ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #2
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘዳግም 2

Deuteronomy 2

1 እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።

1 Then we turned, and took our journey into the wilderness by the way of the Red sea, as the Lord spake unto me: and we compassed mount Seir many days.

2 እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።

2 And the Lord spake unto me, saying,

3 ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ።

3 Ye have compassed this mountain long enough: turn you northward.

4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው። በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።

4 And command thou the people, saying, Ye are to pass through the coast of your brethren the children of Esau, which dwell in Seir; and they shall be afraid of you: take ye good heed unto yourselves therefore:

5 የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።

5 Meddle not with them; for I will not give you of their land, no, not so much as a foot breadth; because I have given mount Seir unto Esau for a possession.

6 ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ ውኃም ደግሞ በገንዘብ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ።

6 Ye shall buy meat of them for money, that ye may eat; and ye shall also buy water of them for money, that ye may drink.

7 አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም።

7 For the Lord thy God hath blessed thee in all the works of thy hand: he knoweth thy walking through this great wilderness: these forty years the Lord thy God hath been with thee; thou hast lacked nothing.

8 በሴይርም ከተቀመጡት ከወንድሞቻችን ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮንጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።

8 And when we passed by from our brethren the children of Esau, which dwelt in Seir, through the way of the plain from Elath, and from Ezion–gaber, we turned and passed by the way of the wilderness of Moab.

9 እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓብን አትጣላ በሰልፍም አትውጋቸው።

9 And the Lord said unto me, Distress not the Moabites, neither contend with them in battle: for I will not give thee of their land for a possession; because I have given Ar unto the children of Lot for a possession.

10 አስቀድሞ ታላቅና ብዙ ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች በቁመት የረዘሙ ኤሚማውያን በዚያ ይቀመጡ ነበር።

10 The Emims dwelt therein in times past, a people great, and many, and tall, as the Anakims;

11 እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል።

11 Which also were accounted giants, as the Anakims; but the Moabites call them Emims.

12 ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን አሳደዱአቸው እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።

12 The Horims also dwelt in Seir beforetime; but the children of Esau succeeded them, when they had destroyed them from before them, and dwelt in their stead; as Israel did unto the land of his possession, which the Lord gave unto them.

13 እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ አለ።

13 Now rise up, said I, and get you over the brook Zered. And we went over the brook Zered.

14 የዘሬድንም ፈፋ ተሻገርን። የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው የሰልፈኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።

14 And the space in which we came from Kadesh–barnea, until we were come over the brook Zered, was thirty and eight years; until all the generation of the men of war were wasted out from among the host, as the Lord sware unto them.

15 ከሰፈርም መካከል ተቈርጠው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ።

15 For indeed the hand of the Lord was against them, to destroy them from among the host, until they were consumed.

16 እንዲህም ሆነ ሰልፈኞቹ ከጠፉ ከሕዝቡም መካከል ከሞቱ በኋላ፥

16 So it came to pass, when all the men of war were consumed and dead from among the people,

17 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።

17 That the Lord spake unto me, saying,

18 አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ

18 Thou art to pass over through Ar, the coast of Moab, this day:

19 ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው አትውጋቸውም።

19 And when thou comest nigh over against the children of Ammon, distress them not, nor meddle with them: for I will not give thee of the land of the children of Ammon any possession; because I have given it unto the children of Lot for a possession.

20 ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሩአቸዋል።

20 (That also was accounted a land of giants: giants dwelt therein in old time; and the Ammonites call them Zamzummims;

21 ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ እግዚአብሔር ከፊታቸው አጠፋቸው እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።

21 A people great, and many, and tall, as the Anakims; but the Lord destroyed them before them; and they succeeded them, and dwelt in their stead:

22 ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።

22 As he did to the children of Esau, which dwelt in Seir, when he destroyed the Horims from before them; and they succeeded them, and dwelt in their stead even unto this day:

23 እስከ ጋዛም ድረስ በመንደሮች ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንን ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።

23 And the Avims which dwelt in Hazerim, even unto Azzah, the Caphtorims, which came forth out of Caphtor, destroyed them, and dwelt in their stead.)

24 ደግሞም አለ። ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ እርስዋን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።

24 Rise ye up, take your journey, and pass over the river Arnon: behold, I have given into thine hand Sihon the Amorite, king of Heshbon, and his land: begin to possess it, and contend with him in battle.

25 ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።

25 This day will I begin to put the dread of thee and the fear of thee upon the nations that are under the whole heaven, who shall hear report of thee, and shall tremble, and be in anguish because of thee.

26 ከቅዴሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ። በአገርህ ላይ ልለፍ

26 And I sent messengers out of the wilderness of Kedemoth unto Sihon king of Heshbon with words of peace, saying,

27 በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም።

27 Let me pass through thy land: I will go along by the high way, I will neither turn unto the right hand nor to the left.

28-29 የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፥ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ ስጠኝ በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች በዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ ብቻ በእግሬ ልለፍ።

28 Thou shalt sell me meat for money, that I may eat; and give me water for money, that I may drink: only I will pass through on my feet;
29 (As the children of Esau which dwell in Seir, and the Moabites which dwell in Ar, did unto me;) until I shall pass over Jordan into the land which the Lord our God giveth us.

30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና።

30 But Sihon king of Heshbon would not let us pass by him: for the Lord thy God hardened his spirit, and made his heart obstinate, that he might deliver him into thy hand, as appeareth this day.

31 እግዚአብሔርም፦ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ፥ ጀመርሁ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር አለኝ።

31 And the Lord said unto me, Behold, I have begun to give Sihon and his land before thee: begin to possess, that thou mayest inherit his land.

32 ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ።

32 Then Sihon came out against us, he and all his people, to fight at Jahaz.

33 አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ ሰጠን እርሱንም ልጆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ መታን።

33 And the Lord our God delivered him before us; and we smote him, and his sons, and all his people.

34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ሰዎች ሁሉ ሴቶችንም ሕፃናቶችንም አጠፋን አንዳችም አላስቀረንም፥

34 And we took all his cities at that time, and utterly destroyed the men, and the women, and the little ones, of every city, we left none to remain:

35 ከብቶቻቸውንና ከከተሞቻቸው ያገኘነውን ብዝበዛ ለራሳችን ወሰድን እንጂ።

35 Only the cattle we took for a prey unto ourselves, and the spoil of the cities which we took.

36 በአርኖን ቈላ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ ማናቸይቱም ከተማ አልጠነከረችብንም አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።

36 From Aroer, which is by the brink of the river of Arnon, and from the city that is by the river, even unto Gilead, there was not one city too strong for us: the Lord our God delivered all unto us:

37 ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ሁሉ፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም።

37 Only unto the land of the children of Ammon thou camest not, nor unto any place of the river Jabbok, nor unto the cities in the mountains, nor unto whatsoever the Lord our God forbad us.