ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #33
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 33

Numbers 33

1 የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን እጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ።

1 These are the journeys of the children of Israel, which went forth out of the land of Egypt with their armies under the hand of Moses and Aaron.

2 ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ።

2 And Moses wrote their goings out according to their journeys by the commandment of the Lord: and these are their journeys according to their goings out.

3 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ።

3 And they departed from Rameses in the first month, on the fifteenth day of the first month; on the morrow after the passover the children of Israel went out with an high hand in the sight of all the Egyptians.

4 በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው።

4 For the Egyptians buried all their firstborn, which the Lord had smitten among them: upon their gods also the Lord executed judgments.

5 የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተጕዘው በሱኮት ሰፈሩ።

5 And the children of Israel removed from Rameses, and pitched in Succoth.

6 ከሱኮትም ተጕዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ።

6 And they departed from Succoth, and pitched in Etham, which is in the edge of the wilderness.

7 ከኤታምም ተጕዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ።

7 And they removed from Etham, and turned again unto Pi–hahiroth, which is before Baal–zephon: and they pitched before Migdol.

8 ከፊሀሒሮትም ተጕዘው በባሕሩ ውስጥ ወደ ምድረ በዳ አለፉ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ።

8 And they departed from before Pi–hahiroth, and passed through the midst of the sea into the wilderness, and went three days’ journey in the wilderness of Etham, and pitched in Marah.

9 ከማራም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ በኤሊምም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ በዚያም ሰፈሩ።

9 And they removed from Marah, and came unto Elim: and in Elim were twelve fountains of water, and threescore and ten palm trees; and they pitched there.

10 ከኤሊምም ተጕዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ።

10 And they removed from Elim, and encamped by the Red sea.

11 ከኤርትራም ባሕር ተጕዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ።

11 And they removed from the Red sea, and encamped in the wilderness of Sin.

12 ከሲን ምድረ በዳም ተጕዘው በራፋቃ ሰፈሩ።

12 And they took their journey out of the wilderness of Sin, and encamped in Dophkah.

13 ከራፋቃም ተጕዘው በኤሉስ ሰፈሩ።

13 And they departed from Dophkah, and encamped in Alush.

14 ከኤሉስም ተጕዘው በራፊዲም ሰፈሩ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም።

14 And they removed from Alush, and encamped at Rephidim, where was no water for the people to drink.

15 ከራፊዲምም ተጕዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።

15 And they departed from Rephidim, and pitched in the wilderness of Sinai.

16 ከሲናም ምድረ በዳ ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ።

16 And they removed from the desert of Sinai, and pitched at Kibroth–hattaavah.

17 ከምኞት መቃብርም ተጕዘው በሐጼሮት ሰፈሩ።

17 And they departed from Kibroth–hattaavah, and encamped at Hazeroth.

18 ከሐጼሮትም ተጕዘው በሪትማ ሰፈሩ።

18 And they departed from Hazeroth, and pitched in Rithmah.

19 ከሪትማም ተጕዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ።

19 And they departed from Rithmah, and pitched at Rimmon–parez.

20 ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ።

20 And they departed from Rimmon–parez, and pitched in Libnah.

21 ከልብናም ተጕዘው በሪሳ ሰፈሩ።

21 And they removed from Libnah, and pitched at Rissah.

22 ከሪሳም ተጕዘው በቀሄላታ ሰፈሩ።

22 And they journeyed from Rissah, and pitched in Kehelathah.

23 ከቀሄላታም ተጕዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ።

23 And they went from Kehelathah, and pitched in mount Shapher.

24 ከሻፍር ተራራም ተጕዘው በሐራዳ ሰፈሩ።

24 And they removed from mount Shapher, and encamped in Haradah.

25 ከሐራዳም ተጕዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ።

25 And they removed from Haradah, and pitched in Makheloth.

26 ከመቅሄሎትም ተጕዘው በታሐት ሰፈሩ።

26 And they removed from Makheloth, and encamped at Tahath.

27 ከታሐትም ተጕዘው በታራ ሰፈሩ።

27 And they departed from Tahath, and pitched at Tarah.

28 ከታራም ተጕዘው በሚትቃ ሰፈሩ።

28 And they removed from Tarah, and pitched in Mithcah.

29 ከሚትቃም ተጕዘው በሐሽሞና ሰፈሩ።

29 And they went from Mithcah, and pitched in Hashmonah.

30 ከሐሽሞናም ተጕዘው በሞሴሮት ሰፈሩ።

30 And they departed from Hashmonah, and encamped at Moseroth.

31 ከሞሴሮትም ተጕዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።

31 And they departed from Moseroth, and pitched in Bene–jaakan.

32 ከብኔያዕቃንም ተጕዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።

32 And they removed from Bene–jaakan, and encamped at Hor–hagidgad.

33 ከሖርሃጊድጋድም ተጕዘው በዮጥባታ ሰፈሩ።

33 And they went from Hor–hagidgad, and pitched in Jotbathah.

34 ከዮጥባታም ተጕዘው በዔብሮና ሰፈሩ።

34 And they removed from Jotbathah, and encamped at Ebronah.

35 ከዔብሮናም ተጕዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።

35 And they departed from Ebronah, and encamped at Ezion–gaber.

36 ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ ይህችም ቃዴስ ናት።

36 And they removed from Ezion–gaber, and pitched in the wilderness of Zin, which is Kadesh.

37 ከቃዴስም ተጕዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።

37 And they removed from Kadesh, and pitched in mount Hor, in the edge of the land of Edom.

38 ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

38 And Aaron the priest went up into mount Hor at the commandment of the Lord, and died there, in the fortieth year after the children of Israel were come out of the land of Egypt, in the first day of the fifth month.

39 አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር።

39 And Aaron was an hundred and twenty and three years old when he died in mount Hor.

40 በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ።

40 And king Arad the Canaanite, which dwelt in the south in the land of Canaan, heard of the coming of the children of Israel.

41 እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ።

41 And they departed from mount Hor, and pitched in Zalmonah.

42 ከሴልሞናም ተጕዘው በፉኖን ሰፈሩ።

42 And they departed from Zalmonah, and pitched in Punon.

43 ከፉኖንም ተጕዘው በኦቦት ሰፈሩ።

43 And they departed from Punon, and pitched in Oboth.

44 ከኦቦትም ተጕዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ።

44 And they departed from Oboth, and pitched in Ije–abarim, in the border of Moab.

45 ከጋይም ተጕዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ።

45 And they departed from Iim, and pitched in Dibon–gad.

46 ከዲቦንጋድም ተጕዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ።

46 And they removed from Dibon–gad, and encamped in Almon–diblathaim.

47 ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ።

47 And they removed from Almon–diblathaim, and pitched in the mountains of Abarim, before Nebo.

48 ከዓብሪምም ተራሮች ተጕዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ።

48 And they departed from the mountains of Abarim, and pitched in the plains of Moab by Jordan near Jericho.

49 በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ።

49 And they pitched by Jordan, from Beth–jesimoth even unto Abel–shittim in the plains of Moab.

50 እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው።

50 And the Lord spake unto Moses in the plains of Moab by Jordan near Jericho, saying,

51 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ወደከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥

51 Speak unto the children of Israel, and say unto them, When ye are passed over Jordan into the land of Canaan;

52 የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ

52 Then ye shall drive out all the inhabitants of the land from before you, and destroy all their pictures, and destroy all their molten images, and quite pluck down all their high places:

53 ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም።

53 And ye shall dispossess the inhabitants of the land, and dwell therein: for I have given you the land to possess it.

54 ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።

54 And ye shall divide the land by lot for an inheritance among your families: and to the more ye shall give the more inheritance, and to the fewer ye shall give the less inheritance: every man’s inheritance shall be in the place where his lot falleth; according to the tribes of your fathers ye shall inherit.

55 የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።

55 But if ye will not drive out the inhabitants of the land from before you; then it shall come to pass, that those which ye let remain of them shall be pricks in your eyes, and thorns in your sides, and shall vex you in the land wherein ye dwell.

56 እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።

56 Moreover it shall come to pass, that I shall do unto you, as I thought to do unto them.