መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #89
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 89 |
Psalm 89 |
1 አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። |
1 I will sing of the mercies of the Lord for ever: with my mouth will I make known thy faithfulness to all generations. |
2 እንዲህ ብለሃልና። ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል። |
2 For I have said, Mercy shall be built up for ever: thy faithfulness shalt thou establish in the very heavens. |
3 ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት ማልሁ። |
3 I have made a covenant with my chosen, I have sworn unto David my servant, |
4 ዘርህን ለዘላለም አዘጋጃለሁ፥ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሠርታለሁ። |
4 Thy seed will I establish for ever, and build up thy throne to all generations. Selah. |
5 አቤቱ፥ ሰማያት ተኣምራትህን እውነትህንም ደግሞ በቅዱሳን ማኅበር ያመሰግናሉ። |
5 And the heavens shall praise thy wonders, O Lord: thy faithfulness also in the congregation of the saints. |
6 እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል? |
6 For who in the heaven can be compared unto the Lord? who among the sons of the mighty can be likened unto the Lord? |
7 በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። |
7 God is greatly to be feared in the assembly of the saints, and to be had in reverence of all them that are about him. |
8 አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እውነትህም ይከብብሃል። |
8 O Lord God of hosts, who is a strong Lord like unto thee? or to thy faithfulness round about thee? |
9 የባሕርን ኃይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ። |
9 Thou rulest the raging of the sea: when the waves thereof arise, thou stillest them. |
10 አንተ ረዓብን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኃይልህም ክንድ ጠላቶችህን በተንሃቸው። |
10 Thou hast broken Rahab in pieces, as one that is slain; thou hast scattered thine enemies with thy strong arm. |
11 ሰማያት የአንተ ናቸው፥ ምድርም የአንተ ናት ዓለምንና ሞላውም አንተ መሠረትህ። |
11 The heavens are thine, the earth also is thine: as for the world and the fulness thereof, thou hast founded them. |
12 ሰሜንና ደቡብን አንተ ፈጠርህ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል። |
12 The north and the south thou hast created them: Tabor and Hermon shall rejoice in thy name. |
13 ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች። |
13 Thou hast a mighty arm: strong is thy hand, and high is thy right hand. |
14 የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ ነው ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ። |
14 Justice and judgment are the habitation of thy throne: mercy and truth shall go before thy face. |
15 እልልታ የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ። |
15 Blessed is the people that know the joyful sound: they shall walk, O Lord, in the light of thy countenance. |
16 በስምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል፥ በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ |
16 In thy name shall they rejoice all the day: and in thy righteousness shall they be exalted. |
17 የኃይላቸው ትምክሕት አንተ ነህና፥ በሞገስህም ቀንዳችን ከፍ ከፍ ይላልና። |
17 For thou art the glory of their strength: and in thy favour our horn shall be exalted. |
18 ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ከንጉሣችንም ከእስራኤል ቅዱስ ነውና። |
18 For the Lord is our defence; and the Holy One of Israel is our king. |
19 በዚያ ጊዜ ለልጆችህ በራእይ ተናገርህ እንዲህም አልህ። ረድኤቴን በኃይል ላይ አኖርሁ ከሕዝቤ የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ። |
19 Then thou spakest in vision to thy holy one, and saidst, I have laid help upon one that is mighty; I have exalted one chosen out of the people. |
20 ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፥ ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት። |
20 I have found David my servant; with my holy oil have I anointed him: |
21 እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች። |
21 With whom my hand shall be established: mine arm also shall strengthen him. |
22 ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም፥ የዓመፃ ልጅም መከራ አይጨምርበትም። |
22 The enemy shall not exact upon him; nor the son of wickedness afflict him. |
23 ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ፥ የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ። |
23 And I will beat down his foes before his face, and plague them that hate him. |
24 እውነቴና ምሕረቴም ከእርሱ ጋር ነው፥ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል። |
24 But my faithfulness and my mercy shall be with him: and in my name shall his horn be exalted. |
25 እጁን በባሕር ላይ ቀኙንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ። |
25 I will set his hand also in the sea, and his right hand in the rivers. |
26 እርሱ። አባቴ አንተ ነህ፥ አምላኬ የመድኃኒቴም መጠጊያ ይላል። |
26 He shall cry unto me, Thou art my father, my God, and the rock of my salvation. |
27 እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፥ ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል። |
27 Also I will make him my firstborn, higher than the kings of the earth. |
28 ለዘላለምም ምሕረቴን ለእርሱ እጠብቃለሁ፥ ኪዳኔም በእርሱ ዘንድ የታመነ ነው። |
28 My mercy will I keep for him for evermore, and my covenant shall stand fast with him. |
29 ዘሩንም ለዓለምና ለዘላለም፥ ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ። |
29 His seed also will I make to endure for ever, and his throne as the days of heaven. |
30 ልጆቹ ግን ሕጌን ቢተዉ፥ በፍርዴም ባይሄዱ |
30 If his children forsake my law, and walk not in my judgments; |
31 ሥርዓቴንም ቢያረክሱ፥ ትእዛዜንም ባይጠብቁ |
31 If they break my statutes, and keep not my commandments; |
32 ኃጢአታቸውን በበትር፥ በደላቸውንም በመቅሠፍት እጐበኛታለሁ። |
32 Then will I visit their transgression with the rod, and their iniquity with stripes. |
33 ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፥ በእውነቴም አልበድልም |
33 Nevertheless my lovingkindness will I not utterly take from him, nor suffer my faithfulness to fail. |
34 ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም። |
34 My covenant will I not break, nor alter the thing that is gone out of my lips. |
35 ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ። |
35 Once have I sworn by my holiness that I will not lie unto David. |
36 ዘሩ ለዘላለም፥ ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሐይ ይኖራል። |
36 His seed shall endure for ever, and his throne as the sun before me. |
37 ለዘላለም እንደ ጨረቃ ይጸናል ምስክርነቱ በሰማይ የታመን ነው። |
37 It shall be established for ever as the moon, and as a faithful witness in heaven. Selah. |
38 አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ የቀባኸውንም ጣልኸው። |
38 But thou hast cast off and abhorred, thou hast been wroth with thine anointed. |
39 የባሪያህንም ኪዳን አፈረስህ፥ መቅደሱንም በምድር አረከስህ። |
39 Thou hast made void the covenant of thy servant: thou hast profaned his crown by casting it to the ground. |
40 ቅጥሩን ሁሉ ጣልህ፥ አምባዎቹንም አጠፋህ። |
40 Thou hast broken down all his hedges; thou hast brought his strong holds to ruin. |
41 መንገድ አላፊም ሁሉ ተናጠቀው፥ ለጎረቤቶቹም ስድብ ሆነ። |
41 All that pass by the way spoil him: he is a reproach to his neighbours. |
42 የጠላቶቹንም ቀኝ ከፍ ከፍ አደረግህ፥ ጠላቶቹንም ሁሉ ደስ አሰኘህ። |
42 Thou hast set up the right hand of his adversaries; thou hast made all his enemies to rejoice. |
43 የሰይፉንም ረድኤት መለስህ፥ በሰልፍም ውስጥ አልደገፍኸውም። |
43 Thou hast also turned the edge of his sword, and hast not made him to stand in the battle. |
44 ከንጽሕናውም ሻርኸው፥ ዙፋኑንም በምድር ጣልህ። |
44 Thou hast made his glory to cease, and cast his throne down to the ground. |
45 የዙፋኑንም ዘመን አሳነስህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው። |
45 The days of his youth hast thou shortened: thou hast covered him with shame. Selah. |
46 አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ፊትህን ትመልሳለህ? እስከ መቼስ ቍጣህ እንደ እሳት ይነድዳል? |
46 How long, Lord? wilt thou hide thyself for ever? shall thy wrath burn like fire? |
47 ችሎታዬ ምን እንደ ሆነ አስብ በውኑ የሰውን ልጅ ሁሉ ለከንቱ ፈጠርኸውን? |
47 Remember how short my time is: wherefore hast thou made all men in vain? |
48 ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው? ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው? |
48 What man is he that liveth, and shall not see death? shall he deliver his soul from the hand of the grave? Selah. |
49 ለዳዊት በእውነት የማልህ፥ አቤቱ፥ የቀድሞ ምሕረትህ ወዴት ነው? |
49 Lord, where are thy former lovingkindnesses, which thou swarest unto David in thy truth? |
50 አቤቱ፥ የባሪያዎችህን ስድብ፥ በብብቴ ብዙ አሕዛብን የተቀበልሁትን፥ |
50 Remember, Lord, the reproach of thy servants; how I do bear in my bosom the reproach of all the mighty people; |
51 አቤቱ፥ ጠላቶችህን የሰደቡትን የቀባኸውን ዘመን የሰደቡትን አስብ። |
51 Wherewith thine enemies have reproached, O Lord; wherewith they have reproached the footsteps of thine anointed. |
52 እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ። ይሁን ይሁን። |
52 Blessed be the Lord for evermore. Amen, and Amen. |