መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #128
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 128

Psalm 128

1 እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።

1 Blessed is every one that feareth the Lord; that walketh in his ways.

2 የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።

2 For thou shalt eat the labour of thine hands: happy shalt thou be, and it shall be well with thee.

3 ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።

3 Thy wife shall be as a fruitful vine by the sides of thine house: thy children like olive plants round about thy table.

4 እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።

4 Behold, that thus shall the man be blessed that feareth the Lord.

5 እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።

5 The Lord shall bless thee out of Zion: and thou shalt see the good of Jerusalem all the days of thy life.

6 የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።

6 Yea, thou shalt see thy children’s children, and peace upon Israel.