መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #46
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 46 |
Ps 46 |
1 አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። |
1 God is our refuge and strength, a very present help in trouble. |
2 ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። |
2 Therefore will not we fear, though the earth be removed, and though the mountains be carried into the midst of the sea; |
3 ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ። |
3 Though the waters thereof roar and be troubled, though the mountains shake with the swelling thereof. Selah. |
4 የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ። |
4 There is a river, the streams whereof shall make glad the city of God, the holy place of the tabernacles of the most High. |
5 እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል። |
5 God is in the midst of her; she shall not be moved: God shall help her, and that right early. |
6 አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች። |
6 The heathen raged, the kingdoms were moved: he uttered his voice, the earth melted. |
7 የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። |
7 The Lord of hosts is with us; the God of Jacob is our refuge. Selah. |
8 የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ። |
8 Come, behold the works of the Lord, what desolations he hath made in the earth. |
9 እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል። ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቈርጣል በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል። |
9 He maketh wars to cease unto the end of the earth; he breaketh the bow, and cutteth the spear in sunder; he burneth the chariot in the fire. |
10 ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። |
10 Be still, and know that I am God: I will be exalted among the heathen, I will be exalted in the earth. |
11 የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። |
11 The Lord of hosts is with us; the God of Jacob is our refuge. Selah. |