መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #25
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 25 |
Psalm 25 |
1 አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ። |
1 Unto thee, O Lord, do I lift up my soul. |
2 አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ። |
2 O my God, I trust in thee: let me not be ashamed, let not mine enemies triumph over me. |
3 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ። |
3 Yea, let none that wait on thee be ashamed: let them be ashamed which transgress without cause. |
4 አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ። |
4 Shew me thy ways, O Lord; teach me thy paths. |
5 አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ። |
5 Lead me in thy truth, and teach me: for thou art the God of my salvation; on thee do I wait all the day. |
6 አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና። |
6 Remember, O Lord, thy tender mercies and thy lovingkindnesses; for they have been ever of old. |
7 የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ። |
7 Remember not the sins of my youth, nor my transgressions: according to thy mercy remember thou me for thy goodness’ sake, O Lord. |
8 እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል። |
8 Good and upright is the Lord: therefore will he teach sinners in the way. |
9 ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል። |
9 The meek will he guide in judgment: and the meek will he teach his way. |
10 የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ። |
10 All the paths of the Lord are mercy and truth unto such as keep his covenant and his testimonies. |
11 አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ። |
11 For thy name’s sake, O Lord, pardon mine iniquity; for it is great. |
12 እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል። |
12 What man is he that feareth the Lord? him shall he teach in the way that he shall choose. |
13 ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል። |
13 His soul shall dwell at ease; and his seed shall inherit the earth. |
14 እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል። |
14 The secret of the Lord is with them that fear him; and he will shew them his covenant. |
15 እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው። |
15 Mine eyes are ever toward the Lord; for he shall pluck my feet out of the net. |
16 እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም። |
16 Turn thee unto me, and have mercy upon me; for I am desolate and afflicted. |
17 የልቤ ችግር ብዙ ነው ከጭንቀቴ አውጣኝ። |
17 The troubles of my heart are enlarged: O bring thou me out of my distresses. |
18 ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ። |
18 Look upon mine affliction and my pain; and forgive all my sins. |
19 ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል። |
19 Consider mine enemies; for they are many; and they hate me with cruel hatred. |
20 ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ አንተን ታምኛለሁና አልፈር። |
20 O keep my soul, and deliver me: let me not be ashamed; for I put my trust in thee. |
21 አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ። |
21 Let integrity and uprightness preserve me; for I wait on thee. |
22 አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው። |
22 Redeem Israel, O God, out of all his troubles. |