መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #24
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 24 |
Psalm 24 |
1 ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። |
1 The earth is the Lord’s, and the fulness thereof; the world, and they that dwell therein. |
2 እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም አጽንቶአታልና። |
2 For he hath founded it upon the seas, and established it upon the floods. |
3 ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? |
3 Who shall ascend into the hill of the Lord? or who shall stand in his holy place? |
4 እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። |
4 He that hath clean hands, and a pure heart; who hath not lifted up his soul unto vanity, nor sworn deceitfully. |
5 እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል። |
5 He shall receive the blessing from the Lord, and righteousness from the God of his salvation. |
6 ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ። |
6 This is the generation of them that seek him, that seek thy face, O Jacob. Selah. |
7 እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ። |
7 Lift up your heads, O ye gates; and be ye lift up, ye everlasting doors; and the King of glory shall come in. |
8 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል። |
8 Who is this King of glory? The Lord strong and mighty, the Lord mighty in battle. |
9 እናንተ መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ። |
9 Lift up your heads, O ye gates; even lift them up, ye everlasting doors; and the King of glory shall come in. |
10 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው። |
10 Who is this King of glory? The Lord of hosts, he is the King of glory. Selah. |