መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #88
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 88 |
Psalm 88 |
1 አቤቱ፥ የመድኃኒቴ አምላክ፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ |
1 O Lord God of my salvation, I have cried day and night before thee: |
2 ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል |
2 Let my prayer come before thee: incline thine ear unto my cry; |
3 ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለችና። |
3 For my soul is full of troubles: and my life draweth nigh unto the grave. |
4 ወደ ጓድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ። |
4 I am counted with them that go down into the pit: I am as a man that hath no strength: |
5 ለዘላለም እንደማታስባቸው፥ እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ በሙታን ውስጥ እንዳሉ የተጣልሁ ሆንሁ እነርሱም ከእጅህ ተለዩ። |
5 Free among the dead, like the slain that lie in the grave, whom thou rememberest no more: and they are cut off from thy hand. |
6 በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጕድጓድ አስቀመጥኸኝ። |
6 Thou hast laid me in the lowest pit, in darkness, in the deeps. |
7 በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥ መቅሠፍትህን ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ። |
7 Thy wrath lieth hard upon me, and thou hast afflicted me with all thy waves. Selah. |
8 የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ በእነርሱ ዘንድ ርኵስ አደረግኸኝ ያዙኝ፥ መውጫም የለኝም። |
8 Thou hast put away mine acquaintance far from me; thou hast made me an abomination unto them: I am shut up, and I cannot come forth. |
9 ዓይኖቼም በመከራ ፈዘዙ አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ፥ |
9 Mine eye mourneth by reason of affliction: Lord, I have called daily upon thee, I have stretched out my hands unto thee. |
10 በውኑ ለሙታን ተኣምራት ታደርጋለህን? የሞቱትስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? |
10 Wilt thou shew wonders to the dead? shall the dead arise and praise thee? Selah. |
11 በመቃብርስ ውስጥ ቸርነትህን፥ እውነትህንስ በጥፋት ስፍራ ይናገራሉን? |
11 Shall thy lovingkindness be declared in the grave? or thy faithfulness in destruction? |
12 ተአምራትህ በጨለማ፥ ጽድቅህንም በመርሳት ምድር ትታወቃለችን? |
12 Shall thy wonders be known in the dark? and thy righteousness in the land of forgetfulness? |
13 አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች። |
13 But unto thee have I cried, O Lord; and in the morning shall my prayer prevent thee. |
14 አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ? |
14 Lord, why castest thou off my soul? why hidest thou thy face from me? |
15 እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ ከፍ ከፍ ካልሁ በኋላ ግን ተዋረድሁ ተናቅሁም። |
15 I am afflicted and ready to die from my youth up: while I suffer thy terrors I am distracted. |
16 መቅሠፍትህ በላዬ አለፈ፥ ግርማህም አስደነገጠኝ። |
16 Thy fierce wrath goeth over me; thy terrors have cut me off. |
17 ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድነትም ያዙኝ። |
17 They came round about me daily like water; they compassed me about together. |
18 ወዳጄንና ባልንጀራዬን ዘመዶቼንም ከመከራ የተነሣ ከእኔ አራቅህ። |
18 Lover and friend hast thou put far from me, and mine acquaintance into darkness. |