መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #108
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 108

Psalm 108

1 ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው እቀኛለሁ በክብሬም እዘምራለሁ።

1 O God, my heart is fixed; I will sing and give praise, even with my glory.

2 በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

2 Awake, psaltery and harp: I myself will awake early.

3 አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም መካከል እዘምርልሃለሁ

3 I will praise thee, O Lord, among the people: and I will sing praises unto thee among the nations.

4 ምሕረትህ በሰማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነውና።

4 For thy mercy is great above the heavens: and thy truth reacheth unto the clouds.

5 አቤቱ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

5 Be thou exalted, O God, above the heavens: and thy glory above all the earth;

6 ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ በቀኝህ አድን አድምጠኝም።

6 That thy beloved may be delivered: save with thy right hand, and answer me.

7 እግዚአብሔር በቅድስናው ተናገረ። ደስ ይለኛል፥ ሴኬምንም እካፈላለሁ፥ የሱኮትንም ሸለቆ እሰፍራለሁ።

7 God hath spoken in his holiness; I will rejoice, I will divide Shechem, and mete out the valley of Succoth.

8 ገለዓድ የእኔ ነው ምናሴም የእኔ ነው ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው።

8 Gilead is mine; Manasseh is mine; Ephraim also is the strength of mine head; Judah is my lawgiver;

9 ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ ፍልስጥኤም ይገዙልኛል።

9 Moab is my washpot; over Edom will I cast out my shoe; over Philistia will I triumph.

10 ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?

10 Who will bring me into the strong city? who will lead me into Edom?

11 አቤቱ፥ የጣልኸኝ አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።

11 Wilt not thou, O God, who hast cast us off? and wilt not thou, O God, go forth with our hosts?

12 በመከራችን ረድኤትን ስጠን የሰውም ማዳን ከንቱ ነው።

12 Give us help from trouble: for vain is the help of man.

13 በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።

13 Through God we shall do valiantly: for he it is that shall tread down our enemies.