መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #14
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 14

Ps 14

1 ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።

1 The fool hath said in his heart, There is no God. They are corrupt, they have done abominable works, there is none that doeth good.

2 የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።

2 The Lord looked down from heaven upon the children of men, to see if there were any that did understand, and seek God.

3 ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም አንድም ስንኳ የለም።

3 They are all gone aside, they are all together become filthy: there is none that doeth good, no, not one.

4 ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ

4 Have all the workers of iniquity no knowledge? who eat up my people as they eat bread, and call not upon the Lord.

5 ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል

5 There were they in great fear: for God is in the generation of the righteous.

6 ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።

6 Ye have shamed the counsel of the poor, because the Lord is his refuge.

7 ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።

7 Oh that the salvation of Israel were come out of Zion! when the Lord bringeth back the captivity of his people, Jacob shall rejoice, and Israel shall be glad.

8 በዚያ በታላቅ ፍርሃት እጅግ ፈሩ፥ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።

9 የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።

10 ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።