መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #132
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 132 |
Psalm 132 |
1 አቤቱ፥ ዳዊትን ገርነቱንም ሁሉ አስብ |
1 Lord, remember David, and all his afflictions: |
2 ለእግዚአብሔር እንደ ማለ፥ ለያዕቆብም አምላክ እንደ ተሳለ። |
2 How he sware unto the Lord, and vowed unto the mighty God of Jacob; |
3 በእውነት ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥ ወደ ምንጣፌም አልጋ አልወጣም፥ |
3 Surely I will not come into the tabernacle of my house, nor go up into my bed; |
4 ለዓይኖቼም መኝታ ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ፥ ለጕንጮቼም ዕረፍትን አልሰጥም፥ |
4 I will not give sleep to mine eyes, or slumber to mine eyelids, |
5 ለእግዚአብሔር ስፍራ፥ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ። |
5 Until I find out a place for the Lord, an habitation for the mighty God of Jacob. |
6 እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥ በዱር ውስጥም አገኘነው። |
6 Lo, we heard of it at Ephratah: we found it in the fields of the wood. |
7 ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን። |
7 We will go into his tabernacles: we will worship at his footstool. |
8 አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። |
8 Arise, O Lord, into thy rest; thou, and the ark of thy strength. |
9 ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። |
9 Let thy priests be clothed with righteousness; and let thy saints shout for joy. |
10 ስለ ዳዊት ስለ ባሪያህ የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ። |
10 For thy servant David’s sake turn not away the face of thine anointed. |
11 እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ። ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ። |
11 The Lord hath sworn in truth unto David; he will not turn from it; Of the fruit of thy body will I set upon thy throne. |
12 ልጆችህ ኪዳኔን፥ ይህንም የማስተምራቸውን ምስክሬን ቢጠብቁ፥ ልጆቻቸው ደግሞ በዙፋንህ ላይ ለዘላለም ይቀመጣሉ። |
12 If thy children will keep my covenant and my testimony that I shall teach them, their children shall also sit upon thy throne for evermore. |
13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ። |
13 For the Lord hath chosen Zion; he hath desired it for his habitation. |
14 ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ። |
14 This is my rest for ever: here will I dwell; for I have desired it. |
15 አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ። |
15 I will abundantly bless her provision: I will satisfy her poor with bread. |
16 ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል። |
16 I will also clothe her priests with salvation: and her saints shall shout aloud for joy. |
17 በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። |
17 There will I make the horn of David to bud: I have ordained a lamp for mine anointed. |
18 ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል። |
18 His enemies will I clothe with shame: but upon himself shall his crown flourish. |