ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #19
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘሌዋውያን 19 |
Leviticus 19 |
1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
1 And the Lord spake unto Moses, saying, |
2 ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ። |
2 Speak unto all the congregation of the children of Israel, and say unto them, Ye shall be holy: for I the Lord your God am holy. |
3 ከእናንተ ሰው ሁሉ እናቱንና አባቱን ይፍራ፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
3 Ye shall fear every man his mother, and his father, and keep my sabbaths: I am the Lord your God. |
4 ወደ ጣዖታትም ዘወር አትበሉ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም የአማልክት ምስሎች ለእናንተ አታድርጉ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
4 Turn ye not unto idols, nor make to yourselves molten gods: I am the Lord your God. |
5 የደኅንነትንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሰዉ እርሱን ደስ እንድታሰኙበት ሠዉት። |
5 And if ye offer a sacrifice of peace offerings unto the Lord, ye shall offer it at your own will. |
6 በምትሠዉት ቀንና በነጋው ይበላል እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። |
6 It shall be eaten the same day ye offer it, and on the morrow: and if ought remain until the third day, it shall be burnt in the fire. |
7 በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፥ ደስም አያሰኝም |
7 And if it be eaten at all on the third day, it is abominable; it shall not be accepted. |
8 የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኃጢአቱን ይሸከማል ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። |
8 Therefore every one that eateth it shall bear his iniquity, because he hath profaned the hallowed thing of the Lord: and that soul shall be cut off from among his people. |
9 የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። |
9 And when ye reap the harvest of your land, thou shalt not wholly reap the corners of thy field, neither shalt thou gather the gleanings of thy harvest. |
10 የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
10 And thou shalt not glean thy vineyard, neither shalt thou gather every grape of thy vineyard; thou shalt leave them for the poor and stranger: I am the Lord your God. |
11 አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም እርስ በርሳችሁ ሐሰት አትነጋገሩ። |
11 Ye shall not steal, neither deal falsely, neither lie one to another. |
12 በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ የአምላካችሁንም ስም አታርክሱ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
12 And ye shall not swear by my name falsely, neither shalt thou profane the name of thy God: I am the Lord. |
13 በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ። |
13 Thou shalt not defraud thy neighbour, neither rob him: the wages of him that is hired shall not abide with thee all night until the morning. |
14 ደንቆሮውን አትስደብ፥ በዕውርም ፊት ዕንቅፋት አታድርግ፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
14 Thou shalt not curse the deaf, nor put a stumblingblock before the blind, but shalt fear thy God: I am the Lord. |
15 በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ። |
15 Ye shall do no unrighteousness in judgment: thou shalt not respect the person of the poor, nor honour the person of the mighty: but in righteousness shalt thou judge thy neighbour. |
16 በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት አትዙር በባልንጀራህም ደም ላይ አትቁም እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
16 Thou shalt not go up and down as a talebearer among thy people: neither shalt thou stand against the blood of thy neighbour: I am the Lord. |
17 ወንድምህን በልብህ አትጥላው በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው። |
17 Thou shalt not hate thy brother in thine heart: thou shalt in any wise rebuke thy neighbour, and not suffer sin upon him. |
18 አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
18 Thou shalt not avenge, nor bear any grudge against the children of thy people, but thou shalt love thy neighbour as thyself: I am the Lord. |
19 ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህ ከሌላ ዓይነት ጋር አይደባለቅ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ። |
19 Ye shall keep my statutes. Thou shalt not let thy cattle gender with a diverse kind: thou shalt not sow thy field with mingled seed: neither shall a garment mingled of linen and woollen come upon thee. |
20 ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እርስዋም ለባል የተሰጠች ዋጋዋም ያልተከፈለ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ቅጣት አለባቸው አርነት አልወጣችምና አይገደሉም። |
20 And whosoever lieth carnally with a woman, that is a bondmaid, betrothed to an husband, and not at all redeemed, nor freedom given her; she shall be scourged; they shall not be put to death, because she was not free. |
21 እርሱም የበደሉን መሥዋዕት ይዞ ወደ እግዚአብሔር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይመጣል፥ ለበደልም መሥዋዕት አውራ በግ ያመጣል። |
21 And he shall bring his trespass offering unto the Lord, unto the door of the tabernacle of the congregation, even a ram for a trespass offering. |
22 ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል የሠራውም ኃጢአት ይቀርለታል። |
22 And the priest shall make an atonement for him with the ram of the trespass offering before the Lord for his sin which he hath done: and the sin which he hath done shall be forgiven him. |
23 ወደ አገሩም በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ ሦስት ዓመት እንዳልተገረዘ ይሆንላችኋል አይበላም። |
23 And when ye shall come into the land, and shall have planted all manner of trees for food, then ye shall count the fruit thereof as uncircumcised: three years shall it be as uncircumcised unto you: it shall not be eaten of. |
24 የአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ቅዱስ ይሁን። |
24 But in the fourth year all the fruit thereof shall be holy to praise the Lord withal. |
25 ፍሬውም ይበዛላችሁ ዘንድ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
25 And in the fifth year shall ye eat of the fruit thereof, that it may yield unto you the increase thereof: I am the Lord your God. |
26 ከደሙ ጋር ምንም አትብሉ አስማትም አታድርጉ፥ ሞራ ገላጭም አትሁኑ። |
26 Ye shall not eat any thing with the blood: neither shall ye use enchantment, nor observe times. |
27 የራስ ጠጕራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቍረጡት። |
27 Ye shall not round the corners of your heads, neither shalt thou mar the corners of thy beard. |
28 ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
28 Ye shall not make any cuttings in your flesh for the dead, nor print any marks upon you: I am the Lord. |
29 ምድሪቱ ከግልሙትና ከርኵሰትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን ታመነዝር ዘንድ አታርክሳት። |
29 Do not prostitute thy daughter, to cause her to be a whore; lest the land fall to whoredom, and the land become full of wickedness. |
30 ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም አክብሩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
30 Ye shall keep my sabbaths, and reverence my sanctuary: I am the Lord. |
31 ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
31 Regard not them that have familiar spirits, neither seek after wizards, to be defiled by them: I am the Lord your God. |
32 በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
32 Thou shalt rise up before the hoary head, and honour the face of the old man, and fear thy God: I am the Lord. |
33 በአገራችሁ ውስጥ ከእናንተ ጋር እንግዳ ቢቀመጥ ግፍ አታድርጉበት። |
33 And if a stranger sojourn with thee in your land, ye shall not vex him. |
34 እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገር ልጅ ይሁንላችሁ፥ እርሱንም እንደ ራስህ ውደድ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
34 But the stranger that dwelleth with you shall be unto you as one born among you, and thou shalt love him as thyself; for ye were strangers in the land of Egypt: I am the Lord your God. |
35 በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም ዓመፃ አታድርጉ። |
35 Ye shall do no unrighteousness in judgment, in meteyard, in weight, or in measure. |
36 የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የኢፍ መስፈሪያ፥ የእውነትም የኢን መስፈሪያ ይሁንላችሁ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ። |
36 Just balances, just weights, a just ephah, and a just hin, shall ye have: I am the Lord your God, which brought you out of the land of Egypt. |
37 ሥርዓቴን ሁሉ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ አድርጉም እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
37 Therefore shall ye observe all my statutes, and all my judgments, and do them: I am the Lord. |