መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #127
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 127

Psalm 127

1 እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።

1 Except the Lord build the house, they labour in vain that build it: except the Lord keep the city, the watchman waketh but in vain.

2 በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።

2 It is vain for you to rise up early, to sit up late, to eat the bread of sorrows: for so he giveth his beloved sleep.

3 እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።

3 Lo, children are an heritage of the Lord: and the fruit of the womb is his reward.

4 በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥ የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው።

4 As arrows are in the hand of a mighty man; so are children of the youth.

5 ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ብፁዕ ሰው ነው ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም።

5 Happy is the man that hath his quiver full of them: they shall not be ashamed, but they shall speak with the enemies in the gate.