ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #6
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘዳግም 6 |
Deuteronomy 6 |
1-2 አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት። |
1 Now these are the commandments, the statutes, and the judgments, which the Lord your God commanded to teach you, that ye might do them in the land whither ye go to possess it: |
3 እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ መልካምም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዛ፥ ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ። |
3 Hear therefore, O Israel, and observe to do it; that it may be well with thee, and that ye may increase mightily, as the Lord God of thy fathers hath promised thee, in the land that floweth with milk and honey. |
4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው |
4 Hear, O Israel: The Lord our God is one Lord: |
5 አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። |
5 And thou shalt love the Lord thy God with all thine heart, and with all thy soul, and with all thy might. |
6 እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። |
6 And these words, which I command thee this day, shall be in thine heart: |
7 ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። |
7 And thou shalt teach them diligently unto thy children, and shalt talk of them when thou sittest in thine house, and when thou walkest by the way, and when thou liest down, and when thou risest up. |
8 በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። |
8 And thou shalt bind them for a sign upon thine hand, and they shall be as frontlets between thine eyes. |
9 በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። |
9 And thou shalt write them upon the posts of thy house, and on thy gates. |
10 አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥ |
10 And it shall be, when the Lord thy God shall have brought thee into the land which he sware unto thy fathers, to Abraham, to Isaac, and to Jacob, to give thee great and goodly cities, which thou buildedst not, |
11 ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጕድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ |
11 And houses full of all good things, which thou filledst not, and wells digged, which thou diggedst not, vineyards and olive trees, which thou plantedst not; when thou shalt have eaten and be full; |
12 በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። |
12 Then beware lest thou forget the Lord, which brought thee forth out of the land of Egypt, from the house of bondage. |
13 አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ እርሱንም አምልክ በስሙም ማል። |
13 Thou shalt fear the Lord thy God, and serve him, and shalt swear by his name. |
14-15 በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና የአምላክህ የእግዚአብሔር ቍጣ እንዳይነድድብህ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ፥ በዙሪያችሁ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተሉ። |
14 Ye shall not go after other gods, of the gods of the people which are round about you; |
16 በማሳህ እንደ ፈተናችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት። |
16 Ye shall not tempt the Lord your God, as ye tempted him in Massah. |
17 ለእናንተ ያዘዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ምስክሩንም ሥርዓቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ። |
17 Ye shall diligently keep the commandments of the Lord your God, and his testimonies, and his statutes, which he hath commanded thee. |
18-19 መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያወጣልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ። |
18 And thou shalt do that which is right and good in the sight of the Lord: that it may be well with thee, and that thou mayest go in and possess the good land which the Lord sware unto thy fathers, |
20 በኋለኛው ዘመንም ልጅህ። አምላካችን እግዚአብሔር ያዘዛችሁ ምስክርና ሥርዓት ፍርድስ ምንድር ነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ |
20 And when thy son asketh thee in time to come, saying, What mean the testimonies, and the statutes, and the judgments, which the Lord our God hath commanded you? |
21 አንተ ልጅህን በለው። በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ነበርን እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ ከግብፅ አወጣን |
21 Then thou shalt say unto thy son, We were Pharaoh’s bondmen in Egypt; and the Lord brought us out of Egypt with a mighty hand: |
22 እግዚአብሔርም ከግብፅና በፈርዖን በቤቱም ሁሉ ላይ እኛ እያየን ታላቅና ክፉ ምልክት ተአምራትም አደረገ። |
22 And the Lord shewed signs and wonders, great and sore, upon Egypt, upon Pharaoh, and upon all his household, before our eyes: |
23 ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር አግብቶ እርስዋን ይሰጠን ዘንድ ከዚያ አወጣን። |
23 And he brought us out from thence, that he might bring us in, to give us the land which he sware unto our fathers. |
24 እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። |
24 And the Lord commanded us to do all these statutes, to fear the Lord our God, for our good always, that he might preserve us alive, as it is at this day. |
25 እርሱም እንዳዘዘን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እናደርጋት ዘንድ ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል። |
25 And it shall be our righteousness, if we observe to do all these commandments before the Lord our God, as he hath commanded us. |