ye blow an alarm, then the camps that lie on the east parts shall go forward.

6 ሁለተኛውንም ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ ለማስጓዝ መለከትን ይነፋሉ።

6 When ye blow an alarm the second time, then the camps that lie on the south side shall take their journey: they shall blow an alarm for their journeys.

7 ጉባኤውም በሚሰበሰብበት ጊዜ ንፉ፥ ነገር ግን ድምፁን ከፍ አታድርጉት።

7 But when the congregation is to be gathered together, ye shall blow, but ye shall not sound an alarm.

8 የአሮንም ልጆች ካህናቱ መለከቶቹን ይንፉ እነርሱም ለልጅ ልጃችሁ ለዘላለም ሥርዓት ይሁኑ።

8 And the sons of Aaron, the priests, shall blow with the trumpets; and they shall be to you for an ordinance for ever throughout your generations.

9 በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ መለከቶቹን ንፉ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ።

9 And if ye go to war in your land against the enemy that oppresseth you, then ye shall blow an alarm with the trumpets; and ye shall be remembered before the Lord your God, and ye shall be saved from your enemies.

10 ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ በወርም መባቻ፥ በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

10 Also in the day of your gladness, and in your solemn days, and in the beginnings of your months, ye shall blow with the trumpets over your burnt offerings, and over the sacrifices of your peace offerings; that they may be to you for a memorial before your God: I am the Lord your God.

11 በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ።

11 And it came to pass on the twentieth day of the second month, in the second year, that the cloud was taken up from off the tabernacle of the testimony.

12 የእስራኤልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየጕዞአቸው ተጓዙ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ቆመ።

12 And the children of Israel took their journeys out of the wilderness of Sinai; and the cloud rested in the wilderness of Paran.

13 በመጀመሪያም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ተጓዙ።

13 And they first took their journey according to the commandment of the Lord by the hand of Moses.

14 በመጀመሪያም የይሁዳ ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ በሠራዊቱም ላይ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን አለቃ ነበረ።

14 In the first place went the standard of the camp of the children of Judah according to their armies: and over his host was Nahshon the son of Amminadab.

15 በይሳኮርም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የሶገር ልጅ ናትናኤል አለቃ ነበረ።

15 And over the host of the tribe of the children of Issachar was Nethaneel the son of Zuar.

16 በዛብሎንም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የኬሎን ልጅ ኤልያብ አለቃ ነበረ።

16 And over the host of the tribe of the children of Zebulun was Eliab the son of Helon.

17 ማደሪያውም ተነቀለ ማደሪያውንም የተሸከሙ የጌድሶን ልጆችና የሜራሪ ልጆች ተጓዙ።

17 And the tabernacle was taken down; and the sons of Gershon and the sons of Merari set forward, bearing the tabernacle.

18 የሮቤልም ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ።

18 And the standard of the camp of Reuben set forward according to their armies: and over his host was Elizur the son of Shedeur.

19 በስምዖንም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል አለቃ ነበረ።

19 And over the host of the tribe of the children of Simeon was Shelumiel the son of Zurishaddai.

20 በጋድም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ አለቃ ነበረ።

20 And over the host of the tribe of the children of Gad was Eliasaph the son of Deuel.

21 ቀዓታውያንም መቅደሱን ተሸክመው ተጓዙ እነዚህም እስኪመጡ ድረስ እነዚያ ማደሪያውን ተከሉ።

21 And the Kohathites set forward, bearing the sanctuary: and the other did set up the tabernacle against they came.

22 የኤፍሬምም ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ በሠራዊቱም ላይ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አለቃ ነበረ።

22 And the standard of the camp of the children of Ephraim set forward according to their armies: and over his host was Elishama the son of Ammihud.

23 በምናሴም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል አለቃ ነበረ።

23 And over the host of the tribe of the children of Manasseh was Gamaliel the son of Pedahzur.

24 በብንያምም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን አለቃ ነበረ።

24 And over the host of the tribe of the children of Benjamin was Abidan the son of Gideoni.

25 ከሰፈሮቹ ሁሉ በኋላ የሆነ የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ።

25 And the standard of the camp of the children of Dan set forward, which was the rereward of all the camps throughout their hosts: and over his host was Ahiezer the son of Ammishaddai.

26 በአሴርም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የኤክራን ልጅ ፋግኤል አለቃ ነበረ።

26 And over the host of the tribe of the children of Asher was Pagiel the son of Ocran.

27 በንፍታሌምም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የዔናን ልጅ አኪሬ አለቃ ነበረ።

27 And over the host of the tribe of the children of Naphtali was Ahira the son of Enan.

28 እንዲሁ የእስራኤል ልጆች ጕዞ በየሠራዊታቸው ነበረ እነርሱም ተጓዙ።

28 Thus were the journeyings of the children of Israel according to their armies, when they set forward.

29 ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው።

29 And Moses said unto Hobab, the son of Raguel the Midianite, Moses’ father in law, We are journeying unto the place of which the Lord said, I will give it you: come thou with us, and we will do thee good: for the Lord hath spoken good concerning Israel.

30 እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው።

30 And he said unto him, I will not go; but I will depart to mine own land, and to my kindred.

31 እርሱም፦ እባክህ፥ በምድረ በዳ የምንሰፍርበትን አንተ ታውቃለህና፥ እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወን

31 And he said, Leave us not, I pray thee; forasmuch as thou knowest how we are to encamp in the wilderness, and thou mayest be to us instead of eyes.

32 ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን አለ።

32 And it shall be, if thou go with us, yea, it shall be, that what goodness the Lord shall do unto us, the same will we do unto thee.

33 ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው።

33 And they departed from the mount of the Lord three days’ journey: and the ark of the covenant of the Lord went before them in the three days’ journey, to search out a resting place for them.

34 ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን በላያቸው ነበረ።

34 And the cloud of the Lord was upon them by day, when they went out of the camp.

35 ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ። አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር።

35 And it came to pass, when the ark set forward, that Moses said, Rise up, Lord, and let thine enemies be scattered; and let them that hate thee flee before thee.

36 ባረፈም ጊዜ። አቤቱ፥ ወደ እስራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ ይል ነበር።

36 And when it rested, he said, Return, O Lord, unto the many thousands of Israel.