ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #39
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 39

Exodus 39

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም በብልሃት የተሠራ ልብስ፥ ለአሮንም የተቀደሰውን ልብስ አደረጉ።

1 And of the blue, and purple, and scarlet, they made cloths of service, to do service in the holy place, and made the holy garments for Aaron; as the Lord commanded Moses.

2 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ ኤፉዱን ከወርቅ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረገ።

2 And he made the ephod of gold, blue, and purple, and scarlet, and fine twined linen.

3 ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አድርገው እንደ ፈትል ቈረጡ። ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ ሰማያዊ ሐምራዊም ቀይም ግምጃ የተፈተለም ጥሩ በፍታ ከእርሱ ጠለፉ።

3 And they did beat the gold into thin plates, and cut it into wires, to work it in the blue, and in the purple, and in the scarlet, and in the fine linen, with cunning work.

4 ሁለቱ ወገን እንዲጋጠም በሁለቱ ጫንቃዎች ላይ የሚጋጠም ልብስ አደረጉት።

4 They made shoulderpieces for it, to couple it together: by the two edges was it coupled together.

5 በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቋድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ነበረ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ።

5 And the curious girdle of his ephod, that was upon it, was of the same, according to the work thereof; of gold, blue, and purple, and scarlet, and fine twined linen; as the Lord commanded Moses.

6 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ በወርቅ ፈርጥ የተያዙ የመረግድ ድንጋዮች ሠርተው እንደ ማኅተም ቅርጽ የእስራኤልን ልጆች ስም ቀረጹባቸው።

6 And they wrought onyx stones inclosed in ouches of gold, graven, as signets are graven, with the names of the children of Israel.

7 ለእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ጫንቃዎች ላይ አደረጋቸው።

7 And he put them on the shoulders of the ephod, that they should be stones for a memorial to the children of Israel; as the Lord commanded Moses.

8 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ የደረቱን ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ እንደ ኤፉዱ አሠራር ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረገው።

8 And he made the breastplate of cunning work, like the work of the ephod; of gold, blue, and purple, and scarlet, and fine twined linen.

9 አራት ማዕዘንም ነበረ የደረቱን ኪስም ድርብ አደረጉ ርዝመቱ ስንዝር፥ ወርዱም ስንዝር፥ ድርብም ነበረ።

9 It was foursquare; they made the breastplate double: a span was the length thereof, and a span the breadth thereof, being doubled.

10 ዕንቍዎቹንም በአራት ተራ አደረጉበት በፊተኛውም ተራ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ

10 And they set in it four rows of stones: the first row was a sardius, a topaz, and a carbuncle: this was the first row.

11 በሁለተኛውም ተራ በሉር፥ ሰንፔር፥ አልማዝ

11 And the second row, an emerald, a sapphire, and a diamond.

12 በሦስተኛውም ተራ ያክንት፥ ኬልቄዶን፥ አሜቴስጢኖስ

12 And the third row, a ligure, an agate, and an amethyst.

13 በአራተኛውም ተራ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ።

13 And the fourth row, a beryl, an onyx, and a jasper: they were inclosed in ouches of gold in their inclosings.

14 የዕንቍዎችም ድንጋዮች እንደ አሥራ ሁለቱ እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ነበሩ በየስማቸውም ማተሚያ እንደሚቀረጽ ተቀረጹ፥ ስለ አሥራ ሁለቱም ነገዶች ነበሩ።

14 And the stones were according to the names of the children of Israel, twelve, according to their names, like the engravings of a signet, every one with his name, according to the twelve tribes.

15 ለደረቱ ኪስም የተጐነጐኑትን ድሪዎች እንደ ገመድ አድርገው ከጥሩ ወርቅ ሠሩ።

15 And they made upon the breastplate chains at the ends, of wreathen work of pure gold.

16 ሁለትም የወርቅ ፈርጦች፥ ሁለትም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረቱ ኪስ በሁለቱ ወገን አደረጉ።

16 And they made two ouches of gold, and two gold rings; and put the two rings in the two ends of the breastplate.

17 ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በደረቱ ኪስ ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች አገቡ።

17 And they put the two wreathen chains of gold in the two rings on the ends of the breastplate.

18 የሁለቱንም ድሪዎች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተው በኤፉዱ ጫንቃዎች ላይ በፊታቸው አደረጉ።

18 And the two ends of the two wreathen chains they fastened in the two ouches, and put them on the shoulderpieces of the ephod, before it.

19 ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለት ጫፎቹ ላይ አደረጉአቸው።

19 And they made two rings of gold, and put them on the two ends of the breastplate, upon the border of it, which was on the side of the ephod inward.

20 ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ በኤፉዱም ፊት፥ ከጫንቃዎች በታች፥ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ፥ በመያዣው አጠገብ አደረጉአቸው።

20 And they made two other golden rings, and put them on the two sides of the ephod underneath, toward the forepart of it, over against the other coupling thereof, above the curious girdle of the ephod.

21 የደረቱ ኪስ በብልሃት ከተጠለፈው ከኤፉዱ ቋድ በላይ እንዲሆን፥ ከኤፉዱም እንዳይለይ የደረቱን ኪስ ከቀለበቶቹ ጋር ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል አሰሩት።

21 And they did bind the breastplate by his rings unto the rings of the ephod with a lace of blue, that it might be above the curious girdle of the ephod, and that the breastplate might not be loosed from the ephod; as the Lord commanded Moses.

22 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ የኤፉዱን ቀሚስ ሞላውን በሸማኔ ሥራ ሰማያዊ አደረገው።

22 And he made the robe of the ephod of woven work, all of blue.

23 በቀሚሱም መካከል አንገትጌ ነበረ እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ነበረ።

23 And there was an hole in the midst of the robe, as the hole of an habergeon, with a band round about the hole, that it should not rend.

24 በቀሚሱም ታችኛ ዘርፍ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለ በፍታም ሮማኖች አደረጉ።

24 And they made upon the hems of the robe pomegranates of blue, and purple, and scarlet, and twined linen.

25 ከጥሩ ወርቅም ሻኵራዎችን ሠሩ፥ ሻኵራዎቹንም ከሮማኖች መካከል በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ አደረጉ።

25 And they made bells of pure gold, and put the bells between the pomegranates upon the hem of the robe, round about between the pomegranates;

26 በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵራንና ሮማንን፥ ሻኵራንና ሮማንን ለማገልገል አደረጉ።

26 A bell and a pomegranate, a bell and a pomegranate, round about the hem of the robe to minister in; as the Lord commanded Moses.

27 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ እንደ ሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን፥

27 And they made coats of fine linen of woven work for Aaron, and for his sons,

28 ከጥሩ በፍታም መጠምጠሚያውን፥ ከጥሩ በፍታም መልካሞቹን ቆቦች፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ የእግር ሱሪዎችን፥

28 And a mitre of fine linen, and goodly bonnets of fine linen, and linen breeches of fine twined linen,

29 ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ በጥልፍ አሠራር የተሠራ መታጠቂያውን አደረጉ።

29 And a girdle of fine twined linen, and blue, and purple, and scarlet, of needlework; as the Lord commanded Moses.

30 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ ከጥሩ ወርቅ የተቀደሰውን የአክሊል ምልክት ሠሩ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገው። ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ጻፉበት።

30 And they made the plate of the holy crown of pure gold, and wrote upon it a writing, like to the engravings of a signet, HOLINESS TO THE Lord.

31 በመጠምጠሚያውም ላይ ያንጠለጥሉት ዘንድ ሰማያዊውን ፈትል አሰሩበት።

31 And they tied unto it a lace of blue, to fasten it on high upon the mitre; as the Lord commanded Moses.

32 እንዲሁም የመገናኛው ድንኳን የማደሪያው ሥራ ሁሉ ተጨረሰ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ የእስራኤል ልጆች አደረጉ እንዲሁ አደረጉ።

32 Thus was all the work of the tabernacle of the tent of the congregation finished: and the children of Israel did according to all that the Lord commanded Moses, so did they.

33 ማደሪያውንም፥ ድንኳኑንም፥ ዕቃውንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም

33 And they brought the tabernacle unto Moses, the tent, and all his furniture, his taches, his boards, his bars, and his pillars, and his sockets,

34 ከቀይ ከአውራ በግ ቁርበትም የተሠራ መደረቢያ፥ ከአቆስጣ ቁርበትም የተሠራ መደረቢያ፥ የሚሸፍነውንም መጋረጃ

34 And the covering of rams’ skins dyed red, and the covering of badgers’ skins, and the vail of the covering,

35 የምስክሩንም ታቦት፥ መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም

35 The ark of the testimony, and the staves thereof, and the mercy seat,

36 ገበታውንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ኅብስት

36 The table, and all the vessels thereof, and the shewbread,

37 ጥሩውንም መቅረዝ፥ መብራቶቹንም፥ በተራ የሚሆኑትንም ቀንዲሎች፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመብራቱንም ዘይት

37 The pure candlestick, with the lamps thereof, even with the lamps to be set in order, and all the vessels thereof, and the oil for light,

38 የወርቁንም መሠዊያ፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ የድንኳኑንም ደጃፍ መጋረጃ

38 And the golden altar, and the anointing oil, and the sweet incense, and the hanging for the tabernacle door,

39 የናሱንም መሠዊያ፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም

39 The brasen altar, and his grate of brass, his staves, and all his vessels, the laver and his foot,

40 የአደባባዩንም መጋረጆች፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቹንም፥ ካስማዎቹንም፥ ለመገናኛው ድንኳን ለማደሪያው ማገልገያ የሚሆኑን ዕቃዎች ሁሉ

40 The hangings of the court, his pillars, and his sockets, and the hanging for the court gate, his cords, and his pins, and all the vessels of the service of the tabernacle, for the tent of the congregation,

41 በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች አመጡ።

41 The cloths of service to do service in the holy place, and the holy garments for Aaron the priest, and his sons’ garments, to minister in the priest’s office.

42 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ሁሉ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች ሥራውን ሁሉ ሠሩ።

42 According to all that the Lord commanded Moses, so the children of Israel made all the work.

43 ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆም አድርገውት ነበር እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር ሙሴም ባረካቸው።

43 And Moses did look upon all the work, and, behold, they had done it as the Lord had commanded, even so had they done it: and Moses blessed them.