ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #34
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 34

Numbers 34

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው። ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ ርስት ትሆናችሁ ዘንድ በዕጣ የምትደርሳችሁ ምድር፥ በዳርቻዋ ያለች የከነዓን ምድር፥

2 Command the children of Israel, and say unto them, When ye come into the land of Canaan; (this is the land that shall fall unto you for an inheritance, even the land of Canaan with the coasts thereof:)

3 ይህች ናት የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤዶምያስ በኩል ይሆናል የደቡቡም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል

3 Then your south quarter shall be from the wilderness of Zin along by the coast of Edom, and your south border shall be the outmost coast of the salt sea eastward:

4 ዳርቻችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ያልፋል መውጫውም በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ይሆናል ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል

4 And your border shall turn from the south to the ascent of Akrabbim, and pass on to Zin: and the going forth thereof shall be from the south to Kadesh–barnea, and shall go on to Hazar–addar, and pass on to Azmon:

5 ዳርቻውም ከዓጽሞን ወደ ግብፅ ወንዝ ይዞራል፥ መውጫውም በባሕሩ በኩል ይሆናል።

5 And the border shall fetch a compass from Azmon unto the river of Egypt, and the goings out of it shall be at the sea.

6 ለምዕራብም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳርቻችሁ ይሆናል ይህ የምዕራብ ዳርቻችሁ ይሆናል።

6 And as for the western border, ye shall even have the great sea for a border: this shall be your west border.

7 የሰሜንም ዳርቻችሁ ይህ ይሆናል ከታላቁ ባሕር ወደ ሖር ተራራ ምልክት ታመለክታላችሁ

7 And this shall be your north border: from the great sea ye shall point out for you mount Hor:

8 ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ ምልክት ታመለክታላችሁ የዳርቻውም መውጫ በጽዳድ ይሆናል

8 From mount Hor ye shall point out your border unto the entrance of Hamath; and the goings forth of the border shall be to Zedad:

9 ዳርቻውም ወደ ዚፍሮን ያልፋል እስከ ሐጸርዔናንም ድረስ ይወጣል ይህ የሰሜን ዳርቻችሁ ይሆናል።

9 And the border shall go on to Ziphron, and the goings out of it shall be at Hazar–enan: this shall be your north border.

10 የምሥራቁንም ዳርቻችሁን ከሐጸርዔናን ወደ ሴፋማ ምልክት ታመለክታላችሁ

10 And ye shall point out your east border from Hazar–enan to Shepham:

11 ዳርቻውም ከሴፋማ በዓይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ ሪብላ ይወርዳል እስከ ኪኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል

11 And the coast shall go down from Shepham to Riblah, on the east side of Ain; and the border shall descend, and shall reach unto the side of the sea of Chinnereth eastward:

12 ዳርቻውም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፥ መውጫውም በጨው ባሕር ይሆናል። ምድራችሁ እንደ ዳርቻዋ በዙሪያዋ ይህች ናት።

12 And the border shall go down to Jordan, and the goings out of it shall be at the salt sea: this shall be your land with the coasts thereof round about.

13 ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው። እግዚአብሔር ለዘጠኝ ነገድ ተኩል ይሰጡአቸው ዘንድ ያዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት

13 And Moses commanded the children of Israel, saying, This is the land which ye shall inherit by lot, which the Lord commanded to give unto the nine tribes, and to the half tribe:

14 የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል።

14 For the tribe of the children of Reuben according to the house of their fathers, and the tribe of the children of Gad according to the house of their fathers, have received their inheritance; and half the tribe of Manasseh have received their inheritance:

15 እነዚህ ሁለቱ ነገድና የአንዱ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ አንጻር በምሥራቅ በኩል ወረሱ።

15 The two tribes and the half tribe have received their inheritance on this side Jordan near Jericho eastward, toward the sunrising.

16 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

16 And the Lord spake unto Moses, saying,

17 ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ።

17 These are the names of the men which shall divide the land unto you: Eleazar the priest, and Joshua the son of Nun.

18 ምድሪቱንም ርስት አድርገው ይከፍሉ ዘንድ ከየነገዱ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ።

18 And ye shall take one prince of every tribe, to divide the land by inheritance.

19 የሰዎቹም ስም ይህ ነው ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፥

19 And the names of the men are these: Of the tribe of Judah, Caleb the son of Jephunneh.

20 ከስምዖን ልጆች ነገድ የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፥

20 And of the tribe of the children of Simeon, Shemuel the son of Ammihud.

21 ከብንያም ነገድ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፥

21 Of the tribe of Benjamin, Elidad the son of Chislon.

22 ከዳን ልጆች ንገድ አንድ አለቃ የዮግሊ ልጅ ቡቂ፥

22 And the prince of the tribe of the children of Dan, Bukki the son of Jogli.

23 ከዮሴፍም ልጆች ከምናሴ ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሱፊድ ልጅ አኒኤል፥

23 The prince of the children of Joseph, for the tribe of the children of Manasseh, Hanniel the son of Ephod.

24 ከኤፍሬም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፥

24 And the prince of the tribe of the children of Ephraim, Kemuel the son of Shiphtan.

25 ከዛብሎን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፥

25 And the prince of the tribe of the children of Zebulun, Elizaphan the son of Parnach.

26 ከይሳኮር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፥

26 And the prince of the tribe of the children of Issachar, Paltiel the son of Azzan.

27 ከአሴር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፥

27 And the prince of the tribe of the children of Asher, Ahihud the son of Shelomi.

28 ከንፍታሌም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል።

28 And the prince of the tribe of the children of Naphtali, Pedahel the son of Ammihud.

29 እግዚአብሔር በከነዓን ምድር ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን ይከፍሉ ዘንድ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።

29 These are they whom the Lord commanded to divide the inheritance unto the children of Israel in the land of Canaan.